👏 #አልፉ_ሶላት ግጥም 🙏👎
ገለታ ይድረሰው ሩሁን ላነገሰው #ነቢይ
ከተውሂድ ጀረት ላይ ለኛ እንዳፈሰሰው #ነቢይ
ከውኑን ለርሶ ላንቱ በልፍኙ ደገሰው #ነቢይ
ኧሀ አልፎ አዝልቆ ለኛው አወረሰው #ነቢይ
በራህመቱ መርጊያ ከውናቱ የረጋው #ነቢይ
በነቢ ስፍራ ነው የራህመት መፍለቂያው #ነቢይ
ለርሶ የሾማቸው ሰጥቷቸው ከአደጋው #ነቢይ
በስሙ ሸክረው ተገኙ ከሊቃው #ነቢይ
አሃ ጨለማውን ራስ ሽበት እስኪያነጋው #ነቢይ
ጉልበታቸው አልቆ መሬት እስኪያድኸው #ነቢይ
ፈርጣማው ክንዳቸው ከአለት የጠናው #ነቢይ
የእርጅና ጉጠት እስኪያሸበሽበው #ነቢይ
አሃ የኡምራቸውን ጠጅ ለህዱ እስኪጠጣው #ነቢይ
በሁቡህ አልቅሰው እንባቸውን ጨርሰው #ነቢይ
እናቱን እንዳጣ ህፃን ተፈቅፍቀው #ነቢይ
ሀዘን ፊታቸውን ዳምኖ እስኪያጠቁረው #ነቢይ
በትካዜ መርከብ እንዳለ ተጭነው #ነቢይ
ቀናት በነሱ ላይ ያልፋሉ ተቆጥረው #ነቢይ
አሃ ደግሞ ሲያሰደሳቸው ደርሶ ጀማሉሁ ያሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
ሆሆሆ በውበቱ ድርማ ላይ ውስጡን ታንጦ
ሁሉንም በለጠው መጨረሻ መጥቶ
ሽርክን ገለባብጦ በተውሂድ አንጦ
አለሙን አበራው በኑር እየቀባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
መፈጋፈግንጂ ማን ሊችለው ነእጁን
ሲፈዎትን በማስፈር የርሶን ዛት ሲፈቱን
ማን በነገረልኝ ሆዴ መባባቱን
እጅ ማሰጠቱን የሙስጦፋ ሀይባ ያሰይድ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
👏👏👏🙏👏👏👏👏👏👏👏👏
ገና ፊትም ሆነው በናትዎ ማፀን
ጫልዩ ጌታችሁ መድሁን ለማጠንጠን
ስንቱን ሞት አነቁት ሶለዋት በማጠን
ለኛውም ይሰጠን የነሱ መሀባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
የርሶ ስም አይደል ወይ ሲዲቅን ያላቀው
ኡመሩል ፋሩቅን በከሽፍ ያደመቀው
ኡስማንን የሀያእ ዝናን ያስታጠቀው
አልይን ያሳደገው ሂዳያ እያጠባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
የቡሰይሪን ፈሊጅ ሲሩን ያፈለሰው
የቡራኢን ሀዘን ጠራርጎ ያጠፋው
የዘቡሯ ልጇን ልሳን ያቀመሰው
አንዩን ዳንዩን መቃም ያደረሰው
አብደርይን በኢልም ጀህልን ያስገረፈው
ሸይኽ አሊ ጎንደርን ሞት ያስቀሰቀሰው
ስንቱን አነገሰው ከኸልዋ እያስገባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
በልቼ እየጠጣሁ ይርብ ይጠማኛል
መድሀኒት ወስጀም አጥብቆ ያመኛል
መከዳ ታቅፌ እንቅልፍ ይርቀኛል
መነመነ ጅስሜ ናፍቆት እየሰባ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
ጀሊሉ የርሶን ስም በክብር ሲያኖጋው
በተጠራ ቁጥር ባንድነት ያስጠራው
እርሱ ነው አማላጅ እርሱ ነው ባላልጋው
ከውኑን ያረጋጋው መስመር እያስገባ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
አልፉ ሶላት የፍቅርሁን ንጋት
የኔ ጌታ በላዩ ላይ ዘልቆ
አልፉ ሶላት የሰራ አካሉቱን
የኔ ጌታ ያልቃል እንባ ፈልቆ
አልፉ ሶላት ከውስጡ እየገባ
የኔ ጌታ ትንፋሹን ሰንጥቆ
አልፉ ሶላት ያስወተውተዋል
የኔ ጌታ ያን ጨረቃ ናፍቆ
የኔ ነቢ ይወርቃል ተንጋሎ
ወለላየ አረፋውን ደፍቆ
ጌታየዋ ነፍሱን ያሰረተዋል
የኔ ጌታ ልቡ ተሰንጥቆ
አልፉ ሶላት ይዞ እያናፈለው
አልፉ ሶላት ውስጡን አሟሙቆ
አልፉ ሶላቱ ጀንበር ከመድና
የኔ ጌታ እየታየው ዘልቆ ያሰይድ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
አልፉ ሶላት አንቺ የኸይር ንፋስ
የኔ ጌታ ገልጠሽ የልቤን
አልፉ ሶላት ብለሽ ንገሪልኝ
ወለላየ ለዛ መኮነን
አሃ ዛሬስ አዳረሰው
አልፉ ሶላት የሰራ አካሉን
የኔ ጌታ ጉበቱ ነደደ
አልፉ ሶላት አፈላው ደሙን
የኔ ጌታ ስጋውን ጨርሶ
አልፉ ሶላት አወራው ጅስሙን
የኔ ጌታ አበደ ጨርሶ
የኔ ነቢ ወሰደው ልቡን
አልፉ ሶላት አካላቱ አለቀ
የኔ ጌታ ተፍቆ እንደ አንጀት
የኔ ጌታ ስጋውን አፍግቶ
የኔ ጌታ ይሄዳል ባጥንት
አልፉ ሶላት ጉበቱ ሁሉ ሳስቶ
የኔ ነቢ እንደ ወረቀት
የኔ ጌታ ሲቆም ደህን መሳይ
አልፉ ሶላት ልብስ ሸፍኖት
የኔ ጌታ ነውጂ እስከቀኑ
አልፉ ሶላት አልተረፈም ከሞት
ወለላየ አድርጉልኝ እዝነት
አልፉ ሶላት የብርሃን እልፍኝ
የኔ ጌታ አኳሀሗኔን ሁላ
የኔ ጌታ እንድትነግሪልኝ
አልፉ ሶላት አካላቴ አለቀ
አልፉ ሶላት ጉልበቴም ከዳኝ
የኔ ጌታ አጥንቴም አለቀ
የኔ ጌታ ደሜ አቃጠለኝ
አልፉ ሶላት ቀኑም ተራዘመ
ጌታየዋ እኔንም ከዳኝ ሰይዲ ያረሱለሏህ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌
ሌሎችንም የነሽዳና መንዙማ ግጥሞች ለማገኘት👇👇
@Yehadra_gtmoch