ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አንድአንድ ባህሪያት
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀፅ 174 መሠረት ሰባት ዓይነት የንግድ ማህበራት ያሉ ሲሆን እነዚህም 1) የኃብረት ሽርክና ማህበር 2) ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማህበር 3) ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማህበር 4) የእሽሙር ማህበር 5) የአክሲዩን ማህበር 6) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 7) ባለአንድ ሰው አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው፡፡ እንደ አዲስ ከተካተቱት ሁለት ሲሆኑ እነሱም ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማህበር እና ባለአንድ ሰው አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው፡፡ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማለት አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማህበር ነው፡፡ማህበሩ ከአባላት የተለየ እና የተነጠለ የራሱ የህግ ሰውነት ያለው ነው፡፡ይህን ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልገው አነስተኛ ካፒታል መጠን ብር 15.000(አስራ አምስት ሺ ብር) ነው፡፡ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመሰረተው አባሉ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት በመቅረብ በሚሰጠው መግለጫ ነው፡፡ይህ መግለጫ መመስረቻ ፅሁፍን የተካ ነው፡፡አንድ ባለአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሌላ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሊያቋቁም አይችልም ይህን ተከላልፎ የተቋቋመ ማህበር ያገባኛል በሚል ሰው ጠያቂነት ሊፈርስ እንዲሁም በምስረታው ምክንያት እና በኃላ ለ3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት አባሉና ማህበሩ በአንድነትና በተናጥል ኃላፊ ይሆናሉ፡፡አንድ ግለሰብ ነጋዴ ወደ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መለወጥ የሚችል ሲሆን ግለሰቡ ማህበሩን ከመመስረቱ በፊት ለገባበት ዕዳ ሁሉ ከማህበሩ ጋር በአንድነትና በተናጥል ኃላፊ ይሆናል፡፡
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግ ምክር #የኢትዮጵያ
#ethiopianlegalinsight
www.ethiopianlegalinsight.com
https://t.me/Ethiopianlegalinsight