አንድ መምህር ለተማሪዎቹ ለእያንዳንዳቸው ፊኛ እንዲነፉ ይሰጣቸዋል። ከዚያም እያንዳንዳቸው ስማቸውን ፊኛው ላይ ጽፈው አዳራሽ ውስጥ እንዲወረውሩት ይነግራቸዋል። ከዚያም ሁሉም ተማሪዎች ይህንን ካደረጉ በኋላ እያንዳንዳቸው ስማቸው የተጻፈበትን ፊኛ ፈልገው እንዲያገኙ 5 ደቂቃ ይሰጣቸዋል። በርካታ ስለነበሩ ምንም ያህል ቢደክሙ የእየራሳቸውን ፊኛ ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።
በመቀጠልም መምህሩ ተማሪዎቹን እያንዳንዱ ተማሪ መጀመሪያ የሚያገኘውን ፊኛ ስሙ ለተጻፈበት ተማሪ ይሰጠው በማለት ያዛችዋል። በ 5 ደቂቃ ውስጥም ሁሉም ተማሪዎች የየእራሳቸው ስም የተጻፈባቸውን ፊኛዎች ማግኘት ቻሉ።
ከዚያም መምህሩ "አያችሁ? እነዚህን ፊኛዎች ልክ እንደ ደስታ ቁጠሯቸው። እያንዳንዳችን የእየራሳችንን ደስታ ብቻ የምንፈልግ ከሆነ፤ የፈለግነውን ደስታ ሳናገኝ እንቀራለን፤ ነገር ግን ስለሌሎች ደስታም የምንጨነቅ ከሆነ እኛም የፈለግነውን ደስታ እናገኛለን።" በማለት ነገራቸው።
@tbebawitarik