ዕቡህ_ብዕር


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


በ ዕቡህ ብዕራችን የሁሉንም ደጃፍ እያንኳኳን ስሜቶቻቸውን እንዳስሳለን. ብዕራችን ያቀለመውን በግጥም እያዋዛን ለእናንተ እናደርሳለን. ✍️
እንኳን ደህና መጣቹ
ለማንኛውም ሀሳብ ፣ አስተያየት እና ጥያቄ
@idcfe
@ediwub
ልታናግሩን ትችላላቹ🖋️

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የኔታ

ሀሁ አቦጊዳ
ከፊደል ገበታ
ጭራቸውን ይዘው
ሲያስቀኙን የኔታ

ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብ
ሂ ሳልስ ሃ ራብዕ
ብለን የቆጠርን ተቀምጠን ስራቸው
አንደበት ያስፈቱን ሊቀ ቀለም ናቸው
.
ወንጌለ ዮሀንስ ውዳሴ ማርያሙን
ቅዳሴ ሰዓታት ስርዓተ ፆሙን
ገድለ መልዓክትን ገድለ ቅዱሳናት
ህማመ ፋሲካን የስቃዩን ወራት
ሰብስበው ያሳዩን መንገደ ሥላሴን
ባህረ ሀሳብ ቀመር አቋጣጠር ጊዜን
.
በፈጣሪ ያሉ ዓለም ያልገዛቸው
የኔታ የሁሉም ባለውለታ ናቸው

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


አይበቃም ወይ ግፉ?
ለስምህ የቆሙ በሙሉ እረገፉ
ሌቱን በምስጋና ቀኑን በቅዳሴ
ይከበር ይወደስ እያሉ ሥላሴ
ዓለምን የጣሉ ፍቅርህ የገባቸው
መሞት መርገፍ ሆኗል ጌታ ሆይ ዕጣቸው
.
እንኳን ለወደደህ ለጠሉህ ምትራራ
መች ይሆን ሚያበቃው ይህ ሁሉ መከራ?
በቀልን የማታውቅ ፅኑዋ እምነታችን
ፍትህን ትሻለች ካንተ ከጌታችን
አሜን ብለን ስንችል ጥቃታችን በዝቷል
ገልጠህ ብታድስሰን ልቦናችን ደምቷል
.
ተደጋገመብን ፀና በላያችን
የሚመጣው በዝቷል በሀይማኖታችን
ጠላታችን በዛ ቆመን ተቀምጠን
አንተ ግን ጌታ ሆይ
የናፈቅነውን ፍትህ መች ይሆን ምትሰጠን?


@Idcfe
@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


የፈሰሰ አይታፈስም
ትላንትና አይመለስም
ስኖር ያኔ ከጎናቹ
ውል ጥቅሜ ያልገባቹ

ምን ፍለጋ ምን ቀረና
ከደጃፌ ተገኛቹ?
.
በትላንቴ ሳልበገር
ወደፊቴ ገስግሻለው
የራስ ዋጋ ሚገባኝን
አሁን በደንብ አውቂያለው
እንደ ወትሮው ላልጎተት
ለአንድ እራሴ ቃል ገብቼ
ሚገባኝን ስላወኩኝ
አልፊያለው ሁሉን ትቼ
.
ባለሁበት ስላልቆምኩኝ
ተጨንቃቹ ተጠባቹ
ካመለጥኩት ትላንትና
ልትመልሱኝ ላሰባቹ
.
የጣልኩትን ዞሬም አላይ
እንኳን ቀርቶ ልመለከት
በመጣ
እግር ተመለሱ
ደስተኛ ነኝ ባለሁበት

