😍😍😍😍😍
ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ;
❤የመዲናውን ; ባየነው አይኑን
በኑር አረንጓዴ ; የተኳለውን
❤የውነት ከሆነ እኔ ; አንቱን መውደዴ
ሀበሻ ምድር ላይ ; አትፈርስም ጀሰዴ
❤አልሀምዱ ሊላሂ ; ልንዘክራችን
ያየኑር ጡሩራ ; የጀነት ቁልፉን
የድል ሁላ ቤቱን ; የጥሜት ሰይፉን
ካፋፍ ላይ አወጣው ; ሰው አህባቦቹን
ያለ እርሱ ወገን ; ሌላ የለኝ እኔ
❤ጌታየዋ ሸውቁ ; ሩሄን ቢያቃጥላት
ወንጀሌ ተሀድራው ; ደሞ ቢነጥላት
ዪቺን አበጀሁኝ ; እንድንሞጥላት
ከዚያ ባንቱ ሀድራ ; አላህ ቢቀጥላት
አንቱን ካዬች ወዲያ ; ብትሞትም እንዳሻት
❤ወርውሮ የመታኝ ; በሙሀባው ሎሎ
ልቤን የረገጠው ; ሌላ አካሌን ዘሎ
ሀያራ ሱካራ ; ያረገኝ አግሎ
ማንም አረታኝም ; እሱን አስመስሎ
ዉቡን ሁላ አዝሎ ; ወደቁለት እኔ
❤ሷሂቡል ኢህሳኒ ; ሀቢቡ ረህማኒ
ነሩ እሚንቧለቀው ; ፊኩሊ ዘማኒ
የፊቱን ብልጭታ ; ቢያሳየን መናኔ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; መስከረምም ሰኔ
ቅረቡኝ ወደ ኔ ; እንዳልወድቅ ከኋላ
❤የሷሊሆች ቀለብ ; የደጎች መደድ
በስሙ ይነሳል ; ሙላውም ሀሲድ j
ባንቱ ነው ሚጠራው ; የኔም ጉዳጉድ
ላንቱ ስወዘወዝ ; ሌላው ቢለኝ እብድ
ቀስዴ ነው በለህድ ; አንቱን ማግኜት እኔ
❤ነቢ ለኔ ብለው ; የዋሉት ውለታ
መች ተከፍሎ ያልቃል ; እስከ ቂያማ ለታ
እኔ ልራብሎ ; እኔ ልንገላታ
እኔው ድንጋይ ልሰር ; ሆኜ ባንቱ ቦታ
እኔው ላልቅስሎ ; ብዬ ዋኔ ዋኔ
ኩራቴዋ ነቢ
ደስታዬ ደስታዬ
❤የትልቅ ሰው እቃ ; የተቀበለ ሰው
ምንድን ማረፊያ አለው ; አፈር እስኪያለብሰው
ተማር ይጣፍጣል ; መድሁን ለቀመሰው
ሙሂቦ ቢጠጣው ; የማይጨረሰው
ጫማዎን ልላሰው ; ይከፈል ሀዘኔ
ወረቴዋ ነቢ
ወዳጄ ወዳጄ
❤ልፈልግ ዘመድ ; መርጬ ወንድ ወንድ
በሀድራ እሚጣድ ; በፍቅሮ እሚርድ
በነቢ ሙሀባ ; እምባ የሚያወርድ
በፍቅሮ ይለካል ; ሴትም ሆነ ወንድ
የሌለው መውደድ ; ስሙን አላቅ እኔ
❤ደርቦ የኖረው ; የሀቁን ልባስ
ኸልቆ ያደመቀው ; ጌታችን ቅዱስ
በርሱ የሚነፍሰው ; የተውሂድ ንፋስ
ሹመተ ገናና ; የጦይባው አሩስ
በሙሀባው ልብስ ; አልብሱኝ ያዘይኔ
ወለላው ነብዬ
❤ሙሂቡ በሸውቁ ; በሀሳብ ገስግሶ
ሌላውን እረስቶ ; ወስጡ ተረስርሶ
የዱንያ ጉልላት ; ከልቡ ላይ ፈርሶ
ያንቱ ሙሀባ ሟች ; እንባው አልቆ ፈሶ
ይታያል ታድሶ ; በስሙህ ብያኔ
ደስታዬዋ ነቢ;
