ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፳፰
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ዕለተ ጌና በዓል
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ይህም እንዲህ ነው በአምላካችን በረቀቀ ጥበቡ ሰዎች ሁሉ ይቈጠሩ ዘንድ ስማቸውንም ይጻፉና ይመዘገቡ ዘንድ ከንጉሥ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ፤ ስለዚህም ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም ጋር ሊቈጠር ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም የርሱንና የቡርክት ድንግል ማርያምንም ስም ሊአስመዘግብ ወጣ፤ እርሱ ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ወገን ነውና ቤተልሔምም የዳዊት ቦታው ናትና።
❖ የከበረ ወንጌል እንደተናገረ ከዚህም በኋላ ከዚያ ሳሉ የምትወልድበት ቀን ደረሰ የበኲር ልጅዋንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሠረችው በጨርቅም ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ለማደሪያቸው ቦታ አልነበራቸውምና።
❖ በዚያም ሰፈር እረኞች ነበሩ ሌሊቱንም በየተራቸው ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ አጠገባቸው ቆመ የእግዚአብሔርም ብርሃን በላያቸው በራ ታላቅ ፍርሀትንም ፈሩ መልአኩም ለእናንተና ለመላው ዓለም ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ አላቸው።
❖ እነሆ ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን የሆነ ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋልና፤ ለእናንተም ምልክቱ እንዲህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱን ታሥሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ አላቸው።
❖ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው በጎ ፈቃድ እያሉ መጡ፤ ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ባረጉ ጊዜ እነዚያ እረኞች ሰዎች እርስበርሳቸው ኑ ወደ ቤተ ልሔም ሔደን ይህን እግዚአብሔር የገለጠልንን ነገር እንወቅ አሉ።
❖ ፈጥነውም ሔዱ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝቶ አገኟቸው። አይተውም የነገሩዋቸው ስለዚህ ሕፃን እንደሆነ አወቁ እረኞች የነገሩዋቸውን የሰሙ ሁሉ አደነቁ፤ እረኞችም ለሕፃኑ ሰግደው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቦታቸው ተመለሱ።
ከወገናችን ሰው ሁኖ ለጐበኘንና ይቅር ላለን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ዕለት ደግሞ ከእንዴናው አገር ሰዎች መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ፤ እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ።
❖ ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት፤ በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና።
❖ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ፤ የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው።
❖ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
በዚችም ቀን የአባቶቻችን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ መታሰቢያ ነው ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
1.አማኑኤል አምላካችን
2.በዓለ ጌና ስቡሕ
3.ዕለተ ማርያም ድንግል
4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
📖ማቴ 1፥20
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
───────────
Channel
🧲 https://t.me/religious_books_lover
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሃያ ስምንት በዚች ዕለት የገና በዓል ሆነ ይኸውም የልደት በዓል ነው።

✍️ሰላም ለበዓለ ጌና ዘኢኮነ ንትጋ። እምልደተ ክርስቶስ ሰዓተ ጸጋ። እስመ አልጸቀት ወበጽሐት ከመ ትለዶ በሥጋ። ዮም ለተጽሕፎ ምስለ ብዙኃን እንግልጋ። ሀገረ ዳዊት ማርያም ዐሪጋ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ዕለት ደግሞ ከእንዴናው አገር ሰዎች መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ፤ እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ።
❖ ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት፤ በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና።
❖ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ፤ የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው።
❖ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለክሙ ማኅበራነ ዕደው ወአንስት። ዘኮንክሙ ስምዐ ዘበሃይማኖት። ነጺረክሙ ገሀደ ግብረ ጳውሎስ ሰማዕት። እምድኅረ መልሕዎ ዐይኖ በዓውደ መኰንን መስሕት። ከመ ኅብረ ገጹ ብሩህ ወዐይኑ ክሡት።
በዚችም ቀን የአባቶቻችን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ መታሰቢያ ነው ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለክሙ ክቡራን ዕደው። እምዕጓለ እመሕያው። አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ዘዝክርሙ ፍትው። እም ሥጋክሙ መዋቲ ከመ ሥጋ ኲሉ አበው። በሀገረ ዳዊት ዮም ተወልደ ሕያው።
📌 ታኅሣሥ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አማኑኤል አምላካችን
2.በዓለ ጌና ስቡሕ
3.ዕለተ ማርያም ድንግል
4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
✍️" የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ልጅም ትወልዳለች ፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፤ በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው"
📖ማቴ 1፥20
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።
───────────
Channel
🧲 https://t.me/religious_books_lover