⛳️መጽሐፈ ሩት “የመጽሐፈ ሩት ፀሐፊ ማን እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ምንም መረጃ የለም፡፡የአይሁድ ትውፊት መጸ ሐፉን የጻፈው ሳሙኤል ነው ይላል፡፡ የመጽሐፉ የመጨረሻ ትኩረት በዳዊት ላይ ስለሆነ ጸሐፊው ሳሙኤል አይመስልም፡፡ ስለዚህ በዳዊት ዘመነ መንግስት ወይም ከዚያ ጥቂት ራቅ ብሎ እግዚአብሔር የዳዊትን የዘር ግንድ ለመጠበቅእንዴት እንደሰራ ለመግለጽ የሚፈልግ አንድ ሰው እንደጻፈው ይገመታል፡፡ 📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 399)፡፡
⛳️መጽሐፈ ሳሙኤል “አንዳንድ ሰዎች የነብዩን ናታን ልጅ የነበረውና የንጉስ ሰለሞን የግል አማካሪ ሆኖ የሰራው ዛቡድ መጽሐፈ ሳሙኤልን ጽፋል ብለው ይገምታሉ(1ኛ ነገስት 4፡5)፡፡ ነገረ ግን ከሁሉም የሚሻለው 1ኛ ና 2ኛ ሳሙኤል ጸሐፊው ማን እንደሆነ አይታወቅም ማለቱ ነው ፡፡ ሳሙኤል ነው የጻፈው ማለት አይቻልም ምክኒያቱም የ1ኛ ሳሙኤል መጨረሻ አከባቢና የ2ኛ ሳሙኤል ታሪክ በሙሉ የተጻፈው እርሱ ከሞተ በኋላ በመሆኑ ነው፡፡”📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 412-413)፡፡
⛳️የሳሙኤል መጻህፍት ማን እንደጻፋቸው አልተገለጠም ሆኖም እነሳሙኤል የዘመናቸው ታሪክ የፃፉ መሆኑ ታውቋል፡፡”፡፡”📜(የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 79)
መጽሐፈ ነገስት “የመጽሐፈ ነገስት ጸሐፊ ማን እንደሆነ የምናውቅበት አንዳችም መንገድ የለም ….መጽሐፈ ነገስትን ከተለያዩ መጽሐፍት ያጠናከረው አንድ ሰው እንደነበረ ማመን ከሁሉም የተሸለ መንገድ ነው ፡፡ይህ ያልታወቀ ጸሐፊ መጽሐፍ ከ586-539 ዓ.ዓለም ባለው ጊዜ አጠናቆታል፡፡
”📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 486) “የነገስታ ታሪክ በሙሉ አስቀድሞ በ1 መጽሐፍ ብቻ ተጽፎ ነበር 70 ሊቃናት ግን ወደ ግሪክ ቋንቋ በመተርጎሙበት ጊዜ መጽሐፉ በ2 ተከፈለ፡፡ መጽሐፉ የተጻፈው ንጉስ ዩአኪን ከሞተ በሃላ ነውና ምናልባት በስደት ዘመን በባሊን አገተረ ሳያጻፍ አልቀራም 2ነገ. 25፤29፤30፡፡ጻሐፊው ማን እንደሆ ግን አልታወቀም፡፡ ነገር ግን እንደ ጥንት አይሁድ አሳብ በታወቀ ነብይ (ነብያት) እንደተጻፈ ይታሰባል፡፡ ጻሐፊው ታሪኩን ሲያዘጋጅ ቀደም ብሎ ስለጉዳዩ የተጻፉ መጻሐፍትን እንዳነበበ ይታመናል፡፡”
📜 (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 136)
መጽሐፈ ዜና መዋእል “መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን መጽሐፍ ጸሓፊ ማን እንደሆነ ጨርሳ ስለማይናገር በበኩላችን የምንሰጠው አስተየየት ግምታዊ ነው ፡፡ የዕብራዊያን ትውፊት የመጽሐፍ ጸሐፊ ታሪኩን በመጽሐፈ ዕዝራ ያነበብነው ካህን እዛራ ነው ይላል፡፡መጽሐፈ ዕዝራ ነሀሚያና ዜና መዋእል በአንድ ጸሐፊ መጻፋቸውን የሚያመለክት በርካታ ተመሳሳይነት አለ በማለት ቡዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይስማማሉ ነገር ግን ሌሎች ምሁራን ደግሞ በርካታ ልየነት ስላለ ጸሐፊው እዝራ አይደለም ይላሉ፡፡ 1ኛ ና 2ኛ ዜና የተጻፉት በአንድ ሰው ነው፡፡ጸሐፊው ማን እንደሆነ ባናውቅም ዳሩ ግን የታሪክ ሰው፤ የስነ መለኮት ትምህርት አዋቂና መምህር መሆኑ ከጻፈው መጽሐፍ እንገነዘባለን፡፡ይህንን የምንመለከተው የጻፋቸው ነገሮች በመረጠበት ሁኔታ ነው፡፡
”📜 (ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 559-560)፡፡