ወረቴዋ ነቢ;
❤ዳኢም ሚጋረፈው ; የሁብሁ ወላፈን
በኛም ላይ ዘነቡ ; ምነው በሸወቀን
ወዳጆቹ ጋራ ; የፊቱ ወጋገን
ጮራው ያልተለዬው ; በሌሊትም በቀን
ያኔ እኛም ተመርጠን ; ባሳመሩን ዘይኔ
❤እርግጥ ነው ባንቱ ; ላይ አለ የኑር ነገር
ለሙሂቦች እንጂ ; ለኔ ማይነገር
በርሱ ተቋድሰው ነው ; ያገኙት መከበር
በዱንያ ላይ ሁኖ ; የኔ መደናበር
በወንጀል ወታደር ; በዛ መታደኔ
ረውዷው ነብዬ
❤በመኳያው ኩሎ ; አህሉ ቢያደርገኝ
ፊት እንዳጠጣቸው ; ለኔም ቢግተኝ
በውዱ ባህር ላይ ; ጠምቆ ቢያስዋኜኝ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; ሌላም አልመኝ
ጠረኑ ይድረሰኝ ; ኸፈላዬ ይንደድ
❤ከደጁ ላይ ቁሟል ; የውዱህ እንግዳ
ባትችልም መዴ ; ባይጠናላት ክንዷ
ነው ከወዳጆቹ ; ከአባቶቿ ለምዳ
ፈይዱን የገበዩት ; በጧት በማለዳ
ካገኙት ሰዐዳ ; መቅመስ በመውደዴ
❤ቀሀዋ አይል ጫካ ; ባንቱ ተመንጥሮ
እንደሌላው ሳይሆን ; ዳኢም በንጉርጉሮ
እንዳንቱ ማን አለ ; የሚያሳምር ኑሮ
ነጃ አውጡኝ ሰይዲ ; ከጥሜት ማሰሮ
የሀሲድ ቋጠሮ ; ይበጣጠስ ከኔ
❤ሰይዲ አደራሁን ; ጣሉብኝ ጥላሁን
ቢሆን መሀያሁን ; አለዛ ጦይፍሁን
ውዴታሁ እሚባል ; አጣብቀው ሁዳሁን
ደህና መስያለሁ ; ታምሚያለሁ አሁን
ና በሉኝ ፊትሁን ; እንቅልፉን ይፍጅ አይኔ
❤ለጂሀድ ሲነሱ ; ሁኜ ከጎንሁ
ካንቱ ጋር ባበርኩኝ ; እንደ አስሀባሁ
እንደ አቡዱ ጃና ; ሁኜ ከፊትሁ
ጥቃት መመለሻ ; ሁኜ እንደ ጋሻሁ
ይፍሰስሎት ደሜ ; እንደ አባይ ይውረድ
❤ለመውሊዱ ድንኳን ; ልሁንለት ማገር
ኸልቁ ተመችቶት ; አንቱን እንዲዘክር
የጎጆዬ አጠና ; ተሰብሮ ይማገር
ልብሴም መሬት ይውደቅ ;ይነጠፍ ለመውሊድ
አህባቡ በሶፋ ; እንዲሎት አህመዴ
❤ለመውሊዱ አጪጄ ; እህሉን ኡጓሮ
በጀርባዬ አስሬ ; ውሀ በማሰሮ
ለአህባቦቹ ሂድሚያ ; እግሬ ቁሞ አድሮ
ከቀልቤ ላይ ይርገፍ ; ደሜ ተመንጥሮ
ሩሄ ጅስሜ አምሮ ; በአይኔ ልዮት ዘይኔ
❤አሰላም አለይኩም ; አህመድ ብልሀቴ
በዱንያ ዙረት ላይ ; የዘለው ጉልበቴ
መውሊድ ያድሰዋል ; ሙላወን ጉድለቴ
አመቱን ስጠብቅ ; በዛ መጎዳቴ
ይሙላ ፍላጎቴ ; ልበል ጉድ ጉድ
❤የቀረበ ጊዜ ; ረቢዒል አወል
ሙሀባን ያዘለ ; ንፋስ ይነፍሳል
ሙዕሚን ቀልበ ; ጥሩ ያኔ ይደሳል
ደግሞ ሸይጧን ጭፍራው ; ደስታው ይነሳል
ብሎ ያለቅሳል ; ዋ ጉዴ ዋ ጉዴ
ወለላው ነብዬ;
❤ሩሄ ዝቅ ብሎ ; ወድቆ እንደ መሬት
አስሬ ተሺጬ ; እኔ ለባርነት
