♦ የዳን 7 ማብራሪያ
እንደሚታወቀው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመላው ብሉይ ኪዳን የተተነበየለት ጌታ ነው። ሉቃ 24:44
ከነዚህ ትንቢቶች ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው ዳን 7 ነው። ይህ ክፍል የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በማያሻማ መልኩ የሚመሰክር ሲሆን እግዚአብሔርም ከአንድ በላይ አካል መሆኑን በግልጽ ይናገራል።
➡ ይህንን ትንቢት ልዩ የሚያደርገው፥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተሰጠው ወሳኝ ገለጻ ነው።
(ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 7)
----------
13፤ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ #የሰው #ልጅ የሚመስል #ከሰማይ #ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
14፤ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ #ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።
▶ በዚህ ስፍራ ነብዩ ዳንኤል አንድ የሰወ ልጅ በደመናት ላይ ሲመጣ ይመለከታል። ይህም የሰው ልጅ በዘመናት ወደ ሸመገለው ይመጣል። የማይጠፋ ግዛትና የህዝብ ሁሉ መገዛት ለእርሱ ይሆናል
🚩 በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት ዋና ነጥቦችን እንመለከታለን
1. ይህ የሰው ልጅ በደመናት ላይ ይመጣል
ይህ የሰው ልጅ ፍጡር አለመሆኑን የምናረጋግጥበት አንደኛው ነጥብ በደመናት ላይ ይሄዳል መባሉ ነው።
የዳንኤል መጽሐፍ በተጻፈበት ዘመንና አውድ በደመናት ላይ ይሄዳል የሚባለው አምላክ ነው ተብሎ የታሰበ ነገር ብቻ ነው። አምላክ ተብሎ ላልታሰበ ነገር ይህ መዓረግ አይሰጥም
" ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን #ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 19:1)
ተጓዳኝ ጥቅሶች፦ ዘዳ 33:26 መዝ 68:33 ናሆ 1:3
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ መዓረግ ተሰጥቶ የምንመለከተው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። በጥንቱም ዘመን የነበረው ማህበረሰብ በደመና ላይ ይሄዳል የሚለው አምላኩን ብቻ ነው
ለዚህ ምሳሌ የጥንት ከነዓናዊያን ለቤል የሰጡትን መዓረግ እንመልከት
" what manner of enemy has risen against #Baal, of foe against the #charioteer of the #clouds? "
(Religious Texts from ugarit, 2nd edition)
እንደሚታወቀው ቤል ለከነዓናዊያኑ አምላክ ነበር። ለዚያም ነው በደመናት ላይ ይሄድ ነበር የሚሉት። ቅዱሳን በደመና ላይ የሚሄደው ያህዌ ነው ሲሉ እውነተኛው አምላክ ያህዌ እንጂ ቤል አለመሆኑን እየተናገሩ ነው (ኤር 50:2)
በዳን 7 ላይ ይህ የሰው ልጅ በደመናት ላይ ይሄዳል መባሉ መለኮት መሆኑን በማያሻማ መልኩ ይገልጻል። ነገር ግን ከዚህም በላይ የሚገልጸው ነገር አለ። ይህ የሰው ልጅ የሄደው በዘመናት ወደ ሸመገለው ነው። በዘመናት የሸመገለው ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
▶ በደመና ላይ መሄድ የመለኮት ማዕረግ ብቻ ከሆነ፥ ይህ የሰው ልጅ እንዴት ወደ እግዚአብሔር መጣ ተባለ?
እንዲህ ሊባል የቻለው እግዚአብሔር ከአንድ በላይ አካል በመሆኑ ነው። ለዚህም ነው አንዱ አካል ወደ ሌላው መጣ ሊባል የቻለው
በዳን 7 ላይ የምንመለከታቸው አካላት ሁለት የተለያዩ መለኮታዊ አካላት መሆናቸውን ክርስቲያን ያልሆኑ አይሁዳውያን ሊቃውንት አምነዋል
" Daniel 7 describes a heavenly enthronement scene involving two divine manifestations, The Son of Man and The ancient of Days...It may easily be describing two #separate divine figures. "
( Two Powers in heaven, Allen F. Segal )
♦ ይህ የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በምን እናውቃለን?