ብዙ መምህራን “መጽሐፉን የጻፈው ካህኑ እዝራ ነው” ይላሉ ይህም እውነት ይመስላል፡፡ ሆኖም የትውልድ ዝርዝሩ ከዕዝራ ዘመን በኋላ ይሆናል፡፡ ዘመኑ ከክርስተስ በፊት 400 ዓመት ያህል ይሆናል፡፡ጸሓፊውም ሲጽፍ የነገስታት ታሪክ በተጻፈባቸው በሌሎች ጹሁፎች መጠቀሙ ታውቋል፡፡”
📜 (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 217)
መጽሐፈ ዕዝራ “የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን መጽሐፈ ዕዝራና ነህሚያ በማን እንደተጻፈና እንዴት እንደተጻፈ ያላቸው አመለካከት የተለያዩ ነው፡፡ የአብዛኛዎቹ አስተሳሰብ ዕዝራና ነህምያን የጣፈው ዜና መዋእልን አጨራረስና የመጽሐፈ ዕዝራ አጀማመር ተመሳሳይ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም በአጻጻፍ ስልቱም ተመሳሳይነት እናገኛለን፡፡
ሌሎች ምሁራን ደግሞ መጻሕፍቱ ቡዙ ተመሳሳይነት ቢኖሯቸውም የተጻፉት ግን በተለያዩ ጸሐፊዎች ለመሆኑ የሚያሳምኑ በቂ ልዩነቶች እነገኛለን ይላ..የመጽሐፈ ዕዝራና ነህሚያ ጸሐፊ ማን እንደሆነ ስለማናውቅ የተጻፉበትንም ጊዜ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም፡፡”
📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 580-582)
⛳️መጽሐፈ አስቴር “መጽሀፉ በፋርስ መንግስት ጊዜ በምርኮኝነት ይኖሩ በነበሩ እስራኤላውያን ላይ የደረሰውን ስደትና ከሞት አደጋ መዳናቸውን፡፡ መጽሐፉ አርጤክስስ ከሞተበት ከ465 ከክርስቶስ በፊት እንደተጻፈ ይገመታል መጽሐፉን የጻፈው ማን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ሆኖም ጸሐፊው የፋርስ ቤተ መንግስት ስርአትና ደንብ ያወቀ አይሁድ ይመስላል፡፡”
📜(የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 150)
መጽሐፈ ኢዮብ “መጽሐፈ ኢዮብ ውስጥ የምናገኘው ታሪካዊ ዘገባ አነስተኛ በመሆኑ መቼ እንደተጻፈና ማን እንደጻፈው ለመናገር አንችልም ልናገርገው የምንችለው የመመራመር ግምት ማቅረብ ነው፡፡
📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 2ኛ መጽሐፍ ገጽ 32)
ከላይ መናሙና የቀረቡት ምሳሌዎች አንድ ጥያቄ እንድንጭር ይዳርገናል ፡፡ “ጸሐፊዎቻቸው ያልታወቁ መጽሐፍት የአምላክ ቃል ናቸው ማለት ይቻላል?”
በዚህ መልኩ ሁሉም የብሉ ኪዳን መጻህፍት ማን ፤ የትና መቼ እንደተጻፈ በእርግጠኛኝነት የማይታወቅ መሆኑን የክርስትና ስለ-መለኮት ምሁራን ይናዘዛሉ፡፡የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን በተመለከተም ተመሳሳይ ብዥታ ያጋጥመናል፡፡ የታሪክ ተመራማሪው አዶልፍ ሐርናክ እንዲህ ይሉናል፡- “አራተኛው ወንጌል ከሐዋሪያው ዩሐንስ አልመነጨም ፡፡ ከርሱ የመነጨ መሆኑ በራሱ አያረጋግጥም ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያው ዩሐንስ ቢሆን እምነት የሚጣልበት የታሪክ ምንጭ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም” አዶልፍ ሐርናክ የታዋቂው የክርስትያን ታሪክ ተመራማሪ የዴቪድ እስትረውስን የምርምር ስራ በመጥቀስ ጸሐፊውፀሐፊው “የአራተኛ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያዎቹን ሶስት ወንጌሎችም ታሪካዊ ተአማኒነት ውድቅ አድርገውታል ሲል ጽፏል” 📕(What is Christianity , Adolf Harnack p20 )