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


የእንግዳ ማረፊያ መስዬ ተገኘው
የመጣን ሳሳርፍ አጂውንም ሸኘው
ተቀብሎ ላኪ ዘላቂ የሌለው
መፈረጋገጫ ያ ሞኙ ልቤ ነው
.
ሲሉት ሚዘሉበት ሲሉት የሚያርፉበት
በቃኝን የማያውቅ ከቶ የሌለው ጉልበት
ጥቅመኛም ዐቀኛም በእኩል እያረፉ
ተረማምደው ጥለው ትተውት ያለፉ
.
ከቁብ ለማይቆጥሩት እየተጣጣረ
መገልገያ ሆኖ ዘላላም የቀረ
ያ ሞኙ ልቤ ነው

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


#የኛው_ገፆች

ሰው በእራሱ እንቆቅልሽ ነው በሀገር ሳይሆን በጊዜ ሚፈታ።

በኪሩቤል አሰፋ

@Idcfe
@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr




፪ ኢትዮጵያ
በዔደን ታደሰ እና ኪሩቤል አሰፋ
ተፅፎ እንደ ቀረበ
@ediwub & @idcfe

@Ebuh_bhr


ይሄ ስራ ይለቀቅ? የምትሉ እስኪ በ reaction vote አድርጉ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr






የህይወት አርያዬ

ስትስቅ ፊቷ ፀሀዳ ነው። ምንም ትሁን ምንም ፈገግታ ከገጿ ተለይቶ አያውቅም። ሁሌም ትስቃለች...ማጥ ውስጥ ሆና እንኳን ለሀዘን አትዳዳም። ድንገት ሁሉ አቅቷት እንኳን ዐይኖቿ ቢያነቡ ዕንባዋን እየጠረገች መሳቅ ትጀምራለች ግርም ትለኛለች። ስሜቶቿ በሙሉ ሳቋ ውስጥ እንደ እየ አመጣጣቸው ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል። ከተረዳዋት ቀን አንስቶ ሳቋን እፈራዋለው። እውነት ከልቧ ይሆን? እያልኩኝ በሀሳብ ዋዥቃለው። በትንሹም በትልቁም ሁልጊዜ መፍለቅለቅ የዕለት ተዕለት ምግባሯ ነው። አንድ ቀን እንዲሁ ስትስቅ ዐይን ዐይኗን እያየው "ደህና ነሽ ግን?" አልኳት።
.
"አረ ደህና ነኝ ምን ሆነህ ነው?" ብላ መሳቋን ቀጠለች። ውስጤ ስላላመነበት ድጋሚ ጠየኳት ፤ የዛኔ "አዎ ደህና ነኝ" እያለች ዕንባዋ ከዐይኗ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ። ከድንጋጤ ብዛት ደርቄ ቀረው። ስትስቅ እንጂ ስታነባ ፈፅሞ አይቻት አላውቅም ነበር። እኔም እንደሌላው ደስተኛ እና ህይወትን ቀለል አድርጋ የምትኖር ሴት አርጌ ነበር ማስባት። እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ኖሮ። ከገባውበት ሰመመን ነቅቼ አባብላት ጀመር። ሁኔታዋን ስጠይቃት ታሪኳን አጫወተችኝ። ነግራኝ እንደ ጨረሰች ምንም እንዳልተፈጠረ ድጋሚ መሳቅ እና እንደ ወትሮዋ ማበዱን ቀጠለች። ግርም ብሎኝ ብዙ አየዃት። ሳፈጥባት ጊዜ "አረ ፈታ በል ምን ይገትርኻል?" እያለች ትስቅብኝ ጀመር።
.
የነገረችኝ ውስጤን ሰርጎ ቢሰማኝም ፤ በዛው ልክም ጥንካሬዋ ገረመኝ። የእስካሁን ግምቴ እና አስተሳሰቤ በሙሉ ፉርሽ ሆነብኝ። ህመም በብዙ መንገድ እንደሚገለፅ በእርሷ ተረዳው። እየረገጧት ምታብብ ፤ እየነከሷት የምትስም ኑሮ የገባት ብርቱ እንስት ናት። ከእሷ የተማርኩት ትምህርት እጅጉን ይልቃል። ከዛች ቀን አንስቶ እንደ ወትሮዬ ሳዝንና ስከፋ ፊቴን ማጨማደድ እና ማልቀስ ቀንቶኝ አያውቅም። ህይወት አጭር ናትና ሁሉን በፈገግታ ተቀብሎ በፈገግታ መሸኘት ነው። "ሳቅ ባይኖር ግን ምን እንሆን ነበር?" የሁልጊዜም ንግግሯ ነው።

እውነትም ሳቅ ባይኖር ግን ምን እንሆን ነበር?

