(የ ኢብሊስ ታሪክ ክፍል 1)
……
የታሪክ መቃኛ መነጥራችንን በርካታ ዘመናትን ወደ ኋላ መልሰን ከወደ ፍጥረተ ዓለም ጅማሮ የነበሩ ሑነቶችን ለመቃኘት ሀ ብለን ተነሳን።የዓለማቱ ጌታ ብቻውን ሆኖ ሳለ፣ፍጥረታትን ማስገኘት ሲሻ በ ኩንያ(ሁን በማለት)ትዕዛዝ የፍጥረታትን መጀመሪያ ኑር አድርጎ ከዚያም ሲልሲላውን በጠበቀ መልኩ የተለያዩ ፍጥረታትን አስገኘ።(ቀድሞ የተፈጠረው ውሃ ነው የሚል እሳቦት ያላቸው ዑለሞችም እንዳሉ እናስታውሳለን) ቢሆንም ከሃሳባችን ጋር ለመጓዝ ይኼ የ ቂያስ ልዩነትን መጥቀሱ ለሃሳብ ተቃርኖዎች ያለንን ክብር ለመጠቆም እንጂ ሌላ አይደለም።እናም ቅኝታችንን እንዲህ በረጋ እና በሰከነ የጉብኝት መንገድ እንቀጥላለን።
ከቀዳማይ ግኝቶች ውስጥም ሰማይና ምድር ይገኙበታል።ሌሎች መውጁዳቶችንም እነ አርሽ፣ ኩርስይ፣ለውህ፣ቀለም፣ውሃ፣ጀነት፣ጀሐነም፣እንዲሁም ሌሎችን በርካታ ነገሮችን ረበል ዓለሚን ፈጥረ። ከዚያም ሰማይና ምድርን አሁን ባለበት ሑናቴ ካነባበረ በኋላ የምድር የመጀመሪያ ነዋሪያንን አስገኝቷል።እነሱም ከሰው ልጅ መፈጠር ብዙ ሺህ አመታትን ቀድመው በምድር የኖሩት ጂኒዎች ናቸው።
የሰው ልጅ ኹሉ አባት የሆነው አባታችን አደም(ዐሰ) ተፈጥሮ ሰዋዊ አካልን ይዞ ሩህ ተዘርቶበት ወደ ጀነት ከመግባቱ ከበርካታ ዓመታት በፊት፣ምድር ላይ የነበሩ ፍጥረታትን ስንዳስስ አንድን ታሪክ እናገኛለን።«የ ሱመያዕ ልጆች»ታሪክ። አባት ሱመያዕ ማለት የመጀመሪያው ጂኒ እና የጂኒዎችም ሁሉ አባት ሲሆን፣በምድር ላይ ተፈጥሮ መኖር ሲጀምር ከ አሏህ ጋር የተጋባው ቃል ኪዳን አብሮ ይወሳል።
የጂኒዎች አባት "ሱመያዕ" በወቅቱ ምድር ላይ የነዋሪነት ፍቃድ ሲሰጠው እጅግ በጣም ሷሊህ እና የአሏህ ህገ ደንብ በስርዓቱ የሚያከብር እና የሚተገብር ነበር።
………
(የጂኖች አፈጣጠር ጅማሮ)
አሏህ ምድርን በመልኳ ዘርግቶ ለረጅም ዓመታት ምንም ዓይነት ፍጥረታት ሳይኖሩባት በዝምታ እንድትቆይ ካደረገ በኋላ በመጨረሻም እሱን ሚያመልኩ ጂኒዎችን ማስገኘት ፈለገ።በቅድሚያም "ሱመያዕ"የተባለው አባታቸውን ፈጠረው።
«የፈለግኸው ምኞትን ተመኝ!»በማለትም ጠየቀው።ሱመያዕ ምኞቱን አስከትሎ ነገረ።
«1,ጌታዬ ሆዬ እኔ እና ዝርያዬን ቁጥራችንን አብዛልን!
