📚IBNU_FARIS PAGE📢


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


👉ይህ ቻናል በالله ፍቃድ ሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ያሉ ዕንቁ የሱና ዱዓቶች ትምህርትና የተለያዩ ምክሮች የሚለቀቅበት የሆነ ቻናል ነው::
[ሒዳያ በالله እጅ ነው! የኛ ግዴታ ማመላከት ነው!!
(📚ወደ ፊት ነው እንጂ የለም ወደ ኃላ!
መማር ማስተማር ነው አንፈልግም ሌላ!!📢
ሃሳብ አስተያየትዎን በዚህ ያጋሩን✍️
@Abu_Fawzan_ibn_Faris

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


,,,,,,,,,,,,,,,,,  ያ ፌስቡክ ተበን ለክ!
ቤንዚል  እሳት ሆኖ          በአረቡ ፀደይ
ግብፅን ሲያንገዳግድ  ሊቢያን ሲያደበይ
እንዳሻው ሲፈነጭ    የለ ማንም ሃይ ባይ

ሶሪያ ስትወድም      ሲታይ ፍርስራሿ
ሰው እንደጉድ ሲፋጅ   እዚም በሀበሻ
ነበረው ለፌስቡክ   የአንበሳው ድርሻ

ልብ ሚቆረቁር      የሚነካ ስሜት
ቆዳ ስጋ አልፎ  ሚሰማ ባአጥንት

ሰኢዱና እያሉ       ሲቆሙ መስጅድ ደጅ
እዚ እስኪደርሱ      አለበት የሱ እጅ        

በኢሞ በቫይበር   በቲክቶክ በዪቱብ
ህሊና ነጥቀው        እያደሉ ገንዘብ
              ይሸነግሉናል፤
    እንዳገለገሉን   እንደቆሙልን ዘብ

ሶሻል ሚድያው መጥቶ   ልክ እንደተስፋፋ
    ሞራል ዳሸቀና        ስነምግባር  ከፋ
    ሃያ ቁጥብነት           የነበረው ጠፋ

ሲታይ በጥቅሉ           ሲወራ በአለም
ደግ ክፉ  አለው       ወሳዒለል ኢዕላም
ይመቻል ይባላል   ሊስፋፋበት ኢስላም
               
#ግን
እውቅና ተሰጠው      ፋሂሻ ገነነ
የእውቀት ባለቤት   ሷሊሁ አዘነ
ከመልካሙ ይልቅ   ክፋቱ መዘነ

ኢሀው ጎነጎነ     ሞራል ዐልባ ወጣት
ደዩሱ የማይነቃ     ገይራው የሞተበት
ካልሆነ በስተቀር         አሏህ ያዘነለት

በምን አይነት ቀመር ምን አይነት ፍብረካ
ድንቅ ይላል ዘዴው      አውሮፓን አይነካ
ወዳጆቹ ናቸው         ሙሰሊምና አፍሪካ

የተሻለ እናምጣ   ዘር ህዝብህ ተጎዳ
በተነስ  መፈክር  በፌስቡክ ግርግዳ
ስንቶቹ ታገቱ        የማይከፍሉት ዕዳ

ሰንቶቹን በላቸው        ሞትና ቸነፈር
በዚህ በጉደኛ   ማይዳስሱት ፍጡር
ስንቶቹስ ተፋቱ         ከሰመረ ትዳር
ልጆች ተበተኑ    ወደቁ መንገድ ዳር

በፍቅር ለምልሞ የአበበው ጎጆ
ካናቱ ተናደ       ጥላቻን አውጆ

ስንቶችንስ ጥቡቅ አስተምሯል ዚና
ስንቱንስ ውዳቂ      አጎናፅፏል ዝና

ጉዳዩም አይደለ       ቢናቅ ወይ ቢደነቅ
የትላንት አልበቃው        ያ ሁሉ ትንቅንቅ
ይህ ጉደኛ ፍጡር     መቼ አረገን  ለቀቅ
ዛሬም ይጓተታል     ወንድሞችን ሊነጥቅ

እየመላለሰ             ካንዱ ጫፍ ከዐለም
አለ በዚህ ዘመን?   እንደ ፌስቡክ ነማም
ወዳጅ ሚቆራርጥ         ደረሳን ከኢማም

እህህ ነው እንጂ          ቢፃፍ የማይወጣ
ክፍት ነው ሊያጋነው  ፔጅ ከፍቶ   ለመጣ
እኩል ነው በፌሱ            አንበሳና ጦጣ

አንበሳው ቢያምር  ጦጣው እያስጠላ
ቁስል አመርቅዞ     ስንት ወደጅ ነጠለ
               
#ፌስቡክ
ከተሰፈረብህ    የተወህ አረፈ
ከባህር አረፋ     ክፋትህ ገዘፈ

ቀን ሙሉ ቢጥዱህ     ሳይተው ለሰኣት
ደረሳክ ተኩኖ       ቢያልፉ     አመታት
አሊም ማታፈራ    መምህር ነህ  ክፋት
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
በአህለ ሱና መኃል    ገብተህ እያሻከርክ
የሀገራት ሰላም             እያየን  ስታውክ
እንዴት እናወድስ          ይወራ  ለኸይርክ
ከደረስከው አንፃር   ያ ፌስቡክ ተበን ለክ!

