የእውቀት ካዝና


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ኢንሻአላህ በአላህ ፍቃድ ስለ ዲናችን እንማማርበታለን ፣ አጫጭር መልዕክቶችን እናስተላልፋለን አላማችን እናንተ ያላወቃችሁትን ማሳወቅ ነው ደግሞ እኛ ከማንም በልጠን አይደለም።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ምንም ያክል ተደራራቢ መከራ ዉስጥ ብንሆንም በአላህ ላይ የሚኖረን ተስፋና መልካም ምኞት ግን ፍጹም ሊሸረሸር አይገባም።
ነብዩላሁ የዕቁብ عليه الصلاة والسلام በጣም የሚወደውን ልጁን ዩሱፍን አጣ። ቀጥሎም የዩሱፍ ወንድም ጠፋበት። በሶስተኛ ደረጃ በብርቱ ሀዘን ምክንያት ዐይኖቹን አጣ።
እንደዚህ አይነት ተደራራቢ ተስፋ አስቆራጭ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የዕቁብ عليه الصلاة والسلام ግን ሁሉም ወደቦታቸው ይመለሳሉ የሚል ጽኑ ተስፋ ነበረው።
"ከአላህ እዝነትማ ፍጹም ተስፋ አትቁረጡ" እያለ ያስተምር ነበር።

ተስፋውም ከንቱ አልሆነበትም። ልጆቹም ተገኙ። የዐይኖቹ ብርሃንም ተመለሰ።

وَلَا تَيْئَسُوا مِنْ رَوْحِ اللَّهِ
سورة يوسف [87]

@Dnel_Eslam
@Yeuwket_kazna


🚩ደርስ አድዱሩሱል ሙሂማህ ክፍል ፦ 4⃣

👤የቂርአቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ (አላህ ይጠብቀው)
للأستاذ ፡ أبو يحي عبد الواسع.(حفظه الله)






Репост из: የእውቀት ካዝና
ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) ማወቅ

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

🍂 ውልደታቸው፡-

የተወለዱት እ.ኤ.አ. በ570 መካ ውስጥ ነው፡፡ ሲወለዱ አባታቸው በህይወት አልነበሩም፡፡ እናታቸውንም ያጡት ገና ልጅ ሆነው ሳለ ነው፡፡ ተንከባክበው ያሳደጓቸው መጀመሪያ አያታቸው ዓብዱል ሙጠሊብ ሲሆኑ በመቀጠል ትንሽ አደግ እንዳሉ ደግሞ አጎታቸው አቢ-ጣሊብ ናቸው

🍂 ህይወታቸውና እድገታቸው፡-

ለነቢይነት ማዕረግ ከመብቃታቸው በፊት ለአርባ አመታት ያህል እ.ኤ.አ. (ከ570 -610) ከቁረይሽ ጎሳዎች ጋር ይኖሩ ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የታላቅ ሥነ-ምግባርና የፅናት ተምሳሌት እንዲሁም መለያ ሆነው ቆይተዋል፡፡ «ታማኙ» «እውነተኛው» በሚሉ የቅፅል ሥሞች በገሃድ ይታወቁ ነበር፡፡

እረኛ ነበሩ፡፡ ከዚያም በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ነብይ ከመሆናቸው በፊትም በኢብራሒም መንገድ በመጓዝ አላህን በብቸኝነት ያመልኩ ነበር፡፡ የጣዖትና የባዕድ አምልኮዎችን ይርቁና ይጠየፉ ነበር፡፡

🍂 ተልዕኳቸው፡-

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) አርባ ዓመታትን በዚህ ሁኔታ ካሳለፉ በኋላ፥ በመካ አቅራቢያ ከሚገኙ ተራራዎች አንዱ በሆነው «ኑር» ተራራ ውስጥ በሚገኘው «ሒራእ» ዋሻ ውስጥ በመሆን በጥልቅ ተመስጦ አላህን ያመልኩ ነበር፡፡ ከዚያም ከአላህ ዘንድ የሆነ ወህይ (ራዕይ) ይገለፅላቸው ጀመር፡፡ የአላህ ቃል የሆነው ቁርኣን በእርሳቸው ላይ መውረድ ጀመረ፡፡

