#ቀን5/3/13ዓም የ1ኛ ሩብ አመት የአፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ ! ================®=============== ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ማለትም ከቀን 5-6/3/13ዓም ድረስ የቢሮውን የ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሙክታር ሳሊህ ሲሆኑ እሳቸውም እንደገለፁት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቢሮው ከባለፉት አመታት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያሰራ እንደሚገኝ አውስተው በተለይም በለፈው አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የገፅ ለገፅ የመማር ማስተማሩ ስራ ቢቋረጥም ቢሮው ከክልሉ መምህራን ጋር በመሆን በደረጉት ከፍተኛ ርብርብ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተማሪዎችን ለመርዳት ያደረጉት ጥረት አበረታች እንደነበረ ኃላፊው ገልፀዋል ፡፡ አያይዘውም ኃላፊው እንደገለፁት በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ኮሮናን እየተከለከልን የመምህርነትን ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ለማድረግ ቢሮው በልዩ ሁኔታ እንደሚሰራ ኃላፊው ገልፀዋል ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና የትምህርት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ2013ዓም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ፡፡
በውይይቱ ላይ በተለይም ኮሮናን እያተከለከሉ የመማር ማስተማር ስራውን የተሰለጠ ከማድረግ አንፃር መምህራን የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ ከቤቱ በሰፊው የተነሳ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በትምህርት ስርዓቱ ላይ የመምህርነት ሙያ ከምልመላ ጀምሮ የሚታየውን ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል ፡፡
መምህርነትን መርጠውና ፈልገው የሚመጡ ባለሙያዎች በሌሉበት የትምህርት ጥራትን ማሻሻል አስቸጋሪ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ሙያው የሚጠበቅበትን ተልዕኮ ለማሳካት የሙያው ባለቤት የሆኑ መምህራን በአግባቡ ሊሰለጥኑና የሙያውን ግዴታ መወጣት በሚያስችላቸው ደረጃ ሊዘጋጁ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
መምህርነትን ተመራጭ የሙያ መስክ ለማድረግ የመምህራንን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ፣ የስልጠና ስርዓቱን፣ የኑሮ፣ የስራና የገቢ ሁኔታን በማሻሻል የሙያውን ክብርና ደረጃ ማሳደግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
በመጨረሻም መምህራን አሁን የተጀመረውን የገፅ ለገፅ ትምህርት በቀጣይ በዘላቂነት ለማስቀጠል በሚደረገው ከፍተኛ ርብርብ ላይ ድርብ ሃላፊነት ያለበቸው በመሆኑ ከዚህ በፊት ትምህርት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተቋረጠበት ወቅት ተማሪዎችን በየቤታቸው ሆኖ ትምህርቱን እንዲከታተሉ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦና ርብርብ እንዳደረጉ ሁሉ አሁንም ዳግም ትምህርት በመከፈቱ ከዚህ በፊት የጀመሩትን ጉልህ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሮው ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል ፡፡