2,እድሜያችን ወደ እርጅና ሲሔድም እንዳዲስ ወጣት አድርገን።
3,እኛ ሌሎችን ሁል፣የምናይ ስንሆን ሌሎች ግን እኛን እንዳያዩ አድርገህ ሰውረን»።አሏህም ሶስቱንም ጥያቄዎች ከተቀበለው በኋላ፣«እኔን እንጂ ሌላን ላታመልክ፣የኔን ትዕዛዝ ልትተገብር።»ብሎ ቃል ኪዳን አስገባው።አባት ሱመያዕም የአሏህን ትዕዛዝ ተቀብሎ ቃለ መሃላውን ፈፅሞ ምድር ላይ አሏህን እየተገዛ መኖር ጀመረ።በየጊዜውም ዝርያዎቹ ቁጥራቸው እየጨመረ፣ግዛታቸው እያሰፉ፣አባት ሱመያዕም ምድሪቱን እያስተዳደረ፣በሰላምና በምቾት መኖራቸውን ቀጠሉ።
በመሰረታዊነት እዚህ ጋር የምናሰምርበት ነገር ቢኖር 1ኛ የሰው ልጅ ምድር ላይ ከመኖሩ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት የምድር ነዋሪያን ጂኒዎች እንደነበሩ ልብ ይሏል።እነዚህ ጂኒዎች የአሏህን የጌትነት ክብር ያወቁና፣አሏህን ብቻ ለመገዛት ቃልኪዳን የተጋቡ ሷሊህ ባሮች የነበሩ ሲሆን፣በሒደት ሁኔታቸው ወዴት እንዳመራ አብረን እንቃኛለን። ስለዚህ ውድ አንባቢያን! በተረጋጋ መንፈስ ሆናችሁ፣ታሪካቸውን አብረን እንቃኝ ዘንድ ተከተሉኝ ስል ባክብሮት እጋብዛለሁ።
…………………
የአባት " ሱመያዕ" ዝሪያቹ እየበዙና እየተበራከቱ፣አሏህም በነሱ ላይ ያኖረውን ገፀ በረከት በማክበር እና እሱን ብቻ በማምለክ መኖር ቀጥለዋል።በወቅቱ የራሳቸው የሆነ ምድራዊ መጠቃቀሚያዎች የነበራቸው ሲሆን በተለያዩ አዝዕርቶችና ምግቦች በመጠቀም የተንበሻበሸ የበረከት ዘመናትን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ጥቁምታን ይሰጣሉ።በዚህም ሁኔታ ብዙ ሰላማዊ፣የተደድላ እና አሏህን የማምለክ ዓመታት ታለፉ።
…………
እነሆ በረከቶች መንበሻበሽ እና ተለምዶ ሲመጣ ግን ዘመን እየተጓዘ ሲሄድ እንዚያ ሷሊህ የነበሩ ጂኒዎች ቀስ በቀስ አሏህን ማመፅ፣ቃልኪዳናቸውን መጣስ እና ትዕዛዙን መቃረን ጀመሩ።ይሄ እርምጃቸውም ቀስ በቀስ እየባሰ ወደ ፍፁም አመፀኛነት አመራቸው።ከዚህም አልፎ የተጠላውን ደም የመፋሰስ ወንጀል ተዳፍረው እርስ በርሳቸው መገዳደል ጀመሩ።
…
አሁን በምድሪቱ ህገ አምላኮዎች ተረስተዋል።አሏህም የነሱን ሁናቴ ሲከታተል ቆይቶ፣በነሱ ላይ የነበረውን ተስፋ እና ትዕግስት ጨረሰ።ስለሆነም እኝህ አማፂያን ከምድረ ገፅ እንዲጠፉ አዘዘ።እርምጃወን ለመውሰድም የመላዒኮች ጁንድ፣ ከሚነሏህ የሆነ የሰላ ሰይፋቸውን ታጥቀው፣ወደ ምድር ዘልቁ።
ጂኒዎችን እንዳልነበሩ አድርገውን አወደሟቸው።ጥቂት ጂኒዎች ግን የመላዕክትን ጦር መቋቋም የማይቻል መሆኑን ሲገነዘቡ፣ ወደ ተለያዪ የባህር ዳርቻዎች፣ደሴቶች፣ጠረፍ ወዳሉ ገደላገደሎች እና ተራሮች እግሬ አውጪኚ ብለው ፈረጠጡ።(እሰይ😄)
የመላዒካው ብርጌድ የጦር አውድማውን በማጣራት ላይ ሳለ፣መሐል ሜዳ ላይ ድንገት አንድ የ 4 ዓመት ታዳጊ ጂኒንን ያገኛሉ።እሱም ተይዞ በቁጥጥር ስር ዋለ።ከዚያም የአሏህ ትዕዛዝ መጣና ይሄ ታዳጊ ጂኒ በመላዕክት ተይዞ ወደ ሰማይ ተወሰደ።ይህ የ 4ዓመቱ ጂኑ ኢብሊስ በመባል ይታወቃል።
ክፍል 2 ይቀጥላል…