✨✨
ኻሊድ
ክፍል ሰባት 7
የመጨረሻው ክፍል
✍ቢንት ሀሰን
ነዒማ ያለወትሮዋ ለይል ሰግዳ ስለትዳራቸው ዱዓ ማድረግን ተያያዘችው። ብዙ ግዜ ስራ በጊዜ ለመግባት ስትል ለሊቷን በእንቅልፍ ታሳልፍ የነበረችው ነዒማ ቁርዓን እየቀራች ጎህ ቀደደ! ቁርሷን ተመግባ ወደስራ ልትሄድ ስትል ድንገት ስልኳ ጠራ! በዚህ ሰዓት ማንም ደውሎላት አያውቅም : በድንጋጤ ሳለች አነሳችው!
"አሰላሙ አለይኪ ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ " ከዛኛው ወገን የተሰማ ተስረቅራቂ የኻሊድ ድምፅ ነበር
"ወአለይከ ሰላም ኻሊዴ ሰላም አደርክ " አለችው ከደቂቃዎች በፊት የነበረውን ድንጋጤ በፈገግታ ተክታ
" አልሀምዱሊላህ ደህና አደርኩ ሩሄ:
ዛሬ ምሳ ልጋብዝሽ ልልሽ ነበር መደወሌ" አላት በእርጋታ
"ደስ ይለኛል በዛው ስለ ሰርጉ እንወያያለን! አይመስልህም? "
"መርሀባ አስሊ ጠብቅሻለው ከዙህር በኋላ "
" እሺ በቃ ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ"
"ወአለይከ ሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ " አላት ውስጥውስጡን እየናፈቀችው
ከወራት በኋላ
ዛሬ ያለወትሮው የነነዒማ ሰፈር ግርግር በዝቶበታል :አላፊ አግዳሚው ሁሉ ጉድ ያለለት ትልቅ ሰርግ ተደግሶ ሙሽራው እየተጠበቀ ነው!
ነዒማ በሰርጓ ቀን እጅግ ተውባ ና በሴቶች ተከባ እየተዜመላት ነው
👏 ሙሽራው ታደለ ሀምድ ያቅርብ ለአላህ
ነዒማን አገኘ በሀያእ ተኩላ
የሙሽራው እናት ተደሰቺ ባንዴ
ይቺን ምርጥ ሙሽራ ሲያገባት ኻሊዴ👏
ሙሽራው መምጣቱን ሲሰሙ ደሞ ለሁለቱም እያደሉ በእልልታ ቀጠሉት
👏 የሙሽሪት እናት ወጣ በይ ከጓዳ
ንጉሱ ኮመጣ የልጅሽ ባለዳ
እጅሽን ከፍ አርገሽ አቅርቢ ሀምዳ
👏 ከዚ እስከ መስጂዱ ወርቅ ይነጠፍበት
ነዒማ ና ኻሊድ ይመላለሱበት
ነዒማም ቤተሰቦቿን ተሰናብታ የሙሽሮች መኪና ውስጥ ስትገባ ነበር ኻሊድ ግጥም አርጎ የሳማት ሁለቱም ፈገግ አሉና እኩል አፈቅርሀለው / አፈቅርሻለው ተባባሉ
አሁንም የሰፈሩ ሰዎችና አጃቢዎች እልልታውን እንዳቀለጡት ነው
👏 በነቢዬ ሱና ተጋቡ ጥንዶቹ
ተራው የናንተ ነው አግቡ ሚዜዎቹ
👏 የዛሬ አመትም ስንመጣ ቤታችሁ
ሀቂቃ ይሆናል ሙሽሮች ወልዳቹ
እኔም አልኳቹ
እንደነ ነዒማ : እንደነ ኻሊድ
በሀላሉ አግቡ ትዳርኮ አይከብድ
በሩቁ ትዳርን ፈርቶ ከመቀመጥ
መጀመሪያ ገብቶ በልጆች መቀወጥ!
ተፈፀመ
ለሀሳብ አስተያየት:-
@tbebawitarik_bot ላይ አድርሱን!!