                   ኢብን ሙዘሚል
                 ዙልሂጃ 05/1443  
t.me//ibnmuzemil


ወደ ስልጤ ዞን የተሰማው ጉድ ጴንጤዎች❌

ጴንጤና ስልጤ

ክፍል አንድ

❌የስልጥኛው መዝሙር ለጥንቃቄ እና ሰዎች ለማስጠንቀቅ አዳምጡትና ተጠንቀቁ አስጠንቀቁ❌❓

ከሄራታጆ የፌስቡክ ገፅ ከስልጥኛ ወደ አማርኛ በከፊል የተተረጎመ።

ከሄራታጆ የተወሰደ ድምፅ ወደ ፅሁፍ በትርጉም እሺ እንቀጥል። ተናጋሪው ያየውና የታዘበው እንዲህ ሲል ይጀምራል፦

ባቢሎ፣ጎልቦ፣ደንጋውርም፣ጋጅን ሴጦ፣ጃረሞ፣ለተሞ፣መናጂና፣ሱሉሎ፣ባጂዶ፣ጅሮ፣የለምበኢዶ በነዚህ አካባቢ የምትኖሩና ባጠቃላይ ከምእራብ አዘርነት በርበሬ ከሙጎ እስከ ሌራ ያላችሁ በሙሉ ሴቶቻችሁም ወንዶቻችሁም ታናሽ ታላቆቻችሁም አንድ ግዜ ስሙኝ (ይለናል) ።
የገጠመው አንገብጋቢ ገጠመኝ ለሰው እያሳሰበና እያስጠነቀቀ።
ማስጠንቀቁ ቀጥሏል። እንዲህም አለ፦

ከሌራ ቡጊን በሚባል አካባቢ ከ20 የሚልጡ የሙስሊም ወጣቶችን ጴንጤዎች ዩኒፎርም ልብስ፣ብር፣ደብተር ሰጥተው አክፍረዋቸው ነበር።በሌራ ሙሀባ የሚባል ሰው እናቱ ሞተው በነበረበት ጊዜ የዚያን ቀን ነገሩ ተወርቶ ለወጣቶቹ(ለልጆቹ) የተሰጣቸው ደብተርም ልብሶቹም እንዲመጣ ተደርጎ ተሰብስቦ ተቃጥሏል።

ተናጋሪው የዛሬ ሳምንት እራሴ አይቻለሁ ይላል። ተናጋሪው ማስጠንቀቁን ቀጠለ እንዲህም አለ፦
ልጆቻችን በልብስ በደብተር በብር እየተነጠቅን ነው ።

በሬ ያጣ በሬ ይገዛለታል፤ ላም የሌለው የወተት ላም ይገዛለታል ።ቤት የፈረሰበት ቤት ይሰሩለታል። ልጁንም ማስተማር ያልቻለው ዩኒፎርም ደብተር እንገዛልሀለን ብለው እያከፈሩት ነው።

የተናገሪው ንግግር አላለቀም ከታች ባለው
ይቀጥላል

አምቤው በል❗️

👉እባካችሁ ሼርና አድ በማድረግ ሙስሊሞችን ከጀሀነም ጓዶች እንታደግ።


على هامان يا فرعون؟؟
ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ…

«ፊርዓውን ከነበረበት ድንበር ያለፈ ጥመት ጋ ጅል (ፋራ) ነገር ነበር አሉ። አማካሪው ሃማን ደግሞ እንደ የትኛውም የንጉሶች አማካሪ ብልጣብልጥ ነበር አሉ። እናም ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት በፊርዓው “የጌትነት ሙገታ” ያመነች አሮጊት ፍየልዋ ይሞትባትና ወደ ፊርዓውን ቤት ትመጣለች።

ስትመጣ ፊርዓውን አልነበረም ሃማንን አገኘችው።
"ጉዳይሽ ምን ነበር?" ሲላት
"ፍየሌ ሞታብኝ ፊርዓውን ሕያው እንዲያደርጋት ነበር የመጣሁት።" ትለዋለች

ሃማን ብልጥ ነበር;  ብለን የለ?
"ነይ በቃ ፊርዓውን አሁን ግመል እየፈጠረ ስለ ሆነ ይቆይብሻል። ስለዚህ ሌላ ፍየል ልስጥሽ።" ይላትና ሌላ ፍየል ሰጥቷት ትሄዳለች።

ፊርዓውን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሃማን "አንዷ አሮጊት ፍየሏ ሙቶባት ሕያው እንድታደርግላት መጥታ ነበር።" ሲለው ፊርዓውን ደነገጠ።

ሃማን "አይዞህ! ፊርዓውን ግመል እየፈጠረ ነው። ብያት ሌላ ፍየል ሰጥቻት ሄዳለች። አትመጣም።" አለው።

በዚህ ጊዜ ፊርዓውን እንደ መረጋጋት አለና በረጅሙ ተንፍሶ…………
  «ግመል መፍጠር እኮ እንዴት እንደ ሚያደክም ብታይ» አለው።


ሃማን ፈገግ አለና… …
     على هامان يا فرعون
ኧረ ፊርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው

በሃማን ላይ ሙድ ትይዛለህ ወይ እንዴ ጭራሽ ልትሸውደኝ ያምርሃል ማለቱ ነው።

ከዛኔ ጀምሮ ሰዎች በሚያውቁት ነገር ላይ  ሊሸውዳቸው ለሞከረ ሰው
على هامان يا فرعون
ኧረ ፊርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው

እያሉ አባባል አድርገው ይዘውታል።»

(منقول!)
||
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


አልሃምዱሊለህ        ይገባው ምስጋና
ከሐይማኖት መሮጦ ሰጠን እስልምና
ደግሞ በችሮታው          ወፈቀን ለሱና

በአይን የምናየው        በጆሮ ምንሰማው
መች ተቆጥሮ ያልቃል  ይዘለቃል ኒዕማው

የሰው ዘር በሙሉ     ሲሆን በኪሳራ
በአላህ ያመነ         መልካምን የሰራ
በሐቅና በሶብር         ያሉትን  አደራ
ካከሳሪው መኃል   አወጣ እስትስና።

አልሐምዱሊለህ ይገባው ድጋሚ
መካሪ ለሰጠን   ለሆነ ሰው ሰሚ

ወጡ ሲባል ሰምተን ወንድሞች ዚያራ
   ተመኝተን ነበር       እኛም ብንጋራ

ከድስ'ሳባ  ቂልጦ   እረጅም በመጓዝ
ልጆቹንም መክሮ    ያሉትን ከመርከዝ

አዲስ ለሐገሩ    መች ሆኖ እንግዳ
አሸበረቃቸው       'ሰነን'እስከ 'ጎዳ'

ተከሰተላቸው     መድረሳ ሳንኩራ
በአለም ገበያ     ተውሂድን ሊዘራ

ሱናን የሚጣራ  አይደክመውም  ሄዶ
ደግሞ ተሻገረ        ወደ ወላይታ ሶዶ

ከዒሻ ቦኃላ        ትላንት ከመሼ'
መክሮ ተሰናብቶ  መጣልን ከሻሼ

መክሮ አስተምሮ    ከደረሰው ስፍራ
ዛሬ ወግ ደርሷታል  ወራቤም በተራ

መካሪዎች መጡ ብለናልም አህለን
ውዴታ ከኢማን      መቼም አይለየን

በሰለፉ ሳሊህ            በቀናው ጎዳና
በአዲሱ መስጅድ      በመስጅደ ሱና
ና በል ወንድሜ    ቁርኣን ሀዲስ ስማ!

ገና ከጅምሩ          ኡስስ አለ ተቅዋ
በሩን ክፍት አድርጎ ጀምሮዋል  ደዕዋ

አልሐምዱሊላሂ         ለፊቱም ለኃላ
ከመደሰት በቀር     ምን ይባላል ሌላ
ነገም ይሰብስበን በፍርደውሰል አዕላ
                      
#ኢብን ሙዘሚል

t.me//ibnmuzemil


ደዕወ ሰለፍያ በጦራ dan repost
ጥያቄ ቁጥር-26፦ ነብዩ ﷺ መካን ከፍተው ከገቡ በኃላ ኡዛ የተባለውን ጣዖት እንዲያወድም የላኩት ሰሃቢ ማን ነበር?
So‘rovnoma
  •   ሀ) ዘይድ እብኑ ሃሪሳ رضي الله عنه
  •   ለ) ኻሊድ እብኑ ወሊድ رضي الله عنه
  •   ሐ) ዓሊይ እብኑ አቢ ጧሊብ رضي الله عنه
  •   መ) ኡመር እብኑ አል-ኸጧብ رضي الله عنه
95 ta ovoz


✍️አቶ ኖክያ ልጆቻቸውን እየመከሩ…

ካሜራ አልነበረኝ ሀራም አልቀረፅኩኝ
ፌስቡክ አልነበረኝ ፊትና አልፈጠርኩኝ።

በፊልም በሙዚቃ ያልሰራሁ ማእስያ

ኩሩ አባታችሁ እኔ ነኝ ኖክያ!
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


አልሃምዱሊለህ        ይገባው ምስጋና
ከሐይማኖት መሮጦ ሰጠን እስልምና
ደግሞ በችሮታው          ወፈቀን ለሱና

በአይን የምናየው        በጆሮ ምንሰማው
መች ተቆጥሮ ያልቃል  ይዘለቃል ኒዕማው

የሰው ዘር በሙሉ     ሲሆን በኪሳራ
በአላህ ያመነ         መልካምን የሰራ
በሐቅና በሶብር         ያሉትን  አደራ
ካከሳሪው መኃል   አወጣ እስትስና።

አልሐምዱሊለህ ይገባው ድጋሚ
መካሪ ለሰጠን   ለሆነ ሰው ሰሚ

ወጡ ሲባል ሰምተን ወንድሞች ዚያራ
   ተመኝተን ነበር       እኛም ብንጋራ

ከድስ'ሳባ ቂልጦ   እረጅም በመጓዝ
ልጆቹንም መክሮ    ያሉትን ከመርከዝ

አዲስ ለሐገሩ    መች ሆኖ እንግዳ
አሸበረቃቸው       'ሰነን'እስከ 'ጎዳ'

