ለመገናኛ ብዙኃን በሙሉ
በሀገራችን አስገራሚ ታሪክ እየተሠራ ነው።
ድምጹን አጥፍቶ ሲሰራ የቆየው የጮቢ በዓታ ለማርያም ገዳም አስገራሚ ተግባራት ጊዜው ደርሶ ይሄውና ለአደባባይ በቅቷል።
በዓለማችን ላይ በሚገኙ ገዳማት ታሪክ ቁጥር አንድ የሆነና የ8 ፎቅ ያህል ርዝመት ያለውን ባለ44 ሜትር ስፋቱ ባለቅስት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን (Dome Type Church) ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀርቶታል። ቤተ ክርስቲያኑ ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ 21 ሽህ ምዕመናን ቆመው ማስቀደስ የሚችሉበት ነው።
ከዚህም የሚበልጥ ሌላ ታሪክም በዚህ ገዳም እየተሠራ ነው። በዓለማችን ገዳማት ታሪክ አሁን የመጀመሪያው የሆነና በትልቅነቱ ቅዱስ ጳውሎስ እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተደምረው የማይደርሱበት ባለ1000 አልጋ ሆስፒታል በ350 ሽህ ካሬ ላይ ሊገነባ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።
ስለዚህ ገዳም አኩሪ ታሪክ መስማት ስለሚገባችሁና ለሀገራችንም ሕዝብ ይህ ታሪክ መነገር ስላለበት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማክሰኞ መጋቢት 03/2016 ከቀኑ 8:00-11:00 ድረስ በዮድ አቢሲኒያ አዳራሽ ተገኝታችሁ እንድትገረሙ ጋብዘናል።
የሆስፒታል አሠሪ ኮሚቴ