በመጀመሪያ በርሳቸው ላይ የወረደው የቁርኣን ቃል…”አንብብ ፥ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም” የሚለው ነበር ይህ የእርሳቸው ተልዕኮ ዕውቀትን፣ ንባብን፣ ብርሃንና የቀጥተኛ ጎዳናን የማብሰሪያ አዲስ ዘመን ጅማሮ መሆኑን ለመግለፅ ይህ አንቀፅ ወረደ፡፡ ከዚያ በሃያ ሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሌሎች የቁርኣን አናቅፅ እየተከታተሉ ወረዱ፡፡

🍂 የዳዕዋ (የሰበካ) መጀመር፡-

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ለሦስት ዓመታት ያህል ሰበካቸውን በድብቅ አካሄዱ፡፡ ከዚያም ለተከታዮቹ አስር ዓመታት ሰበካቸውን በግልፅና በገሃዱ አደረጉ፡፡

ነቢዩና (ሰ.ዐ.ወ.) የእምነት ባልደረቦቻቸው (ሶሃቦች) ይህን በማድረጋቸው፥ ጎሳዎቻቸው ከሆኑት ቁረይሾች ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ፣ ሁከትና፣ ማዋከብ ገጠማቸው፡፡

ወደ ሐጅ ለሚመላለሱ ጎሳዎች የእስልምና ግብዣ ቀረበላቸው፡፡ የመዲና ነዋሪዎች ዘንድ ጥሪው ተቀባይነትን አገኘ፡፡ ከዚያ ቀስበቀስ ወደ መዲና ከተማ የስደት ጉዞ ተደረገ፡፡.

🍂 ስደት፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እ.ኤ.አ. በ622 ያኔ «የስሪብ» ትባል ወደ ነበረችው መዲና ከተማ ስደት አደረጉ፡፡ በወቅቱ የሃምሳ ሦስት ዓመት ጎልማሳ ነበሩ፡፡ ዳዕዋቸውን ያወገዙ የቁረይሽ ጎሳ ባላባቶች ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ላይ ግድያ ለመፈፀመ አሲረው ነበር፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ኢስላም እየተጣሩ ለአስር አመታት ያህል በመዲና ከተማ ኖሩ፡፡ ሰላት፣ ዘካና ሌሎች የሸሪዓው ህግጋቶች እንዲተገበሩ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡

🍂 እስልምናን ማሰራጨት፡-

የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ ከ622-632 ባለው ጊዜ ውሰጥ የኢሰላማዊ ስልጣኔ መሠረት ተክለዋል፡፡ አዲስ ሙስሊም ማህበረሰብ ፈጥረዋል፡፡ ዘረኝነትና ጎሰኝነትን አስቀርተዋል፡፡ ዕውቀትን አሰራጭተዋል፡፡

የፍትህ፣ የፅናት፣ የወንድማማችነት፣ የመረዳዳት መርህን ገንብተዋል፡፡ አንዳንድ ጎሳዎች እስልምናን በአጭሩ በማስቀረት ተነሳስተው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ጦርነቶች ተካሂደዋል፡፡ አላህ ሃይማኖቱንና መልእክተኛውን ረድቷል፡፡

ከዚህ በኋላ በመካ ነዋሪ የሆኑ ብዙ ጎሳዎች ወደ እስልምና ገብተዋል፡፡ በዓረብ ፔንሱላ ከተማዎች የሚኖሩ በርካታ ጎሳዎችም በራሳቸው ምርጫ ፍላጎትና ውዴታ ወደ ዚህ ታላቅ ሃይማኖት እየተግተለተሉ ገብተዋል፡፡

🍂 ህልፈታችው፡-

የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) በሂጅራ የዘመን አቆጣጠር ሰፈር 11፣ መልእክታቸውን አድርሰው ጨረሱ፣ አደራቸውንም ተወጡ፡፡ አላህም ሃይማኖቱን ሙሉ በማድረግ ለሰዎች ፀጋውን አጎናፀፈ፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የወባ ህመም አጋጠማቸው፡፡ ያደረባቸው ህመም እየፀና ሄደ በወርሃ ረቢዑል አወል በዕለተ ሰኞ በ11ኛው ዓመተ ሒጅራ ይህን ዓለም ተሰናብተው ወደ ቀጣዩ ዓለም ተሸጋገሩ፡፡