ተከሰተላቸው     መድረሳ ሳንኩራ
በአለም ገበያ     ተውሂድን ሊዘራ

ሱናን የሚጣራ  አይደክመውም  ሄዶ
ደግሞ ተሻገረ        ወደ ወላይታ ሶዶ

ከዒሻ ቦኃላ        ትላንት ከመሼ'
መክሮ ተሰናብቶ መጣልን ከሻሼ

መክሮ አስተምሮ    ከደረሰው ስፍራ
ዛሬ ወግ ደርሷታል  ወራቤም በተራ

መካሪዎች መጡ ብለናልም አህለን
ውዴታ ከኢማን      መቼም አይለየን

በሰለፉ ሳሊህ            በቀናው ጎዳና
በአዲሱ መስጅድ      በመስጅደ ሱና
ና በል ወንድሜ    ቁርኣን ሀዲስ ስማ!

ገና ከጅምሩ          ኡስስ አለ ተቅዋ
በሩን ክፍት አድርጎ ጀምሮዋል  ደዕዋ

አልሐምዱሊላሂ         ለፊቱም ለኃላ
ከመደሰት በቀር     ምን ይባላል ሌላ
ነገም ይሰብስበን በፍርደውሰል አዕላ
                      
#ኢብን ሙዘሚል
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


አንጀት የሚሰብር የልጆች ግንዛቤ


እናቱን ሞት የነጠቀው ህፃን መንገድ ዳር ተቀምጦ ጭቃ እያቦካ ነው

አባቱ ከስራ ወደ ቤት ሲመለስ አፈርን ከውሀ ጋር እያላወሰ ሲያሽ ይመለከተዋል

"ልጄ ሆይ:- በጭቃ አትጫወት ልብስህ ይቆሽሻል ሰውነትህም ይቦካል በል ና አሁን ተነስ ወደ ቤት ግባና ታጠብ"

"አባቴ ሆይ:- እኛ ከጭቃ እንደተፈጠርን አልነገርከኝምን?"

"አዎ ልጄ:- ከጭቃ ነው የተፈጠርነው"

"እባክህ እርዳኝና እናቴን እንደገና እንስራት" የአላህህህህህህ

"እህ የእናት ናፍቆት"

ከአፈር በታች የሆኑ እናቶችን ሁሉ ፈጣሪ ምህረቱን ይለግሳቸው🤲

በህይወት ያሉትንም ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸው እንከባከባቸው 🤲


https://t.me/abufawzanibnufarisaselefiy




ሽርክ
በታላቁ አባታችን አቢ አብዱረህማን ኢብራሂም ሀፊዘሁላህ ወረዓ


በደንብ አንብብናና ለሙስሊም   ጓደኞችህ አካፍላቸው!!!
👆የዚህን ትርጉም ለሁሉም ግልፅ እንዲሆንና ሙስሊሞች ሁሉ ከዚህ ሙሲባ  ሸር እንዲርቁ   👉 ብዙ ሙስሊም ወገኖቻችን ተገናኝተው ሲለያዩ አሰላሙ አለይኩም ከማለት ፋንታ የሚጠቀሙትን  (by) ባይ የምትለዋ ቃል  ትርጉሟንና አደገኝነቷ ታውቃለህን? እኛ ሙስሊሞች ሳናውቅ አውሮፓዊያኖችን እየተከተልን አደጋ ላይ ስንወድቅ ተመልከቱ ነቢያችን صلى الله عليه وسلم ሀዲሳቸው ላይ እንዲህ ይላሉ  (( የሰው ልጅ አንዲት  ንግግርን ይናገራል ምንም ቦታና ትኩረት ሳይሰጣት ነገር ግን የሰባ አመትን ያክል የጀሀነም እሳት ውስጥ ይዛው ትወርዳለች )) አሉ።   እና ይቺ ባይ የምትለዋ ቃል ትርጉሟ  ካየን ፦  ጳጳሱ (ቄሱ) ጥበቃቸው  ስር ያርጉህ   ብሎ ዱአ ማድርግን ነው  ፣እኛ ሙስሊሞች ጠባቂያችን الله ብቻ ነው ከሱ ውጪ ጥበቃን መፈለግ ሽርክ ነው እያልን   ነገር ግን በዚች ቃል ብቻ  ሳናውቅ ጠባቂያችን በሆነው በጌታች በ الله አሻርከናል አጋርተናል ማለት ነው። ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ  ልናረግለትና ሙስሊሞችን በሙሉ ልናስጠነቅቃቸው ግድ የሚሆንብን  ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው ፣                                         ነፍሶችን ለማዳን ለቻልከው ሁሉ አስተላልፍ አድርስ አንተም ይቺን ቃል ዳግመኛ እንዳትጠቀማት ተጠንቀቅ ፣  አስበው ይህንን እያስተላለፍክ በ الله ፍቃድ ስንት ሚሊየን ሙስሊሞችን ለማዳን ሰበብ መሆን እንደምትችል፡                                                       وفق الله الجميع

https://t.me/oumershaer/193
https://t.me/oumershaer/193


✍️
ሁሉም የቢድዓ ባልተቤቶች……
በአመለካከት ቢለያዩም ሰለፍዮችን በመዋጋት ግን ይስማማሉ።

ከጥቃቅን ጀምዕዮች ጀምሮ እስከ ትላልቅ ኸዋሪጆች ሁሉም ሰለፍዮችን ማስወገድ ይፈልጋሉ።

እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ
አጠቃላይ የእስልምና ጥላቻ ያለበት ሁሉ የእነርሱ ደጋፊና ተባባሪ ነው።

