የቁርአን ሱራህ ►⁴
አላህ ራሱ ነው ቁርአንን ከፋፍሎ ያወረደው፦
وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا
►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡
ቁርአን ሱራ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦
سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡
ሱራህ አንድ፦►ሱረቱል ፋቲሓህ ፦~فاتحة~
ፋቲሓህ ማለት መክፈቻ ማለት ነው።
وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ
►📗[ሱረቱ አል-ሒጅር 15፤87]
ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡
ከሚደጋገሙ የኾኑ የተባለው ሱረቱል ፋቲሓህ መሆኑን ነብያችንصلى الله عليه وسلمነግረውናል፦
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي " .
አቢ ሁረይራ ረ.ዐ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ፦አልሐምዱሊላህ የቁርኣን እናት፣ የመጽሐፉ እናት እና ሰባት የተደጋገሙ (አናቅጽ)ናቸው።
Narrated Abu Hurairah:
that the Messenger of Allah صلى الله عليه وسلم said: "Al-Hamdulillah is Umm Al-Qur'an and Umm Al-Kitab and the seven oft-repeated."
►📕[Jami at-Tirmidhi, Vol. 5, Book 44, Hadith 3124]
በተጨማሪም ይመልከቱ►
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 61, Hadith 528]
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 60, Hadith 226]
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 60, Hadith 227]
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلم ሱረቱል ፋቲሓህን በስሙ ጠርተዋል? አው በሚገባ፦
አንድ ሰው ፋቲሓህን ሳይቀራ ሰላት ከሰገደ ውድቅ መሆኑን ሲነግሩን بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ
የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓህ ብለው ተጠቅመዋል፦
عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ".
ኡባዳ ቢን አስ-ሳሚት እንደተረከው፦
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦
በሶላቱ ውስጥ የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓን ያልቀራ ሰላቱ ውድቅ ነው።
Narrated 'Ubada bin As-Samit:
Allah's Messenger صلى الله عليه وسلم said, "Whoever does not recite Al-Fatiha in his prayer, his prayer is invalid."
►📕[Sahih al-Bukhari Vol. 1, Book 12, Hadith 723]
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እራሳቸው بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ". የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓህ
ብለው ይጠቀሙ ነበር ሌላም ተመሳሳይ ሐዲስ እንመልከት፦
عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، يَبْلُغُ بِهِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم " لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ " .
ዑባዳህ ኢብን አል-ሳሚት እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፡-የመፅሃፉን መክፈቻ ሱረቱል ፋቲሓን ያልቀራ ሰው ምንም ሶላት የለውም ።
Ubadah ibn al-Samit reported from the Messenger of Allahصلى الله عليه وسلم
He who does not recite Fatihat al-Kitab is not credited with having observed the prayer.
►📕[Sahih Muslim,Book,4 Hadith 37]
عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ " .
ዑባዳህ ቢን ሳሚት እንደተረከው፦ነብዩصلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፡- “የመፅሃፉን መክፈቻ ሱረቱል ፋቲሓን ላልቀራ ሰው ምንም ሶላት የለውም ።
It was narrated from Ubadah bin As-Samit that :
The Prophet صلى الله عليه وسلم said: "There is no Salah for one who does not recite Fatihatil-Kitab."
►📕[Sunan an-Nasa'i,Vol. 2, Book 11, Hadith 911]
በተመሳሳይ መልኩ ቲርሚዚ ዘግቦታል፦
►📕[Jami at-Tirmidhi, Vol. 1, Book 2, Hadith 247]
ኢብኑ ማጃህም ዘግቦታል፦
►📕[Sunan Ibn Majah, Vol. 1, Book 5, Hadith 837]
እናም ነብያችን صلى الله عليه وسلم ራሳቸው እና ሰሀባዎች ፋቲሓህ ብለው እነደሚጠቀሙ ተመልክተናል፦
በተጨማሪም ይመልከቱ►
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 1, Book,12Hadith 726]
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 1, Book 12, Hadith 729]
►📕[Sahih Muslim, Book 4, Hadith 1760]
በጣም ብዙ ሐዲስ አለ ላለማርዘም ይሄ በቂ ነው።
ማጠቃለያ፦
እንግዲህ ከላይ ጀምረን እንዳየነው
►አላህ ቁርአንን ከፋፍሎ እዳወረደ አይተናል
►አላህ ቁርአን ሱራ እንዳለው ቁርአን ውስጥ እንደነገረን አይተናል
►ነብያችን صلى الله عليه وسلم እና ሰሐቦች አል-ፋቲሓህ~ الفاتحة~ ብለው እንደተጠቀሙ ከጊዜ በኋላ እንዳልመጣ አይተናል።
سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡
ይቀጥላል .................https://t.me/AliDawah2