"ንጋት"
ኒብራስ × ያስ ሁዳ
.
ክፍል3
.
> እናቴ በትዉስታ ረጂም አመታትን የኋሊት ሸመጠጠች...እኔም በየመሃሉ ስለአባቴ ስታነሳ ልቤ ትር እያለ አብሬያት በትዝታ ጋሪ ተሳፍሬያለሁ..
> ዓለሜ ከሄደችበት የትዝታ መንደር በጀበናዉ ዉስጥ እየተንተከተከ ካልወጣሁ እያለ የሚታገለዉ የቡና ድምፅ ቀሰቀሳት..> እሷ ይህን ትበል እንጂ እኔ ለማዳመጥ ካለኝ ጉጉት በላይ እሷ በትዝታ እየሰጠመች ማዉራት እንደጓጓች አዉቄባታለሁ...ምክንያቱም የምታወራዉ ስለ ይመር ነዋ...የልጇ-አባትየልጅነት ባሏ!!
>
>
>
>
>
> እናቴ ፊቶች ላይ የናፍቆት እና የፍቅር ደሞች ይዘዋወራሉ..በአባቴ ፍቅር ዛሬም ድረስ ተስፋ አልቆረጠችም፣ ሊመጣ ቃል እንደገባ እንግዳ ትጠብቀዋለች።
>
>
>
>
>
>
>
>
>
> ሲሰሙት ቢያድሩ የማይጠገብ የሳቅ ዜማ-የእናቴ!!
*
የመማሪያ ክላስ ዉስጥ ፊቴን ወደበሩ አዙሬ ብቻዬን ተቀምጫለሁ። ምን እንደነካኝ አላዉቅም ዛሬ በጠዋት ነዉ የተገኘሁት። ክላሱ በጣም ይበርዳል...እንደኔ በጠዋት የመጡ ተማሪዎች ብርዱን ሽሽት ከክላሱ ፊት ለፊት ተቀምጠዉ ፀሃይ ይሞቃሉ። ፀሀይ የሚሞቁትን ተማሪዎች እየተመለከትኩ ሳለሁ በፊት ለፊቴ ጥቁር ጅልባብ የለበሰች ሴት አለፈች። ወዲያዉ በአዕምሮዬ የመጣችዉ ሂክመት ነበረች.. ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ባለ ጥቁር ጅልባቧን ሴት ተከተልኳት። ሂክመት ከሆነች እንደምንም አዋርቻት ለመመለስ ነበር የተከተልኳት። በድንገት ከኋላ "ኸዉሊ" የሚል ድምፅ ተሰማ...ያቺ ጅልባብ ለባሽ ዞረች - ሂክመት አልነበረችም። ይህን ያክል ስለ ሂክመት ማሰቤና የተፈጠረዉ አጋጣሚ እያሳቀኝ ወደ ክላስ ተመለስኩ። ክላስ ተቀምጬ ሳለሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ...እናቴ ለአባቴ የመጀመሪያ ቀን ሲገናኙ ያሳየችዉ ፊት እና ሂክመት መጀመሪያ ቀን ስንተያይ ያሳየችኝ ፊት...የእማዬን በእንጥልጥል የቆመ ታሪክ ለመጨረስ ጓጓሁ፤ የእኔን እና የሂክመትን ጉዳይ ይወስን ይመስል።
> አቤል ነበር ጓደኛዬ።
>
>
>
>
>
> አቤል እንዲህ ነዉ..ሆዱን የሚሞላለት ካገኘ እናቱንም ቢሆን ይክዳል-እኔ አይደለሁም ራሱ ነዉ ያለዉ። ለመብላት ያለዉን ጉጉት ስላየሁ ተስማምቼ ተያይዘን ሄድን። ቦታዉ ላይ ስንደርስ ሜሮን እና ሀያት ተቀምጠዋል። ሜሮን ማለት ሰሞኑን ወድጄሃለሁ እያለች ደጅ የምትጠና ሴት ናት። መምጣታችንን ሲያዩ በፈገግታ ተቀበሉን። በየተራ ሰላም ካልናቸዉ በኋላ ሜሮን ካጠገቤ መጥታ ተቀመጠች። እጇን በትከሻዬ ላይ አስቀምጣ ፀጉሬን ትደባብሰኝ ጀመር።
>
> ወደ አንገቴ ተጠግታ ለመሳም ስትሞክር አንድ ሴት ከካፌዉ ስትወጣ ተመለከትኩ_ሂክመት ነበረች። ሜሮንን አመናጭቄያት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ..ተሰምቶኝ የማያዉቅ ድንጋጤ ዋጠኝ። "ሂክመት አይታኝ ይሆን?" እያልኩ ራሴን መጠየቅ ተያያዝኩ። አቤል ከተቀመጠበት እየተነሳ..
>
>
>
> እየተጣደፍኩ ከካፌዉ ወጣሁ። ከመዉጣቴ የሂክመትን ዳና ብፈልግም አጣኋት-የለችም። የተዘበራረቀ ሀሳብ ዉስጥ ሆኜ ወደ ግቢ ሄድኩ። ክላስ ስደርስ መምህር ገብቶ lecture እየሰጠ ስለነበር አርፍደሃል ብሎ መግባት ከለከለኝ። ወዲያዉ ወደ ግቢዉ Lounge አመራሁ። ዉስጥ ማንም የለም ከአስተናጋጆቹ በስተቀር...ሻይ አዝዤ ተቀመጥኩ።