ለዚህም ነው ለኢማሙ ሻፊዒይ
“የሐቅ ባለቤቶች ከባጢል ባለቤቶች እንዴት መለየት እንችላለን❓”
ተብለው ሲጠየቁ
👇
👉"የጠላት ቀስት ተከታተል; እሷ ወደ ሐቀኞች ትመራሃለች።"
ብለው የመለሱት። ምክንያቱም፦
የጠላት ቀስት የሚወነጨፈው፣ የጠላት ጦር የሚወረወረው፣ የጠላት ምላስ የሚሾለው፣ የጠላት አፈ ሙዝ የሚያልመው ሐቀኞች ሰለፍዮች ላይ ነው።

ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋ
ሁሌም በሁሉም ቦታ የበላይነት የእነርሱ ነው። ምክንያቱም፦
{وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ}
{ያማረው መጨረሻ አላህን ለሚፈሩት ነው።}

🔗 t.me/hamdquante


«ግጥም
አቡ አብዱረህማን ቡዙነው ውለታው»


📎በምል ርዕስ አጠር ያለች ግጥም

🎙 በወንድማችን አቡ አቡበክር (ሙሀመድ ዳሪ) አላህ ይጠብቀው።

🏢በስልጤ ዞን ሳንኩራ አለም ገበያ መድረሳ

📅 እሁድ:- 14/05/2015 EC ከዙሁር በኋላ።

https://t.me/Abueshek/3648


Abu furayhan dan repost
📚እየተቀራ ያለ ኪታብ

የኪታቡ ፒድኤፍ
https://t.me/museffafaris/2487

1:
https://t.me/museffafaris/2558

2:
https://t.me/museffafaris/2490

3:
https://t.me/museffafaris/2493

4:
https://t.me/museffafaris/2500

5:
https://t.me/museffafaris/2502

6:
https://t.me/museffafaris/2512

7:
https://t.me/museffafaris/2519

8:
https://t.me/museffafaris/2524

9:
https://t.me/museffafaris/2527

10:
https://t.me/museffafaris/2542

11:
https://t.me/museffafaris/2543

12:
https://t.me/museffafaris/2544

13:
https://t.me/museffafaris/2557

14:
https://t.me/museffafaris/2558

15:
https://t.me/museffafaris/2576

16:
https://t.me/museffafaris/2583

17:
https://t.me/museffafaris/2602

18:
https://t.me/museffafaris/2605

19:
https://t.me/museffafaris/2635

20:
https://t.me/museffafaris/2636

21:
https://t.me/museffafaris/2639

22:
https://t.me/museffafaris/2651

23:
https://t.me/museffafaris/2654

24:
https://t.me/museffafaris/2665

25:
https://t.me/museffafaris/2668

26:
https://t.me/museffafaris/2671

27:
https://t.me/museffafaris/2683

28:
https://t.me/museffafaris/2692

29:
https://t.me/museffafaris/2710

30:
https://t.me/museffafaris/2726

31:
https://t.me/museffafaris/2727

32:
https://t.me/museffafaris/2732

33:
https://t.me/museffafaris/2740

34:
https://t.me/museffafaris/2760

35:
https://t.me/museffafaris/2762

36:
https://t.me/museffafaris/2778

37:
https://t.me/museffafaris/2779

38:
https://t.me/museffafaris/2819

39:
https://t.me/museffafaris/2829

40:
https://t.me/museffafaris/2835

41:
https://t.me/museffafaris/2837

42:
https://t.me/museffafaris/2848

43:
https://t.me/museffafaris/2850

44:
https://t.me/museffafaris/2872

45:
https://t.me/museffafaris/2895

46:
https://t.me/museffafaris/2904

47:
https://t.me/museffafaris/2927

ይቀጥላል.....




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
#ለአለማት እዝነት በተላኩት በውዱ ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት አውርዱ!!

@መልካም ጁመዓ


አንዲት ባሏ ሌላ ሚስት ሊደርብባት መሆኑን የሰማች ሚስት ለባሏ አራት እንቁላሎች ቀቅላ የተለያየ ቀለም ቀብታ አቀረበችለት።
እሱም በነዚህ እንቁላሎች መካከል ምን ልዩነት አለ? ለምን የተለያየ ቀለም ተቀቡ?
እያለ ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ ጥያቄውን አቀረበ።

እሷም እስኪ ቅመሳቸው ስትል ወደ እንቁላሎቹ አመላከተችው።

እሱም ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ ሁሉንም እንቁላሎችን በላ። በመጨረሻም እንቁላሎችን ተመሳሳይ ጣእምና ቃና የያዙ ሆነው አገኛቸው።

እሷም ልቦናው ሌላን ለከጀለው ባሏ ሴቶችም ልክ እንደነዚህ እንቁላሎች የከለር እንጅ ሌላ ልዩነት የላቸው ስትል ነገረቸው።

እሱም የዋዛ አልነበረምና ውዷ ባለቤቴ ሆይ ንግግርሽ ልክ ነው። ነገር ግን ካቀረብሽልኝ ምሳሌ አንድ እውነት ገብቶኛል ሲል ነገራት።

እሷም ምንድን ነው የገባህ እውነታ ብላ ጠየቀችው።

እሱም አንድ አካል አራት እንቁላል ካልበላ መጥገብ እንደማይችል ሲል መራራውን .....ነገራት ።

ከመጠነኛ ለውጥ ጋር ከዐረብኛ የተመለሰ

👇👇👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇
👇👇👇
👇
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


3)
(يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا)

«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
[አል-አሕዛብ: 59]

√ ታላቁ የቁርኣን ሊቅና የነቢዩ ﷺ ባልደረባ ኢብኑ ዐ-ብ'ባስ " أمر الله نساء المؤمنين إذا خرجن من بيوتهن في حاجة أن يغطين وجوههن من فوق رؤوسهن بالجلابيب ويبدين عيناً واحدة " «አማኝ ሴቶች ከቤታቸው በወጡ ጊዜ በጅልባቦቻቸው ከራሶቻቸው ጀምሮ ፊቶቻቸውን እንዲሸፍኑና አንደደ ዓይናቸውን እንዲገልጡ አዟል!» ብሏል። አንድ ዓይን መግለጥ የሚቻለው መንገድ ለማየትና መሰል አስገዳጅ ነገር ካለ ብቻ እንጂ ሙሉውን መሸፈን አለባቸው።
وقوله رضي الله عنه : ويبدين عيناً واحدة إنما رخص في ذلك لأجل الضرورة والحاجة إلى نظر الطريق فأما إذا لم يكن حاجة فلا موجب لكشف العين .
ከፊል ዑለማዎች ይህንን ንግግሩን መርፉዕ (ከነቢዩ ﷺ የተነገረ) ነው ብለዋል።

*
4)
(لَّا جُنَاحَ عَلَيْهِنَّ فِي آبَائِهِنَّ وَلَا أَبْنَائِهِنَّ وَلَا إِخْوَانِهِنَّ وَلَا أَبْنَاءِ إِخْوَانِهِنَّ وَلَا أَبْنَاءِ أَخَوَاتِهِنَّ وَلَا نِسَائِهِنَّ وَلَا مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ ۗ وَاتَّقِينَ اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدًا)

«(የነቢዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸውም፣ በወንድሞቻቸውም፣ ወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ (ምእምናት በኾኑት) በሴቶቻቸውም፣ እጆቻቸው በጨበጧቸውም ባሮች (አጠገብ በመገለጥ) በእነርሱ ላይ ኃጢአት የለባቸውም፡፡ (ሴቶች ሆይ! ታዘዙ) አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡፡»

[አል-አሕዛብ: 55]

√ ከዚህ አንቀፅ የምንረዳው ከነዚና በሱረቱ-ል-ኑር ላይ ከተዘረዘሩት ከተፈቀዱላቸው አካላት ውጭ መገለጥ እንደማይቻል ነው።
*

5) በሐዲሥ እንደመጣው ነቢያችን ﷺ
" إذا خطب أحدكم إمرأة فلا جناح عليه أن ينظر منها إذا كان إنما ينظر إليها لخطبة وإن كانت لاتعلم"
«ከእናንተ አንዳችሁ ሴትን ማጨት በሻ ጊዜ፤ ወደርሷ የሚመለከተው ለማግባት ከሆነ በማታውቅ መልኩ ቢመለከታት ችግር የለውም!» ብለዋል። ይህ ማለት ከዚህ አላማ ውጭ አጅነቢይ ሴትን መመልከት የተከለከለ መሆኑን ያሳያል።

ሐዲሡን ያስተላለፈው ጃቢር ኢብኑ ዐብዲ-ል'ላህ ሲሆን፤ አሕመድ: 14626፣ አቡ ዳውድ: 2082 ላይ ይገኛል።
*
6) ኡሙ ዓጢየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢያችን ﷺ በሁለቱ የዒድ በዓላት ወቅት ሐይዽ ላይ ያሉ ሴቶችም ጭምር እንድንወጣ አዘዙን ካለች በኋላ፤
قُلتُ: يا رَسولَ اللهِ، إحْدَانَا لا يَكونُ لَهَا جِلْبَابٌ،
«ከእኛ አንዳችን ጂልባብ የሌላት ናት!» ብዬ ስጠይቃቸው፤
قالَ: لِتُلْبِسْهَا أُخْتُهَا مِن جِلْبَابِهَا.
«እህቷ ከጅልባቧ ታልብሳት!» ብለው መለሱልኝ ብላለች።

