ሞሮ
ክፍል 20
ሰምሃል ኤቤጊያን በጥፊ አጮለቻት ኤቤጊያ ይበልጥ ደንግጣ ጉንጯን እያሻሸች ምን አረኩሽ ሰሙ አለቻት። ሰሙ....ሙ አትበይኝ አንቺ ደደብ ነሽ ማፈሪያ! እንደሰው እሚያስብ አእምሮ ቢኖርሽ እንዲ እሚያሳፍር ነገር ባላደረግሽ ነበር ከዚ በኃላ ቀና ብለሽ እንዳታዪኝ አጠገቤ እንዳትደርሽ እኔ ከእንዳንቺ አይነቱ የቀለለ ስብእና ያለው ሰው ጋር ጓደኛ መሆን አልችልም አለቻትና እየደነፋች ወደኔ ዞራ ይዛኝ ልትሄድ ስትል ኤቤጊይ እጇን ያዘቻትና የምርሽን ነው ብላ ጮኀች አንድ ወር ለምታውቂው ሞሮ ብለሽ የአመታት ጓደኛሽን ልትጣዪ ነው አረ ይደብራል ሼም ነው! ኤቤጊያ ይህንን ስትል ሰምሃል ወደኔ ዙራ ነበር ሞሮ ስትላት ንዴቷ ጣራ ሲነካ አይቼ እኔ እራሱ ፈራኃት። ወደ ኤቤጊያ ዞራ እጇን መንጭቃ አስለቅቃት ሞ...ሮሮሮ አትበይውውውውው!! አንቺ ቀላል ብላ ጮኀችባት ሁሉም ሰው ድምፁን አጥፍቶ ድራማውን በተመስጦ ይከታተላል ሰምሃል እየተንቦገቦገች ወደ ኤቤጊያ ስትጠጋ ራስታው ልጅ መሃል ገብቶ ገላገላት ዞርበል አንተ ብላ ገፈተረችው ራስታው ልጅ መሬት ላይ ወደቀ ኤቤጊያ እየተናደደች ምንድነው ቆይ ችግርሽ በጣም ነገሩን አካበድሽው አለቻትና ራስታውን ልታነሳው ስትል ሰምሃል የብሽቀት ሳቅ እየሳቀች አንቺ መልካም ስብእና ስለሌለሽ መልካም ሰው ምን አይነት እንደሆነ አታውቂም ከስብእና ይልቅ ዘናጭ እና አጉል አራዳ ነኝ እሚል መወልወያ ራስ ነው የሚመችሽ ስትል ሁሉም ተማሪ ራስታውን እያዪ እንደጉድ ሳቁበት ኤቤጊያ ይበልጥ ተቃጠለች እሱን እዚ ውስጥ አታስገቢው እኔ... ሰምሃል እስክትጨርስ አልጠበቀቻትም አንቺ የጠበሽው ራስታ እሚወድሽ ይመስልሻል ደና ስሜቱን እሚወጣብሽ ርካሽ ሴት ነሽ አደለም አንቺን እኔንም ጠይቆኝ.... ብላ ድንገት አቆመችውና ተይው በራስሽ ግዜ ታይዋለሽ ብላት አፏን አሲዛት ወደኔ ዞራ እንሂድ ብላኝ የተሰበሰበው ሰው እየሳቀ ከኪያር ጋር ሶስታችንም ጥለናቸው ሄድን።
ሰምሃል አሁንም ንዴቷ አለቀቃትም
እኔም ኪያም ዝም ብለን አብረናት እንሄዳለን አምፊ አከባቢ ስንደርስ ወደኪያር ዞረችና ኪዩ አንዴ ናዲን ስለምፈልገው አንተ ወደ ዶርም ሂድ እሱ ትንሽ ቆይቶ ይመጣል አለችው ኪያር ስለፈራት እሺ ብሏት መሰስ ብሎ ከአምፊ አከባቢ ጠፋ ደረጃዎቹ አከባቢ ስንደርስ ቆምን ተቀመጥ! አለችኝ ንግግሯ ውስጥ አሁንም ንዴት አለ ምንም ልላት ስላልፈለግኩ እሺ ብያት ስልልም ብዬ ደረጃዎቹ ላይ ቁጭ አልኩ እሷ ደረጃዎቹን ቀስ እያለች ወርዳ ከፊቴ ዝም ብላ ቆመች። በእግሯ መሬቱን ተጠበጥበዋለች ራሷን በሁለት እጇ ትይዘዋለች ግራ ተጋባው ሰሙ ይሄን ያክል ምን ሁና ነው እኔ የማላውቀው ሌላ ፀብ አላቸው እንዴ? ራሴን ጠየቅኩ። ድምፄን ለስለስ አድርጌ ሰሙ ቆይ ምን ሆነሻል በጣም ተናደድሽ ብዙም እሚያናድ ነገር እኮ አልነበረም አልኳት። ሰምሃል አይኗን እኔ ላይ ይበልጥ አጠጠችው ወዲያው ምን ልትለኝ እንደሆን ገምቼ ባላወራው ይሻለኝ ነበር ብዬ ተፀፀትኩ። አንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንደዚ እምትሆነው ትንሽ ለራስህ እንኳን ክብር አይኖርህም! አይሰማህም! ያሃ ሁሉ ሰው እየተሳለቀብህ አፈቅራታለው እምትላት ሴት እንኳን በአደባባይ እያዋረደችህ ትንሽ አይሰማህም እስከመቼ ነው እንዲ እምትሆነው እራስህን አስተካክል እንጂ ሁለት አመት በሷ ያቃጠልከው ቀላል ይመስልሃል ሁለት አመት የማትመጥንህን ሴት ስትጠብቅ ጀዝበህ ቀረህ ግቢው ሙሉ ጀዝባ! ሞሮ! ሲልህ እንኳን አትነቃም አይሰማህም ቀና ብለህ እየኝ ምን ታቀረቅራለህ ብላ ጮኀችብኝ። ምንም ልናገራት አልቻልኩም ግቢው ሙሉ ጀዝባ ሲለኝ ሞሮ.እያለ ሲያላግጥብኝ በጣም ከመደነዜ የተነሳም ምንም አይሰማኝም ነበር። ሰምሃል በረጅሙ ኡፍፍፍፍ.... ብላ በረጅሙ ተነፈሰችና ራሷን ለማረጋጋት ከስሬ ካለው ደረጃ ላይ ቁጭ አለች የተወሰኑ ደቂቃዎች በዝምታ አለፉ። ሯሷን በደምብ ካረጋጋች በኃላ ይቅርታ ናዲ ትንሽ ስሜታዊ ሆኜ ተናገኩህ ትንሽ ተናድጄ ስለነበር ነው ነገ በጥዋት ላግኝህና እናውራለን እንዳትቀር እሺ ማውራት ያለብን ጉዳይ አለ ብላኝ ቻው እንኳን ሳትለኝ እዛው አምፊ ደረጃዎች ላይ ጥላኝ ሄደች። እኔም ትንሽ ተቀምጬ በሰመመን ሆኜ ካሰብኩ በኃላ እስከመቼ? ብዬ ራሴን ጠየቅኩ እና መልስ ከማንም ሳልጠብቅ ወደ ዶርም ልሄድ ተነሳው።
ይቀጥላል ....
https://t.me/New_life_20