ይህ ማለት እ.ኤ.አ. ሜይ 8¸ 632 መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ዓለም ሲለዩ የስድሳ ሦስት ዓመት አዛውንት ነበሩ፡፡ ግብአተ-መሬታቸው የተፈፀመው ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ አጠገብ እሜቴ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ነው፡፡

🍂 የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ሙሉ ስም፡-

ሙሐመድ ቢን አብደላህ ቢን ዓብዱል ሙጠሊብ ቢን ሃሺም አል-ቁረይሺ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ጎሳ በዓረቦች ዘንድ እጅግ የተከበረ ጎሳ ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰው ዘር ሁሉ የተላኩ መልእክተኛ ናቸው፡፡

 አላህ ነቢያችን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሁሉም የሰው ዘር በጠቅላላ ልኳቸዋል፡፡ እርሳቸውን መታዘዝ በሁሉም ሰው ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልእክተኛ ነኝ፡፡” (አል-ዕራፍ፡158)

በርሳቸው ላይ ቁርኣንን አወረደ፡-
አላህ፥ ከፊቱም ሆነ ከኋላው ሃሰት የሌለውን ታላቅ መፅሐፍ ቁርኣን በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ አወረደ፡፡

የነቢያትና የመልእክተኞች መደምደሚያ፡-
አላህ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ.) የላከው የመጨረሻና መደምደሚያ ነቢይ አድርጎ ነው፡፡ ከርሳቸው በኋላ የሚነሳ አንድም ነቢይ የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “…ግን የአላህ መልእክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡” (አል-አሕዛብ፡4ዐ)

🍂 «ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው» የሚለው ቃል ትርጉም

እንዲህ ብሎ መመስከር፥ የተናገሩትን አምኖ መቀበል፣ ትዕዛዛቸውን መፈፀምና ክልከላቸውን መታቀብ ማለት ነው፡፡ አላህንም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በደነገጉትና ባስተማሩን መሠረት ብቻ ማምለክና መግገዛት ማለት ነው

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 https://t.me/Dnel_Eslam


አስርቱ ውድ ቀናቶች
➖➖➖➖➖➖➖➖

🇸🇦የተክቢራ አይነቶች
🇸🇦የኢድ ተክቢራ አፈፃፀም
🇸🇦ተወዳጁ የተክቢራ አይነት
🇸🇦ተክቢራ የሚጀመርበት ጊዜ
🇸🇦ተክቢራ የሚያበቃበት ወቅት
🇸🇦በተክቢራ ጊዜ የሚፈፀም ቢድአ

◾️ሼር በማድረግ ሰዎችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/TCEdrT16en4tGrEB


Репост из: የእውቀት ካዝና
🚩አድዱሩሱል ሙሂማህ ደርስ ክፍል ፦ 3⃣

👤የቂርአቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ (አላህ ይጠብቀው)
للأستاذ ፡ أبو يحي عبد الواسع.(حفظه الله)




Репост из: የእውቀት ካዝና
“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

የዚህ ታላቅ የሆነ ቃል ትርጉምና ዓላማ ግልፅ እንዲሆንልን ከተፈለገ ሁለት መሠረቶችን ማወቁ ግድ ይለናል፡፡

የመጀመሪያው መሠረት፡- «ላ ኢላሃ» (አምላከ የለም) የሚለው ነው፡፡ ይህ ከአላህ ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ አምልኮን መሻራችንን ማረጋገጫ ቃል ነው፡፡ ማጋራትን ውድቅ ማድረጊያ ቃል ነው፡፡ ከአላህ ሌላ በሚመለኩ ነገሮች ሁሉ መካድ ግዴታ ነው፡፡ ከአላህ ሌላ ሰውም ሆነ እንሰሳትም ሆነ መቃብርም ሆነ ከዋክብትም ሆነ ሌላ ማምለክ አይቻልም፡፡

ሁለተኛው መሠረት፡- ኢልለ ላህ (ከአላህ በስተቀር) የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ አምልኮን ለአላህ ብቻ የምናረጋግጥበት ቃል ነው፡፡ ሶላትን፣ ዱዓእና መመካትን የመሳሰሉ የአምልኮ ዓይነቶችን ሁሉ ለአላህ ብቻ የምናውልበት ማረጋገጫ ነው፡፡

