☞‹‹ሀብትን በትዳር ውስጥ ፈልጉ፡፡›› ኢብኑ
መስዑድ (ረደየላሁ.ዐንሁ.)
☞ ‹‹ ፍቅር ማለት በሀላል ተገናኝተህ
የምትመሰርተው ትዳር ውስጥ የምታገኘው
ምድራዊ ገነት ነው።››
☞ ቆንጆ ወንድ ማለት ራሱን (ከእይታ) ዝቅ
የሚያደርግ ነው! ቆንጅዬ እህት ማለት ራሷን
የጠበቀች ነች!
☞ ጥሩ(ሷሊህ) ሚስት የሚፈልግ ወንድም
እይታውን ሊሰብርና አደብ ሊኖረው ይገባል::
☞ በአንፃሩም ሷሊህ ባል የምትፈልግ እህት
ራሷን ልትጠብቅና ሀያእ ሊኖራት ይገባል
ማለት ነው::
☞ ሀራም የሆነ ፍቅር ልክ እንደ ጨዋማ ውሃ
ነው.. ምንም ያክል ከርሱ ብትጠጣ
አያስደስትህም፤እንዲያውም ጥማትህን
ይጨምረዋል።
☞ ‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ሰው በሚስቱ
መልካም አያያዝ በላጫችሁ ነው›› ረሱል
( ﺻـــــﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋــﻠﻴـﻪ ﻭﺳــﻠﻢ )
☞‹‹ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች፣
ጥሩዎቹ ወንዶቹም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ
ናቸው።››አል-ኑር፦ 26
☞ ‹‹ኒካህ በማሰር(ትዳር በመመስረት) አላህን
ታዘዙት፤ቃል የገባላችኁን ይሰጣችኋልና፡፡››
አቡበከር ሲዲቅ (ረደየላሁ ዐንሁ.)
☞ ‹‹ጋብቻ በኔ ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው፡፡
እኔ ለምወደው ነገር ጀርባውን የሰጠ ለኔ
ጀርባውን እንደሰጠ ነው፡፡›› ነብዩ ሙሀመድ
( ﺻـــﻠـــــــــى ﻋﻠـــﻴــﻪ ﻭﺳــــﻠﻢ )
☞ ‹‹ዲኑንና ባህሪውን (አኽላቁን)
የምትወዱለት ሰው ከጠየቃችሁ አጋቡት
( ካልሆነ በምድር ላይ ፈሳድ ጥፋትና ፊትናን
እያንሰራፋችሁ መሆኑን ተገንዘቡ)፡፡›› ነብዩ
ሙሀመድ ( ﺻــــﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠـــﻴـﻪ ﻭﺳــــﻠﻢ )
☞ ‹‹ከራሳችሁ የሆነችን ተጣማሪ ትረኩበት
ዘንድ መፍጠሩ በመሀከላችሁ ፍቅርና
መተዛዘንን ማድረጉ ከተዓምራት
አሉ፡፡››ሱረቱ ሩም 21
☞ ‹‹ሚስትህን ውደዳት፤ጊዜም ሰጥተህ
አስደስታት፡፡››
☞ ‹‹ግማሽ ዲንህን የሞላህበትን ቀን
መቼውም ቢሆን አትዘንጋ፤እሷ ሚስትህ ብቻ
ሳትሆን ከአራህማን የተለገሰችህ ንግስትህ
ነችና!!››
☞ ባልን ማክበር እና መታዘዝ የአላህን እና
የረሱልን ( ﺻـــﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴــﻪ ﻭﺳــﻠﻢ ) ትእዛዝ ከመጠበቅ
ይቆጠራል፡፡📲
https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa