የህይወት አርያዬ
ስትስቅ ፊቷ ፀሀዳ ነው። ምንም ትሁን ምንም ፈገግታ ከገጿ ተለይቶ አያውቅም። ሁሌም ትስቃለች...ማጥ ውስጥ ሆና እንኳን ለሀዘን አትዳዳም። ድንገት ሁሉ አቅቷት እንኳን ዐይኖቿ ቢያነቡ ዕንባዋን እየጠረገች መሳቅ ትጀምራለች ግርም ትለኛለች። ስሜቶቿ በሙሉ ሳቋ ውስጥ እንደ እየ አመጣጣቸው ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል። ከተረዳዋት ቀን አንስቶ ሳቋን እፈራዋለው። እውነት ከልቧ ይሆን? እያልኩኝ በሀሳብ ዋዥቃለው። በትንሹም በትልቁም ሁልጊዜ መፍለቅለቅ የዕለት ተዕለት ምግባሯ ነው። አንድ ቀን እንዲሁ ስትስቅ ዐይን ዐይኗን እያየው "ደህና ነሽ ግን?" አልኳት።
.
"አረ ደህና ነኝ ምን ሆነህ ነው?" ብላ መሳቋን ቀጠለች። ውስጤ ስላላመነበት ድጋሚ ጠየኳት ፤ የዛኔ "አዎ ደህና ነኝ" እያለች ዕንባዋ ከዐይኗ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ። ከድንጋጤ ብዛት ደርቄ ቀረው። ስትስቅ እንጂ ስታነባ ፈፅሞ አይቻት አላውቅም ነበር። እኔም እንደሌላው ደስተኛ እና ህይወትን ቀለል አድርጋ የምትኖር ሴት አርጌ ነበር ማስባት። እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ኖሮ። ከገባውበት ሰመመን ነቅቼ አባብላት ጀመር። ሁኔታዋን ስጠይቃት ታሪኳን አጫወተችኝ። ነግራኝ እንደ ጨረሰች ምንም እንዳልተፈጠረ ድጋሚ መሳቅ እና እንደ ወትሮዋ ማበዱን ቀጠለች። ግርም ብሎኝ ብዙ አየዃት። ሳፈጥባት ጊዜ "አረ ፈታ በል ምን ይገትርኻል?" እያለች ትስቅብኝ ጀመር።
.
የነገረችኝ ውስጤን ሰርጎ ቢሰማኝም ፤ በዛው ልክም ጥንካሬዋ ገረመኝ። የእስካሁን ግምቴ እና አስተሳሰቤ በሙሉ ፉርሽ ሆነብኝ። ህመም በብዙ መንገድ እንደሚገለፅ በእርሷ ተረዳው። እየረገጧት ምታብብ ፤ እየነከሷት የምትስም ኑሮ የገባት ብርቱ እንስት ናት። ከእሷ የተማርኩት ትምህርት እጅጉን ይልቃል። ከዛች ቀን አንስቶ እንደ ወትሮዬ ሳዝንና ስከፋ ፊቴን ማጨማደድ እና ማልቀስ ቀንቶኝ አያውቅም። ህይወት አጭር ናትና ሁሉን በፈገግታ ተቀብሎ በፈገግታ መሸኘት ነው። "ሳቅ ባይኖር ግን ምን እንሆን ነበር?" የሁልጊዜም ንግግሯ ነው።
እውነትም ሳቅ ባይኖር ግን ምን እንሆን ነበር?
ሰላም
በኪሩቤል አሰፋ
@Ebuh_bhr
@Ebuh_nhr