ይህ የሰው ልጅ ጌታ መሆኑን የምናውቅባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። አንደኛው፥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ክርስቶስ ራሱን "የሰው ልጅ" በማለት ስለሚጠራ ነው
ነገር ግን ጌታ ራሱን የዳን 7ቱ የሰው ልጅ መሆኑን የምናውቀው በራሱ አንደበት ስለተናገረ ነው።
(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 14)
----------
62፤ ኢየሱስም። እኔ ነኝ፤ #የሰው #ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ #በሰማይም #ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።
63፤ ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና። ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል?
64፤ #ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ። ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት።
▶ በዚህ ስፍራ ኢየሱስ ለሊቀ ካህናቱ እሱ በደመናት ላይ የሚመጣው የሰው ልጅ መሆኑን ሲነግረው እንመለከታለን። ያንንም ክፍል ከመዝ 110 ጋር ያገናኘዋል
ከዚያም ሊቀካህናቱ የሰጠው ምላሽ አስገራሚ ነው። ልብሱን በመቅደድ ክርስቶስ የተናገረው ስድብ (Blasphemy) ነው አለ
በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አንድ ሰው blaspheme አደረገ የሚባለው ራሱን አምላክ ካደረገ ነው።
" አይሁድም። ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ #ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን #አምላክ ስለ #ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።"
(የዮሐንስ ወንጌል 10:33)
በዮሐ 10:33 እና በማር 14:64 #ስድብ የሚለው የግሪክ ቃል አንድ ሲሆን አውዱም ተመሳሳይ ነው። አይሁድ ራሱን አምላክ አደረገ በማለት ከስሰውት ስለነበር ነው ስድብ ተናገርህ ያሉት
🚩 በማር 14:64 ግን ጌታ ያለው እኔ የዳን 7 የሰው ልጅ ነኝ ነው። ሊቀካህናቱ ግን እንደ ስድብ አየው። ይህ በእርግጥም የዳን 7 የሰው ልጅ አምላክ መሆኑን ያመለክተናል
ጌታ ያን የሰው ልጅ ነኝ ሲለው ሊቀካህናቱ "እግዚአብሔር ነኝ" ማለቱ እንደሆነ ተረድቶ ልብሱን በመቅደድ ስድብ ነው አለ።
▶ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በደመናት ላይ ይሄዳል የተባለው የሰው ልጅ በመሆኑ እግዚአብሔር መሆኑን እናረጋግጣለን
ሁለተኛው ነጥብ ፦
" ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ #ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። "
(ትንቢተ ዳንኤል 7:14)
በዚህ ስፍራ በሰማይ ደመና ይመጣል ለተባለው የሰው ልጅ አህዛብ፥ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ይገዙለታል
ቃሉን ስንመረምር አሕዛብ ሁሉ ለእግዚአብሔር እንደሚገዙ እንረዳለን። ይህ በደመናት ላይ የሚመጣው የሰው ልጅ መለኮት መሆኑን አመላካች ነው። መዝ 72:11 መዝ 102:22 መዝ 22:27 መዝ 86:9
ነገር ግን በትክክል ይህ የሰው ልጅ መለኮት መሆኑን የምናረጋግጠው ለእርሱ በዋለው ቃል ነው።
#ይገዙለት ተብሎ የተተረጎመው የአረማይክ ቃል (ፒላኽ/פְּלַח) ለእግዚአብሔር ብቻ የሚውል የአምልኮ ቃል ነው።
ለምሳሌ
" የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ፥ ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉት፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም። ሁልጊዜ #የምታመልከው አምላክህ እርሱ ያድንህ አለው። "
(ትንቢተ ዳንኤል 6:16)
በዚህ ስፍራ #የምታመልከው የሚለው ቃል በዳን 7:14 ላይ ለሰው ልጅ የዋለው ቃል ነው። ሌላ ምሳሌ
" #የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!"
(ትንቢተ ዳንኤል 3:17)
▶ ይህ ቃል መለኮት ላልሆነ ለሌላ ነገር ከዋለ ጣዖት አምልኮ ነው
" ናቡከደነፆርም። ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ፥ አምላኬን #አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለ