#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን
#መሠረቱ
👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው።
👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል።
#ቅጣት የሚገደበው
1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤
2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤
3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል።
4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል።
#ቅጣት የማይገደበው
1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤
2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤
4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ።
ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
#laws2016
https://t.me/NegereFej
#ነገረ_ፈጅ