🏮
~የዛሬውን ግጥም ለማንበብ ወስኑ
~ትንሽ ጠቃሚ ነው ብታምኑም ባታምኑ
ማንበቡስ ብቻውን ምንም ዋጋ የለው
መቼ ጠፍቶ ነበር ° ° ° ተናጋሪስ እንደው
ተግባሪው ነው እንጂ ከኛ ውስጥ ያጣነው
✔የዛሬውን ግጥም_ልጀምር ቢስሚላህ
✔እንደምን አላችሁ ✔ያ አህባቢ ፊላህ
✔የኢስላምን መግቢያ ሁለቱን ቃላቶች
✔ጠንቅቀን እንወቅ ✔ ብእሬ ብላለች
✔ትርጉሙን ተረዳው እንግዲ ወንድሜ
✔አሰፍርልሃለው ✔ እዚው በግጥሜ
✔የሸሃዳን ትርጉም ስፅፈው በአጭር
✔በሀቅ የሚመለክ የለም አንድም ነገር
✔ከአለማት ፈጣሪ✔ከአላህ በስተቀር
✔የሚለው ይሆናል•• ወንድሜ ሲፈሰር
✔የጥመት ቡድኖች ተብሊግን ይመስል
✔ከዚህ ውጪ ሌላ ትርጉም ይሰጡታል
✔ቢለዋም አይቆርጥም ያለ አላህ ፍቃድ
✔እሱ ካልፈቀደ ✔ እሳትም አይነድ
✔አላህ ነው ያቆመው የበሬውን ቀንድ
✔እያለ ይኖራል✔ "የተብሊግ ሙሪድ
✔አረ አላህን ፍራ በኢስላም አትቀልድ
✔ብሎሃል በልልኝ *☞* ዲኑን አትናድ
✔ከየት እንዳመጣሀው ንገር ይህን ትርጉም
✔ብትለው እንግዲ ✔ምንም አይችልም
✔ለቆ ከመሄድ ውጭ ✔ትንሽም አይልም
✔ስለ ተብሊግ ፊርቃ _ብዙ ጉዳጉድ
✔በግጥም መልክ_አለ የተፃፈ ረድ
✔ፈልገህ አንብበው_ እንዳትሸወድ
✔የአንዳንዱን ሁኔታ °°° እንደው ስቃኘው
✔ቢላል አህመድ ብሎ የሙስሊም ስም ነው
✔ጠጋ ብለሀው ግን አንዴ ብትፈትሸው
✔የሸሃዳን ትርጉም✔ ገና የማያቅ ነው
✔አይደፋም አንዴ ✔ለጌታው ሱጁድ
✔ለይቶ አያውቅም ሽርኩን ከተውሂድ
✔ቢድዓ እና ሽርክን✔ የወንጀል መሀት
✔ሲፈፅም ይውላል አይሰግድም ሰላት
_የመስጂድን በራፍ ረግጦ መቼ ያውቃል
_እንደው ሲታይ ስሙ አብደላህ ተብሏል
_እይልኝ እንግዲ አብዘሃኛው ሙስሊም ሰው
_በዚሁኔታ ነው ወንድም የሚኖረው
_ስለዚህ ፈጠን በል ተውሂድ አስተምረው
_የሽርክን አደጋ ✉ ቀርበህ አስረዳው
✔የሰላቷን ሸርጥ ✉ ሩክኗን ንገረው
✔ትልቅ ምንዳ አለክ አላህ ከመራው
_የሸሃዳው ቃል ☞ ትርጉሙ ሳይታወቅ
_ሙስሊም አይኮንም እንግዲ እንወቅ
~አደራ እላለው___ ከዚ በመቀጠል
~ዲኑን ማያቅ ሙስሊም አትሁኑ ስል
~በስም ብቻ ሙስሊም መሆን አይቻልም
~ጀነት ያለ ተግባር ✔ ምንም አይገኝም
_"በአላህ በአንድነቱ በተውሂድ ካመንክ
_`የአብደላህን ልጅ ﷺ ወድጃለው ካልክ
_``ወደ ተግባር ግባ ዳይ ወደ ሰላትክ
_``እንግዲ ወዳጄ✔ እንዳታንቀላፍ
_``በዲንህ ላይ ጠንክር አትሁን ዘፋፋ
✔•ቁርዓንን አንብበው በጥዋትም በማታ
✔•ላንተ ነው የላከው ከአዐርሽ በላይ ጌታ
✔_ውዶቼ እንግዲ የእናንተው ተግባር
✔_በጭራሽ እንዳይሆን ሸሪዓን ሚፃረር
✔እስኪ ቆም ብለህ እራስህን እየው
✔ልብስ አለባበስህ እውን የሙስሊም ነው
✔ከላይ በኩልሳ ☞•• ቆቡ ምንድነው
[]መልእክቱ ሲደርስክ ቀስ ብለህ ሄደህ
[]የላይኛውን ቆብ በደንብ አስቀንሰህ
[]እንደው ቢቻል ቢቻል ..ልሙጥ አስቆርጠህ
[]ሱሪህም ከበዛ ሱና አስደርገህ
[]ወደ መስጂድ ግባ እንግዲ አደራህ
[]እሺ በል ታዘዘኝ ለአላህ ብለህ
[]ላንተው ነው ጥቅሙ ሁሉም ነገር ሲታይ
[]ሱሪህም ከሆነ ☞ምድርን ወልዋይ👖
[]ልብስ ስታጥብ__ ሁሌ አትጎዳም ቆይ?
[]ሳሙና ተወዷል {}{} ወንድም በዛ ላይ
[]ልክ እንደዛው ሁላ ካበቀልክ ፍሪዝ
[]ትጎዳብኛለህ ✔ ስትገዛ ቫልዝ
[]ፊሪዝህን አንሳው ✔እሺ ብለሀኝ
[]የማስቆረጫ ብር ካጣህ ጠይቀኝ
[]ስለዚህ ሸሪዓ ~~አንድን ነገር ሲያዝ
[]ጥቅሙ ላንተ ነው ቢልህም ጋዝ ጋዝ
[]ነቃ ብለህ ተግብር ወንድም አትፍዘዝ
___
✍በወንድማችን አቡ ያሲር አላህ ይጠብቀው!
☞ክፍል ሶስት
ይቀ-ጥ-ላል
https://t.me/YusufAsselafyhttps://t.me/YusufAsselafy