በማወጣው ዋጋ ; መውሊዱ ይውጣበት
ተምኪንን እሻለሁ ; ለሩሄ ሽልማት
ጀማልሁን ማየት ; ይሁን እጣ የኔ
❤መውሊዱን ከምንቅ ; አፈሩ ይብላኝ
ጉድጓድ ትግባ ነፍሴ ; ምቾት ይራቀኝ
መቆም እስኪያቅተኝ ; ጉልበቴ ይክዳኝ
ከአንቱ ሌላ ደስታ ; እኔ ምን አለኝ
ዘይኔ ና በሉኝ ; ተቋደስ ከማድ
❤የመውሊዶን ጠላት ; ልምታው እንደ ድቢ
እኔ እንድወዛወዝ ; እርሱን አንገብግቤ
ቢሰራ ነው እንጂ ; ቀልቡ እንደ ሹርቤ
በወንጀል ቢጠለፍ ; ሩሁ እንደጋቢ
የኸይራቱን ግቢ ; የመጣው ሊያነድ
❤ቢወርድ ለኢሳ ; ከሰማዩ ማድ
ጌታን ለማመስገን ; አደረጉት ኢድ
ምግብም ከተገባው ; ይሄን ያህል ሀምድ
እንዴት ይዘነጋል ; ያንቱ መወለድ
እናከብረዋለን ; እስክንገባ ለህድ
❤ሶላትና ሰላም ; በሞላው ቁጥር
ከሰማይ ምድር ; ባረከው ስፍር
ከሳር ቅጠል በልጠው ; ካሸዋ ክምር
በኸልቁ ሁላ እድሜ ; ቆጥሮ ዘር ማንዘር
አውርደው ቃዲር ; ረህመቱን በዘይኔ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😍ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
#Al burda jeme'a
👏👏👏👏👏👏👏👏
@yehadra_gtmoch
👏👏👏👏👏👏👏👏
ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ;
❤የመዲናውን ; ባየነው አይኑን
በኑር አረንጓዴ ; የተኳለውን
❤የውነት ከሆነ እኔ ; አንቱን መውደዴ
ሀበሻ ምድር ላይ ; አትፈርስም ጀሰዴ
❤አልሀምዱ ሊላሂ ; ልንዘክራችን
ያየኑር ጡሩራ ; የጀነት ቁልፉን
የድል ሁላ ቤቱን ; የጥሜት ሰይፉን
ካፋፍ ላይ አወጣው ; ሰው አህባቦቹን
ያለ እርሱ ወገን ; ሌላ የለኝ እኔ
❤ጌታየዋ ሸውቁ ; ሩሄን ቢያቃጥላት
ወንጀሌ ተሀድራው ; ደሞ ቢነጥላት
ዪቺን አበጀሁኝ ; እንድንሞጥላት
ከዚያ ባንቱ ሀድራ ; አላህ ቢቀጥላት
አንቱን ካዬች ወዲያ ; ብትሞትም እንዳሻት
❤ወርውሮ የመታኝ ; በሙሀባው ሎሎ
ልቤን የረገጠው ; ሌላ አካሌን ዘሎ
ሀያራ ሱካራ ; ያረገኝ አግሎ
ማንም አረታኝም ; እሱን አስመስሎ
ዉቡን ሁላ አዝሎ ; ወደቁለት እኔ
❤ሷሂቡል ኢህሳኒ ; ሀቢቡ ረህማኒ
ነሩ እሚንቧለቀው ; ፊኩሊ ዘማኒ
የፊቱን ብልጭታ ; ቢያሳየን መናኔ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; መስከረምም ሰኔ
ቅረቡኝ ወደ ኔ ; እንዳልወድቅ ከኋላ
❤የሷሊሆች ቀለብ ; የደጎች መደድ
በስሙ ይነሳል ; ሙላውም ሀሲድ j
