ጾመ ነቢያት: አስተምህሮ፣ ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ
የነቢያት ጾም ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ሲሆን “ጾመ ነቢያት” የተባለበት ምክንያት ነቢያት ስለጾሙት ነው፡፡ “ነቢያት የጾሙት ስለምንድን ነው?” ቢሉ ለአዳም የተሰጠውን “አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፣ ከድንግል ማርያም ይወለዳል፣ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነፃ ያወጣዋል ብለው ነው፡፡ “ይህንን ጾም የትኞቹ ነቢያት ናቸው የጾ...