ለትግራይ ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ዱቄት ተልኳል ?
በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መቐለ "ማይወይኒ" መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ከቀናት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የስንዴ ዱቄትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበት ቀን የታተመበት አጠራጣሪ ዘይት 'ቀይ መስቀል' አቅርቧል በሚል እንደማይጠቀሙ ገልፀው ነበር።
የቀይ መስቀል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን አሊ ፥ በመቐለም ሆነ በሌላ የትኛውም አካባቢ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት ምግብ እንደላቀርቡ እና እንደማያቀርቡ ገልፀዋል።
የጥርጣሬው መነሻ የሀገሪቱ ስንዴ አምራች ኩባንያዎች የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበትን ጊዜ ማሸጊያው ላይ የሚያትም ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ቀይ መስቀል ያቀረበው ስንዴ እና ዘይት የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት አይደለም ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን #ለቪኦኤ ፦
"የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን በአ/አ እና መቐለ ባለው ተረጋግጧል። እነዚህ ምልክቶች በወረቀት ተለጥፈው ነው የሚሄዱት እነዚህ ምልክቶች የሚያሳስቱ መስሏቸው ስለተጠራጠሩ አንወስድም ፤ ይሄ ተለጥፎ ነው የመጣው፤ ቀኑም ልክ አይደልም ብለዋል።
የእኛ ሀገር ዱቄት ይሄን ሁሉ መንገድ አጓጉዘን፤ ዱቄቶቹ ከቃጫ የሚሰሩ ናቸው ከማሌዢያ ወይም ከፊሊፒንስ የሚመጡ አይደለም ፤ እነዚህን ሲያዩ አንዳንድ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እነዚህን ነገሮች ተጠራጥረዋል።
መጠራጠራቸውን ትክክል ነው ፤ እነዚህ ነገሮች ይታዩ ፤ ይፈተሹ ተባለ ፤ ናሙናው ተወስዶ ታዩ ዱቄቱ በሙሉ ንፁህ ነው ፤ ለምግብነት መዋል ይችላል የሚል የፅሁፍ ማረገገጫ ነው ያገኘነው።
ዘይቶቹ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚያገለግሉ ዘይቶች ናቸው። ነገር ግን ምርመራ ሲደረግ የአዮዲን መጠናቸውን አነስተኛ ሆነው ነው የተገኘው"
ያንብቡ : telegra.ph/ERCS-05-05
@tikvahethiopia