ሰላም

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_nhr


ሳቁ
ዕልፍ አመት ላትኖሩ ከቶ አትጨነቁ
ዛሬያቹውን እንጂ ነጊያቹን አታውቁ
ምንም ብትከፉ ውጣውረድ ቢበዛም
ያደጋቹበት ጥርስ መሳቅን አይረሳም
ሳቁ
ብዙ ለማትኖሩት ለአጭር ዕድሚያቹ
ምን ቢከብድ እንኳን ይሳቅ ጥርሶቻቹ
መፍትሔ ባይሰጥም መላ ባያመጣ
ከተቋጠረ ፊት መሳቅ ነው ሚያዋጣ

ሳቁ😄

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


ጌጤ እና ሽጉጤ ቀናቸው ነው ዛሬ
ሲባባሉ ያድራሉ ሀኒ፣ ቤቢ ፍቅሬ
ጌጤም በመልኳ ላይ ሜካፗን ለቅልቃ
ችሎ ያኖራትን ሺቲዋን አውልቃ
የእራት ልብሷን ለብሳ ቀጭ ቋ እያለች
ከሽጉጤ ዕቅፍ ጠልቃ ትገባለች
.
ሽጉዬም ላመሉ ፀጉሩን አስፈርዞ
የኪራይ ሱፍ ኮቱን በእጁ ላይ ይዞ
እንደ ውጪዎቹ አበባ አንጠልጥሎ
ለአንድ ቀንም ቢሆን ድህነቱን ጥሎ
ቀፍሎ ባመጣው ኪሱን አሳብጦ
ጌጥዬን እያየ ይበላል አማርጦ
.
ተበላ ተጠጣ ፍቅራቸው ነደደ
ገና ነው እያሉ ሰዓቱ እረፈደ
በፍቅራዊ ቃና እየተገፋፉ
ለሊቱን አነጉት አልጋ ሲያነጥፉ
ለስራቸው ጥራት ለድካም ወዛቸው
ከወራት በኃላ ደሞዝ ደረሳቸው

ዘንድሮም ጠንክራቹ ስሩ💪



በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


አሁን አሁን ከሰው በላይ እንስሳ ያሳዝነኝ ጀምሯል. በእንደ እኛ ዓይነት ውለታ ቢስ ፍጥረቶች መሀል ተሰይመው መገኘታቸው በእራሱ ይደንቀኛል. እላይ እላዩን ሲታዩ ምንም ማያውቁ ምስኪን ማስተዋል የተሳናቸው ቢመስሉም ፤ ውስጥ ውስጡን ግን ብዙ የሚያውቁት ሚስጥር ያለ ይመስለኛል. በምድር ላይ የሚቆዩት ዕድሜ ማጠሩ ለምን ይሆን? የመኖራቸው ጥቅምስ ለኛ አገልጋይነት ብቻ ነው? ምን አልባት የሞኝ ሀሳብ ሊመስል ይችላል...ግን አስባቹታል? ከክርስቶስ ቀጥሎ ፍቅርን የት ታገኛዋለህ ቢሉኝ መልሴ ከሰው መሀል አይደለም. ከእነዛ ማውራት ከማይችሉ ነገር ግን ፍቅርን እንዴት መስጠት እንዳለባቸው ከሚያውቁ እንስሶች መሀል ነው. እንደ ሰው ዛሬ ወደው ነገ ማይጠሉ ናቸው. ፈጣሪ የፍቅሩን ተምሳሌት በእነሱ ውስጥ በምድር ያኖረ ይመስለኛል. እንስሳ ይባሉ እንጂ ከእኛ በዕጥፍ ዕጥፍ ይሻላሉ. ማሰብ አይችሉም ባዮቹ ማሰብ ካቆምን ዘመናት አልፎናል. ማሰብ አይችሉም ያልናቸው ማሰብ ከምንችለው በላይ ህይወትን የተረዱ ናቸው. እንደ እኛ መንታ ማንነት የሌላቸው ፤ ስሜታቸው፣ ንዴታቸው፣ ቁጣቸው ፊትለፊት ግልፅ የሆነ የማስመሰል ጥበብ የማያውቃቸው እውነተኛ ኗሪዎች. እንደ እኔ እንደ እኔ ከሰው በላይ ትልቅ ቦታ እና ትልቅ ክብር ይገባቸዋል ባይ ነኝ. ፈፅሞ ለእንደ እኛ ዓይነቱ ፍጥረት አይገቡም.

