+ የማይነገር መቃተት +
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ። 8፥26
የማይነገር መቃተት ምንድ ነው ? ከተባለ ፦ መቃተት አስጨናቂ በሆነ ነገር መድከም ማለት ።
የመቃተት ትርጉም መልፍት ፣ መድከም ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ይለፍል ፣ ይደክማል ማለት ነው ወይ ተብሎ ከተጠየቀ፦ መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል እንደሚረዳን ወይም እንደሚያግዘን ይገባን ዘንድ (ይረዳን ዘንድ ) ለሰው ልጆች በሚነገረው አነጋገር ስለ ተነገረ ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደክምም ተብሎ ይመለሳል ። የማነገር መቃተት የሚለው መንፈስ ቅዱስ ይደክማል ተብሎ ስለማይነገር ነው ። መንፈስ ቅዱስ ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ጭንቅላቴ ዞረ አይልምና ። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ይህን የመሰሉ አነጋገሮች ይገኛሉ ።
በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ አረፈ (ዘፍ 2፥2 ) እግዚአብሔር ሥራ ሰርቶ ድካም አይሰማውም ። ዕረፍትም አያስፈልገውም ። ለሰው ልጆች በሚገባቸው አነጋገር ለመግለጽ ነው እንጂ ። አንድም የሰንበትን ዕረፍ ለሰው ልጆች ለመሥራት ነው ። "ጌታችን ያረፈበት ቀን ሰንበተ (ዕረፍት) ተብሎአልና ። እስራኤል በኃጢአት ላይ ኃጢአት ሲጨምሩ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት "ሸክም ሆነብኛል ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ " ብሎአል (ኢሳ.1፥14 ) ። እግዚአብሔር እንደ ሰው በትግዕሥቱ አይደክምም ። ወይም እንደ ሰው ትዕግሥቴን ጨርሻለሁ አይልም። "ልታገሣቸው ደክሜያለሁ " ማለቱ ፦ ብዙ ቢተገሣቸውም ከኃጢአታቸው የማይመለሱ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው እንጂ ። ( የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ከሮሜ እስከ ገላትያ ትርጓሜ/ማብራርያ መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ -106)
#ዓምደ_ሃይማኖት