በአንድ መንደር ውስጥ ሥዕል እየሳለ በውድ ዋጋ በመሸጥ የሚተዳደር ሽማግሌ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን አንድ የመንደሩ ነዋሪ የሆነ የኔ ቢጤ መጣና "አንተ ሠዓሊ ነህ። ሥዕል
እየሳልክ ብዙ ስለምታገኝ ሀብተም ሆነሀል፤ ግን ለድሆች አትሰጥም፤ ባለ ልኳንዳ ቤቱ እንኳ ሁሌ ሥጋ ለድሆች በነጻ ያድላል።"
አለው ሽማግሌው ሠዓሊም ፈገግ ከማለት ውጪ ምንም መልስ አልሰጠውም . ድሀው ሰውዬም በመንደሩ እየዞረ ሽማግሌው ሀብታም እንደሆነና ግን ስስታም እንደሆነ አናፈሰ።
የመንደሩ ሰዎች አዛውንቱን ጠሉት . . ከጊዚያት በኃላ አዛውንቱ ታመመ። አንድ እንኳ የሚያስታምመው ሰው አጥቶ ሞተ . ከዚያን ቀን በኋላ ባለ ልኳንዳው ሥጋ ማደሉን አቆመ።
ለምን እንዳቆመ የመንደሩ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት . "እስከ ዛሬ የማድላችሁ እኮ ሠዓሊው ስለሚከፍለኝ ነው" ብሎ መለሰላቸው።
አንዳንዴ ነገሮችን ሳናረጋግጥ ለውሳኔ አንቸኩል!
@HTpsychiatrist