ባንቱ ነው ሚጠራው ; የኔም ጉዳጉድ
ላንቱ ስወዘወዝ ; ሌላው ቢለኝ እብድ
ቀስዴ ነው በለህድ ; አንቱን ማግኜት እኔ
❤ነቢ ለኔ ብለው ; የዋሉት ውለታ
መች ተከፍሎ ያልቃል ; እስከ ቂያማ ለታ
እኔ ልራብሎ ; እኔ ልንገላታ
እኔው ድንጋይ ልሰር ; ሆኜ ባንቱ ቦታ
እኔው ላልቅስሎ ; ብዬ ዋኔ ዋኔ
ኩራቴዋ ነቢ
ደስታዬ ደስታዬ
❤የትልቅ ሰው እቃ ; የተቀበለ ሰው
ምንድን ማረፊያ አለው ; አፈር እስኪያለብሰው
ተማር ይጣፍጣል ; መድሁን ለቀመሰው
ሙሂቦ ቢጠጣው ; የማይጨረሰው
ጫማዎን ልላሰው ; ይከፈል ሀዘኔ
ወረቴዋ ነቢ
ወዳጄ ወዳጄ
❤ልፈልግ ዘመድ ; መርጬ ወንድ ወንድ
በሀድራ እሚጣድ ; በፍቅሮ እሚርድ
በነቢ ሙሀባ ; እምባ የሚያወርድ
በፍቅሮ ይለካል ; ሴትም ሆነ ወንድ
የሌለው መውደድ ; ስሙን አላቅ እኔ
❤ደርቦ የኖረው ; የሀቁን ልባስ
ኸልቆ ያደመቀው ; ጌታችን ቅዱስ
በርሱ የሚነፍሰው ; የተውሂድ ንፋስ
ሹመተ ገናና ; የጦይባው አሩስ
በሙሀባው ልብስ ; አልብሱኝ ያዘይኔ
ወለላው ነብዬ
❤ሙሂቡ በሸውቁ ; በሀሳብ ገስግሶ
ሌላውን እረስቶ ; ወስጡ ተረስርሶ
የዱንያ ጉልላት ; ከልቡ ላይ ፈርሶ
ያንቱ ሙሀባ ሟች ; እንባው አልቆ ፈሶ
ይታያል ታድሶ ; በስሙህ ብያኔ
ደስታዬዋ ነቢ;
ወረቴዋ ነቢ;
❤ዳኢም ሚጋረፈው ; የሁብሁ ወላፈን
በኛም ላይ ዘነቡ ; ምነው በሸወቀን
ወዳጆቹ ጋራ ; የፊቱ ወጋገን
ጮራው ያልተለዬው ; በሌሊትም በቀን
ያኔ እኛም ተመርጠን ; ባሳመሩን ዘይኔ
❤እርግጥ ነው ባንቱ ; ላይ አለ የኑር ነገር
ለሙሂቦች እንጂ ; ለኔ ማይነገር
በርሱ ተቋድሰው ነው ; ያገኙት መከበር
በዱንያ ላይ ሁኖ ; የኔ መደናበር
በወንጀል ወታደር ; በዛ መታደኔ
ረውዷው ነብዬ
❤በመኳያው ኩሎ ; አህሉ ቢያደርገኝ
ፊት እንዳጠጣቸው ; ለኔም ቢግተኝ
በውዱ ባህር ላይ ; ጠምቆ ቢያስዋኜኝ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; ሌላም አልመኝ
ጠረኑ ይድረሰኝ ; ኸፈላዬ ይንደድ
❤ከደጁ ላይ ቁሟል ; የውዱህ እንግዳ
ባትችልም መዴ ; ባይጠናላት ክንዷ
ነው ከወዳጆቹ ; ከአባቶቿ ለምዳ
ፈይዱን የገበዩት ; በጧት በማለዳ
ካገኙት ሰዐዳ ; መቅመስ በመውደዴ
❤ቀሀዋ አይል ጫካ ; ባንቱ ተመንጥሮ
እንደሌላው ሳይሆን ; ዳኢም በንጉርጉሮ
እንዳንቱ ማን አለ ; የሚያሳምር ኑሮ
ነጃ አውጡኝ ሰይዲ ; ከጥሜት ማሰሮ
የሀሲድ ቋጠሮ ; ይበጣጠስ ከኔ
❤ሰይዲ አደራሁን ; ጣሉብኝ ጥላሁን
ቢሆን መሀያሁን ; አለዛ ጦይፍሁን