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


ዐይኔ አልታደለም ወግ ደርሶት ሊያነባ
ፈፅሞ አይፈልግም የሰው ሆድ ሊያባባ
በጥርሱ ይመክታል ሁሉን እያመቀ
ላነባለት ሁሉ ዕንባው መች ደረቀ


በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


ያልወረደ እንባ
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....

በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤

መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤

በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤

አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@Ebuh_bhr


አስታወሼ እኮ ነው
.
ስጠፋ ሚጨነቅ ስሸሸው ናፋቂ
በቀን ሶስት አራቴ አጥብቆ ጠያቂ
ማጣቴን ማይሻ ሲያልፍልኝ ደስተኛ
ስቸገር ስከፋ አለው ባይ መፅናኛ
ኖሮት የማይሰስት እጁን ሚዘረጋ
አለውልህ ባዬ በመሸ በነጋ
.
ለበዓል ስጦታ አስታውሶ ለጋሼ
ስንቱን ያሳለፍኩት እርሱን ተተርሼ
ቃላት የማይገልፁት ከቶ ማይተረጎም
ውለታው ብዙ ነው ኢትዮ-ቴሌኮም


ላንተ ቃል የለኝም....በተለይ 810🫶

በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


አላወራም የኔን ችግር
እንዲህ ሆንኩኝ እንዲያ እያልኩኝ
ለጠያቂው ፈገግ እያልኩ
አልፈዋለው እየሳኩኝ
.
የውስጤን ዐቅ ስሜቶቼን
አውጥቻቸው ብተነፍስ
አይዞህ በርታ እያለ ነው
የአድማጭ ጆሮ የሚመልስ
.
ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ
ላይሰማው የኔ ህመም
እንዲህ ሆንኩኝ እንዲያ ሆንኩኝ
በመናገር ለምን ልደከም?
.
ከንፈር መጦ ለሚያልፍ ሰው
ከመተረክ ከማውራቱ
"ደህና" ብሎ ማለፉ ነው
የሚበጀው በእውነቱ


በኪሩቤል አሰፋ

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr


ቴክስት ብልክልሽ
ዘመናት ቆይተሽ ኮርተሽ ስትመልሺ
ለሳምንት ስዘጋሽ
ሀኒ፣ቤቢ እያልሽ ስታለቃቅሺ
.
ዕርሜን የደወልኩ' ዕለት
ጥሪው ተመችቶሽ ደግመሽ እንዳልሰማሽ
የኔ ተራ ሲደርስ እንደው ምን ተሰማሽ?
.
አየሽ!!
የተጣለ ሁሉ ወድቆ ላይቀር ደርሶ
ምንም አይበጀኝም ያአንቺ ያሁን ለቅሶ
.
የተናቀ አስማጠ የተገፋም ወጣ
እኔም አልቀረሁም ይኸው ቀኔ መጣ


ይድረስ ላማረሩዋቹ ሴቶች🙌

በ ኪሩቤል አሰፋ


@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

453

obunachilar
Kanal statistikasi