15ኛው የኦሮሚያ ባንክ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በፊንፊኔ ሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄደ።
ኦሮሚያ ባንክ በተግዳሮት በታጀበ የባንኪንግ ኢንደስትሪ ዉስጥ የማይዋዥቅ የላቀ የአገልግሎት ማዕከልነቱን አስጠብቆ ቀጥሏል፡፡
ዘንድሮ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች የባንኪንግ ዘርፉን በተለያየ መልኩ ቢፈትኑትም፤ ኦሮሚያ ባንክ ለፈተናዎቹ ሳይበገር በዋና ዋና ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ዉጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ በተለይም የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ እጥረት የሀገራችንን ባንኮች በከፍተኛ ሁኔታ ቢፈታተንም፤ ኦሮሚያ ባንክ ፈተናዎቹን ተቋቁሞ ጥራት ያለዉ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የላቀ የአገልግሎት ማዕከልነቱን አስጠብቆ ቀጥሏል፡፡ ባንካችን በተለይም አለም አቀፍ ንግዱን በማሳለጥ በገነባዉ መልካም ስም እና ዝና ኮረስፓንደንት ባንኮች እና በበርካታ ደንበኞቻችን ዘንድ የመጀመሪያ ምርጫ መሆን ችሏል፡፡
ኦሮሚያ ባንክ 3.7 ሚሊዮን የዲጂታል ባንኪንግ አግልገሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ማፍራቱን አስታወቀ፡፡
ባንካችን የመጪዉን ዘመን የባንክ ኢንደስትሪ በመረዳት እንዲሁም እያደገ የመጣዉን የደንበኞቻችንን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ፍላጎት ማዕከል በማድረግ ኦሮዲጂታል ተሰኘ እጅግ ዘመናዊ ሱፐር አፕ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት በማስተዋወቅ እና ስራ ላይ በማዋል፣ በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት ብቻ ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራት ችሏል፡፡ በዚህም አጠቃላይ የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ከባለፈው ተመሳሳይ የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ157 % ከፍተኛ እድገት አሳይቷል። ይህ ቁጥርም በኢንደስትሪ ዉስጥ ኦሮሚያ ባንክን በርካታ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ካላቸዉ ጥቂት ቀዳሚ ባንኮች ተርታ ያሰልፈዋል፡፡
ኦሮሚያ ባንክ ዘመን ተሻጋሪ ሜጋ የፕሮጀክት ኢንቨስትመንቶች በስፋት እያካሄደ መሆኑን ገለፀ፡፡
በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት ከባንካችን ቀዳሚ ስኬቶች መካከል ባንኩ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ በማፍሰስ እያካሄዳቸዉ የሚገኙ ዘመን ተሻጋሪ ሜጋ የፕሮጀክት ኢንቨስትመንቶች በጉልህ ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
ለአብነት ያህል በመሃል ፊንፊኔ ጎማ ቁጠባ አከባቢ የፊኒሺንግ ስራው እየተቀላጠፈ የሚገኘው፤ ባለ 35 ወለል የኦሮሚያ ባንክ የሽግግር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ይገኝበታል፡፡ ይህ የባንኩ የሽግግር ዋና መስሪያ ቤት ግዙፍ ህንፃ፤ በ2200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን ከአጠቃላይ ሥራው 32 በመቶ የሚይዘው የኮንክሪት ሙሌት ስራዉ ከጥቂት ወራት በፊት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ፤ የፊኒሽንግ ስራዉ 20 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 52% ላይ ደርሷል። ህንፃዉ በያዘዉ ገዢ ቦታም ለባንካችን ተጨማሪ አዲስ ከፍታ፣ ለከተማችን አዲስ የእይታ አድማስ እና ዉበት፣ ለሀገራችን ተጨማሪ ኩራት ነው ተብሏል።
ሌላኛዉ ሜጋ ኢንቨስትመንት በባንካችን እየተገነባ የሚገኘዉ በ20 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈዉ የገላን የልህቀትና ኮንቬንሽን ማዕከል (Gelan Excellence and Convention Centre) ይገኝበታል። የማዕከሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ፤ የሁለተኛዉ ምዕራፍ ባለ B+G+9 ወለል ግዙፍ ሁለገብ ህንፃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ ነው 40 በመቶ ላይ ደርሷል።
ለአምስት ዓመታት በፍርድ ቤቶች ሲጓተት የከረመዉ ሰንጋተራ አከባቢ የሚገኘዉ የመጪዉ ዘመን የባንካችን የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ ቦታ መቋጫ አግኝቶ የመሬት ማረጋገጫ ካርታ የወሰድንበት ዓመት ነዉ፡፡ ይህም በቀድሞ ስሙ ሎምባርዲያ በመባል የሚታወቀው ቦታ ባንካችን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተረክቧል፡፡
ኦሮሚያ ባንክ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን የ1.4 ሚሊዮን ተጨማሪ አደዳዲስ ደንበኞች ማፍራቱን
አስታወቀ፡፡
በእስትራቴጂካዊ የማስፋፊያ እርምጃ የባንኩን የደንበኞች መሰረት እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽነታችንን ለማሳደግ ባንካችን ባለፈዉ የበጀት ዓመት 73 ተጨማሪ ቅርንጫፎች የተከፈቱ ሲሆን በአጠቃላይ የቅርንጫፎቻችንን ብዛት 575 በማድረስ ከዕቅድ በላይ አሳክቷል።
ባንካችን ኦሮሚያ ባንክ በየጊዜዉ የአግልግሎት ማሻሻዎች በማድረግ ደንበኛን ማዕከል ያደረጉ እና ዘመኑን የዋጁ የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የደንበኛ መሰረት ስፋቱ በየዓመቱ እያደገ ይገኛል፡፡ በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት ከባንኩ ስኬታማ ተግባራት መካከል 1.4 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞች ማፍራት በቀዳሚት ይጠቀሳል፡፡ ይህም አጠቃላይ የባንኩን የደንበኛ መሰረት ብዛት ወደ 6 ሚሊዮን የሚጠጋ ያደርሰዋል፡፡
ኦሮሚያ ባንክ ቀጣይነት ያለዉ እና ጤናማ ተቋም በመገንባት ሂደት ስኬታማ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የባንካችን ልዩ መለያ እና መወዳደሪያ በመሆን የሚታወቀው ተቋማዊ ጤንነታችን ዘንድሮም እንደወትሮው በተሻለ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ በበርካታ ተግዳሮቶችን አስተናግዶ በተጠናቀቀው የበጀት አመት የባንካችን የተበላሸ ብድር (NPLs) 2.26% የነበረ ሲሆን፤ በዕቅድ ተይዞ ከነበረው የ3.00% አፈፃፀም እንዲሁም ከኢንደስትሪው አማካይ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ጋር ሲነፃፃር የተሻለ አፈጻጸም አሳይቷል። ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የተሻለ የብድር ጥራት ካላቸው ቀዳሚ ባንኮች ተርታ ያሰልፈዋል፡፡