ውዴታሁ እሚባል ; አጣብቀው ሁዳሁን
ደህና መስያለሁ ; ታምሚያለሁ አሁን
ና በሉኝ ፊትሁን ; እንቅልፉን ይፍጅ አይኔ
❤ለጂሀድ ሲነሱ ; ሁኜ ከጎንሁ
ካንቱ ጋር ባበርኩኝ ; እንደ አስሀባሁ
እንደ አቡዱ ጃና ; ሁኜ ከፊትሁ
ጥቃት መመለሻ ; ሁኜ እንደ ጋሻሁ
ይፍሰስሎት ደሜ ; እንደ አባይ ይውረድ
❤ለመውሊዱ ድንኳን ; ልሁንለት ማገር
ኸልቁ ተመችቶት ; አንቱን እንዲዘክር
የጎጆዬ አጠና ; ተሰብሮ ይማገር
ልብሴም መሬት ይውደቅ ;ይነጠፍ ለመውሊድ
አህባቡ በሶፋ ; እንዲሎት አህመዴ
❤ለመውሊዱ አጪጄ ; እህሉን ኡጓሮ
በጀርባዬ አስሬ ; ውሀ በማሰሮ
ለአህባቦቹ ሂድሚያ ; እግሬ ቁሞ አድሮ
ከቀልቤ ላይ ይርገፍ ; ደሜ ተመንጥሮ
ሩሄ ጅስሜ አምሮ ; በአይኔ ልዮት ዘይኔ
❤አሰላም አለይኩም ; አህመድ ብልሀቴ
በዱንያ ዙረት ላይ ; የዘለው ጉልበቴ
መውሊድ ያድሰዋል ; ሙላወን ጉድለቴ
አመቱን ስጠብቅ ; በዛ መጎዳቴ
ይሙላ ፍላጎቴ ; ልበል ጉድ ጉድ
❤የቀረበ ጊዜ ; ረቢዒል አወል
ሙሀባን ያዘለ ; ንፋስ ይነፍሳል
ሙዕሚን ቀልበ ; ጥሩ ያኔ ይደሳል
ደግሞ ሸይጧን ጭፍራው ; ደስታው ይነሳል
ብሎ ያለቅሳል ; ዋ ጉዴ ዋ ጉዴ
ወለላው ነብዬ;
❤ሩሄ ዝቅ ብሎ ; ወድቆ እንደ መሬት
አስሬ ተሺጬ ; እኔ ለባርነት
በማወጣው ዋጋ ; መውሊዱ ይውጣበት
ተምኪንን እሻለሁ ; ለሩሄ ሽልማት
ጀማልሁን ማየት ; ይሁን እጣ የኔ
❤መውሊዱን ከምንቅ ; አፈሩ ይብላኝ
ጉድጓድ ትግባ ነፍሴ ; ምቾት ይራቀኝ
መቆም እስኪያቅተኝ ; ጉልበቴ ይክዳኝ
ከአንቱ ሌላ ደስታ ; እኔ ምን አለኝ
ዘይኔ ና በሉኝ ; ተቋደስ ከማድ
❤የመውሊዶን ጠላት ; ልምታው እንደ ድቢ
እኔ እንድወዛወዝ ; እርሱን አንገብግቤ
ቢሰራ ነው እንጂ ; ቀልቡ እንደ ሹርቤ
በወንጀል ቢጠለፍ ; ሩሁ እንደጋቢ
የኸይራቱን ግቢ ; የመጣው ሊያነድ
❤ቢወርድ ለኢሳ ; ከሰማዩ ማድ
ጌታን ለማመስገን ; አደረጉት ኢድ
ምግብም ከተገባው ; ይሄን ያህል ሀምድ
እንዴት ይዘነጋል ; ያንቱ መወለድ
እናከብረዋለን ; እስክንገባ ለህድ
❤ሶላትና ሰላም ; በሞላው ቁጥር
ከሰማይ ምድር ; ባረከው ስፍር
ከሳር ቅጠል በልጠው ; ካሸዋ ክምር
በኸልቁ ሁላ እድሜ ; ቆጥሮ ዘር ማንዘር
አውርደው ቃዲር ; ረህመቱን በዘይኔ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😍ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
#Al burda jeme'a
👏👏👏👏👏👏👏👏
@yehadra_gtmoch
👏👏👏👏👏👏👏👏