የሟች ውንድምና እህት መቼ ነው ወራሽ ሊሆኑ የሚችሉት?
በኢትዮጵያ የውርስ ህግ ላይ የወራሾችን ቅደም ተከተል ሲደነግግ እና የሟች ወራሾች እነማን ናቸው ሲያስቀምጥ የሟችን እህት ወይም ወንድም የመውረስ መብትና ደረጃን በተዘዋዋሪ እንጂ በግልፅ አልደነገገም፡፡በኢትዮጵያ የውርስ ህግ ላይ የሟች ወንድም ወይም እህት ወራሽ ለመሆናቸው በፍ/ህ/ቁ 844(2) ላይ ከአባት ከእናት አስቀድሞ የሞተ ቢኖር የሱን ፈንታ ልጆቹ ወይም ሌሎች ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆቹ በሱ ተተክተው ይወርሳሉ ሲል የደነገገ ሲሆን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 10 በሰ/መ/ቁ 45587 ላይ የሟቹ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ የሟች ልጆች እንደሆኑ በፍ/ህ/ቁ 842 ስር በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከሌለ የሟች ንብረት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዘመዶች እንደሚተላለፍ እነዚህ ሁለተኛ ደረጃ ዘመዶች የሚባሉትም የሟች እናትና አባት መሆናቸውን የሟች አባትና እናት ሟችን ቀድሞ ከሞቱ የእነርሱ ተወላጆች ማለትም የሟች ወንድምና እህት እናትና አባቱን በመተካት በሟች ውርስ እንደሚካፈሉ የፍ/ህ/ቁ 843 እና 844 ድንጋጌዎች ይዘት የሚያሳይ ጉዳይ ነው ሲል ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡በመሆኑም በኢትዮጵያ ህግ የሟች ወንድም ወይም እህት ሟች ወንድማቸውን ሊወርሱ የሚችሉት አባት ወይም እናቱን ሲሞቱ በመተካት እንጂ በቀጥታ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግ ምክር #የኢትዮጵያ
#ethiopianlegalinsight
www.ethiopianlegalinsight.com
https://t.me/Ethiopianlegalinsight