የሐዲሡ አስተላላፊ ራሷ ኡሙ ዓጢያህ ነሲባህ ቢንት ከዕብ ስትሆን ሐዲሡ ሶሒሕ ሙስሊም: 883 ላይ ይገኛል።
አስቡት! ጂልባብ ለሌላት ሴት እንኳ ያለ ጂልባብ መውጣት አልተፈቀደላትም። ጂልባብ መግዛት እየቻሉ የማይለብሱ ምን ሊባሉ ነው? የሶሐባ ሴቶች አርዓያዎችሽ ከሆኑ፤ ተመልከች እነርሱ ያለ ጂልባብ አይወጡም ነበር። ያለ ጂልባብ ስለማይወጣ ነው «ጂልባብ የሌላት ምን ትሁን?» ተብለው መጠየቃቸው።

*
7) የአማኞች እናት እናታችን ዓኢሻህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) በነቢያችን ﷺ ዘመን ሴቶች የፈጅርን ሶላት ከርሳቸው ጋር በጀማዓህ ለመስገድ ይታደሙ እንደነበር ገልጻ ከነርሱ መካከል የተወሰኑት ሒጃባቸውን በትክክል አልለበሲም ነበርና እንዲህ አለች፦
وقالت : لو رأى رسول الله صلى الله عليه وسلم من النساء ما رأينا لمنعهن من المساجد كما منعت بنو إسرائيل نساءها " .
«እንደው እኛ ያየነውን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ተመልከተው በነበር፤ የእስራኤል ልጆች ሴቶቻቸውን እንደከለከሉት ሁሉ ከመስጅደደ ይከለክሏቸው ነበር!» አለች። የዛሬዎቹን ሴቶች ብትመለከት ምን ልትል ነው በአላህ?! ይህ የሚያሳየው መሸፈን የሶሐባ ሴቶች የተለመደ ተግባር መሆኑን ነው።
*
8) ኢብኑ ዑመር ባስተላለፈው ሐዲሥ ላይ ነቢያችን ﷺ «مَنْ جَرَّ ثَوْبَهُ خُيَلاءَ لَمْ يَنْظُرْ اللَّهُ إِلَيْهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ» «ልብሱን በኩራት የጎተተን ሰው፤ አላህ የቂያም ቀን ወደርሱ አይመለከትም!» ሲሉ፤ ኡሙ ሰለማህ «ሴቶች እንደት ሊያደርጉ ነው?» ብላ ስትጠይቅ «አንድ ስንዝር ያርዝሙት!» አሏት  እርሷም ሲራመዱ እግራቸው ሊገለጥ እንደሚችል ስትነግራቸው፤ አንድ ክንድ እንዲጨምሩበት ነገሯት። ታዲያ ግማሽ አግራቸው ድረስ የሰቀሉት እህቶችስ? እግሯን በዚህ ደረጃ እንድትሸፍን ከታዘዘች፤ ከእግር በላይ ፈታኝ የሆነው ፊትስ?

ሐዲሡ: ቲርሚዚይ: 1731፣ አልነሳኢይ: 5336፣ አሕመድ: 5173 ላይ ይገኛል።
*
9) አሁንም እናታችን ዓኢሻህ እንዳስተላለፈችው ከነቢያችን ﷺ ጋር በመሰናበቻው ሐጅ ወቅት ኢሕራም ላይ ሳሉ ጋላቢዎች በአጠገባቸው ሲያልፉ የተገለጠውን ፊታቸውን በጂልባባቸው ይሸፍኑ እንደነበር ተናግራለች። ይህ የሚያሳየው በሐጅና ዑምራ ጊዜ ፊት እንደሚገለጡና ከዚያ ውጭ ግን እንደሚሸፈኑ ነው። ሐዲሡ አቡ ዳውድ: 1562 ላይ ይገኛል።

*
10) በኢፍክ ዘመቻ ጊዜ እናታችን ዓኢሻህ ወደ ኋላ ቀርታ ነበርና የሶፍዋን ኢብኑ ሙዕጢልን ድምፅ የሰማች ጊዜ ፊቷን መሸፈኗን ተናግራለች። ምንም እንኳ ሒጃብ ከመደንገጉ በፊት አይቷት የሚያውቅ ቢሆንም!

[አል-ቡኻሪይ: 4750፣ ሙስሊም: 2770]
*

11)
(… وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ ۚ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ ۚ…)
«…ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡ …»
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


👋"አጅነቢይ"( أَجْنَبِيّ ) መጨበጥ🚫

አጅነቢይ ማለት:- ባዕድ" ማለት ሲሆን አንድ ሙሥሊም ወንድ ወይም አንዲት ሙሥሊም ሴት በተቃራኒ ፆታ ያሉትን ለመጨበጥ ወይም ጸጉሯን ለማየት ሐላል ያልሆነ ሰው ማለት ነው።

ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ በእስልምናችን እንዴት ይታያል ለሚለው ?
أَنَّ عَائِشَةَ، أَخْبَرَتْهُ عَنْ بَيْعَةِ النِّسَاءِ، قَالَتْ مَا مَسَّ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم بِيَدِهِ امْرَأَةً
ዓኢሻህ እንዳስተላለፈችው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አጅነቢይ ሴቶችን በእጃቸው አይጨብጡም ነበር" ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 33, ሐዲስ 131
عن معقل بن يسار يقول : قال رسول الله ﷺ : " لئن يطعن في رأس أحدكم بمخيط من حديد خير له من أن يمس امرأة لا تحل له " رواه الطبراني في الكبير ( 486 ) والحديث : قال الألباني عنه في " صحيح الجامع " ( 5045 ) : صحيح .
"ከእናንተ አንዳችሁ የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ: አናቱን ከብረት በሆነ ወስፌ ቢወጋ ይሻለዋል"
وعن عروة أن عائشة أخبرته عن بيعة النساء قالت : ما مس رسول الله ﷺ بيده امرأة قط رواه مسلم ( 1866 )
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች:– "የአላህ መልክተኛ ﷺ በፍፁም አጅነቢይ ሴትን ነክተው አያውቁም"
قال رسول الله ﷺ : " إني لا أصافح النساء إنما قولي لمائة امرأة كقولي لامرأة واحدة " رواه النسائي ( 4181 ) وصححه الألباني " صحيح الجامع " ( 2513 ) .
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ግን እንዲህ አሉ “እኔ (አጅነቢይ) ሴቶችን አልጨብጥም፡፡ ለመቶ ሴቶች የምናገረው በተናጠል ለአንዲት ሴት እንደተናገርኩ ነው::”
قال الإمام النووي : ولا يجوز مسها في شيء من ذلك ." المجموع " ( 4 / 515 )

ኢማሙ ነወዊ በአልመጅሙእ
4 / 515 ላይ እንዳሰፈሩት

« አጅነቢይ ሴት የትኛውም አካሏን መንካት አይቻልም»።
لا تجوز المصافحة ولو بحائل من تحت ثوب وما أشبهه والذي ورد بذلك من الحديث ضعيف

☀️አንድ ሙሥሊም✅
ወንድ ጸጉሯ ለማየት ሆነ እጇን ለመጨበጥ
#ሐላል_የሆኑለት_እንስት
እናቱ፣ አክስቱ፣ እህቱ፣ የወንድሙን ሴት ልጅ፣ የእህቱን ሴት ልጅ፣ ሚስቱ፣ ሴት ልጁ፣ የሚስቱ እናት ናቸው።

☀️አንዲት ሙሥሊም✅ ሴት_ጸጉሯ_ለማሳየት_ሆነ_ለመጨበጥ ሐላል የሆኑላት
#ተባዕት

አባቷ፣ አጎቷ፣ ወንድሟ፣ የወንድሟ ወንድ ልጅ፣ የእህቷ ወንድ ልጅ፣ ባሏ፣ ወንድ ልጇ፣ የባሏ አባት ናቸው።

☀️አንድ ሙሥሊም🚫 ወንድ_ጸጉሯ_ለማየት_ሆነ እጇን ለመጨበጥ ሐራም የሆኑባት

እንስት የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ፣ የወንድም ሚስት፣ የሚስት እህት፣ የጎረቤት ሴት፣ የአብነት ሴት፣ የአስኳላ ሴት፣ የሥራ ባልደረባ ሴት ወዘተ ናቸው።

☀️አንዲት ሙሥሊም🚫 ሴት_ጸጉሯ_ለማሳየት_ሆነ ለመጨበጥ ሐራም የሆኑባትት ተባዕት
የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ፣ የእህት ባል፣ የባል ወንድም፣ የጎረቤት ወንድ፣ የአብነት ወንድ፣ የአስኳላ ወንድ፣ የሥራ ባልደረባ ወንድ ወዘተ ናቸው።

💥ተልካሻ ምክንያቶች
ልባችን ንፁህ ናት" ይላሉ
የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩﷺልብ
የበለጠ ንፁህ ናትን❓
◉" ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል" ይላሉ
እስልምና የመጣው ነብያችንም ﷺየተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ ለኢትዮፕያ ለዓረብ ለፈረንጅ
ለጥቁር ለሀብታም ለድሀ አይደለም
ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ
"ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም"ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል።
◉አይ ዘመዶቼ ሌላእምነት ተከታይ ስለሆ አይርዱኝም:: ካልተረዱህ እንዲህ በላቸው:-
لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِىَ دِينِ
«ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡ በል።
◉ከሚከፉብኝ……
ሰዎችን ለማስደሰት ስትለፋ ከጌታህን እንዳትጠላ ተጠንቀቅ ግብህን /ግብሽን ያ አላህ ውዴታ ይሁን!

ሸርርርር

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy


መገን  ዘመናችን  መገን  አራዳነት፣
ዱባ እየገመጡ ትርንጎ ነው ማለት፣
እንዳው ከንቱ መሆን እራስን ማሞኘት።
እንደት ነሽ አማነሽ ፒስ ነሽ የሚል መቶ፣
አሰላሙ አለይኩም ተጥሎ ተረስቶ፣
ሰው በፖለቲካ  በወሬ ተሞልቶ።
አንተ የነ እንትና የነገሌ እያለ፣
የገዛ ወንድሙን አርዶ እየገደለ።
ሲቀመጥ ሲነሳ ሲበላ ሲጠጣ፣
ሰው የሰውን ነውር መንጥሮ እያወጣ፣
የራሱን አሽጎ ባቅማዳ በሻንጣ፣
ታዲያ
የአላህ ነስር እንደት ብሎ ይምጣ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/abuayubzakir

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

134

obunachilar
Kanal statistikasi