የአምልኮ ዓይነቶችን በሙሉ ልንሰጥ የሚገባው አንድና አጋር ለሌለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳ ከአላሀ ውጪ ላለ ነገር አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ይሆናል፡፡

አላህ እንዲሀ ይላል …“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለርሱ በርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚግገዛ ሰው ምርመራው ጌታው ዘንድ ብቻ ነው፤ እነሆ ከሀዲዎች አይድኑም፡፡” (አል-ሙእሚን፡117)

ከአላሀ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለው ቃል ትርጓሜና መሠረቶች እንዲህ በሚለው የአላህ ቃል ውስጥ ተገልጿል… “በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡” (አል-በቀራህ፡256)

በዚህ የአላህ ቃል ውስጥ “በጣዖትም የሚክድ” የሚለው ቃል የመጀመሪያ መሠረት የሆነውን “አምላክ የለም” የሚለውን ቃል ሲሆን ያረጋገጠው “በአላህ የሚያምን” የሚለው የጌታችን ቃል ደግሞ ሁለተኛ መሠረት የሆነውን ከአላህ በስተቀር የሚለውን ቃል የረጋግጥልናል፡፡

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 https://t.me/Dnel_Eslam


ያወቁትን ማሳወቅና ጥቅሞቹ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

◼️እውቀትን ማሰራጨት፦
👉ጥቅሞቹና
👉መንገዶቹ
ወደ አላህ መንገድ መጣራት
🔻አሳሳቢነትና
🔻አስፈላጊነት

🎙አቡ አብደላህ ኢብኑ ኸይሩ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


🎤 የቁርአን ሀለቃ ፕሮግራም🌷

የዛሬው ቂርአት ሱረቱ አል ፋቲሀ ይሆናል

🖌ቁርአን አስተካክሎ ማንበብ
ለሚፈልግ ሁሉ ቀለል ካለ
የተጅዊድ ማብራሪያ ጋር

✅ክፍል 1⃣

🔭በወንድም ጀላሉ ሁሰይን

ማክሰኞ 26/11/1442 ሂ

@bin_Husseynfurii
👆👆👆👆👆👆👆
ቻናሉን ተቀላቅለው ቁርአኖን ያስተካክሉ
ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩት


ደርስ ክፍል ፦ 2⃣

👤የቂርአቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ (አላህ ይጠብቀው)
للأستاذ ፡ أبو يحي عبد الواسع.(حفظه الله)

🔴የዛሬው ደርስ የሚያካትተው ፦

♦️ባለፈው ደርስ ላይ ስለተመለከትነው 4ቱን የ"ላኢላሃኢልለሏህ" መስፈርቶች መጠነኛ ዳሰሳ
°https://t.me/Dnel_Eslam


Репост из: QUR'AN RECITATION ONLY
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: የእውቀት ካዝና


🔻በሁለት ቅንብ መካከል ያለን ፀጉር ማንሳት በተመለከተ




ደርስ ክፍል ፦ 1⃣
👤የቂርአቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ (አላህ ይጠብቀው)
للأستاذ ፡ أبو يحي عبد الواسع.(حفظه


Репост из: የእውቀት ካዝና
አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹አማኞቸ ከአላህ ዘንድ ያለውን ቅጣት ቢያውቁ ኖሮ አንዳቸውም ጀነትን ባልተመኙ ነበር፡፡ ከሀዲያን ከአላህ ዘንድ ያለውን እዝነት ቢያውቁ ኖሮም አንዳቸውም ከጀነት ተስፋ ባልቆረጡ ነበር፡፡››

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ የአላህ ምህረት ሰፊ ነው! በፍርሃት ብቻ ተውጦ ወደ ተስፋ መቁረጥ ማምራት አያስፈልግም፡፡ መልካም ነገር እየሰሩ በተስፋ መሞላት የግድ ነው፡፡
‹‹ ሀዲሱ የፍርሃትና የተስፋን ባህር በአንድ አዋህዶና አጣጥሞ መጓዝ ተገቢ እንደሆነ ያስተምራል፡፡

https://t.me/Dnel_Eslam
🇸🇦🇸🇦
https://t.me/Yeuwuket_kazna


ሸህ ሚስባህ

https://t.me/Dnel_Eslam
https://t.me/Dnel_Eslam
🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦



Показано 20 последних публикаций.

18

подписчиков
Статистика канала