አልሃምዱሊለህ ይገባው ምስጋና
ከሐይማኖት መሮጦ ሰጠን እስልምና
ደግሞ በችሮታው ወፈቀን ለሱና
በአይን የምናየው በጆሮ ምንሰማው
መች ተቆጥሮ ያልቃል ይዘለቃል ኒዕማው
የሰው ዘር በሙሉ ሲሆን በኪሳራ
በአላህ ያመነ መልካምን የሰራ
በሐቅና በሶብር ያሉትን አደራ
ካከሳሪው መኃል አወጣ እስትስና።
አልሐምዱሊለህ ይገባው ድጋሚ
መካሪ ለሰጠን ለሆነ ሰው ሰሚ
ወጡ ሲባል ሰምተን ወንድሞች ዚያራ
ተመኝተን ነበር እኛም ብንጋራ
ከድስ'ሳባ ቂልጦ እረጅም በመጓዝ
ልጆቹንም መክሮ ያሉትን ከመርከዝ
አዲስ ለሐገሩ መች ሆኖ እንግዳ
አሸበረቃቸው 'ሰነን'እስከ 'ጎዳ'
ተከሰተላቸው መድረሳ ሳንኩራ
በአለም ገበያ ተውሂድን ሊዘራ
ሱናን የሚጣራ አይደክመውም ሄዶ
ደግሞ ተሻገረ ወደ ወላይታ ሶዶ
ከዒሻ ቦኃላ ትላንት ከመሼ'
መክሮ ተሰናብቶ መጣልን ከሻሼ
መክሮ አስተምሮ ከደረሰው ስፍራ
ዛሬ ወግ ደርሷታል ወራቤም በተራ
መካሪዎች መጡ ብለናልም አህለን
ውዴታ ከኢማን መቼም አይለየን
በሰለፉ ሳሊህ በቀናው ጎዳና
በአዲሱ መስጅድ በመስጅደ ሱና
ና በል ወንድሜ ቁርኣን ሀዲስ ስማ!
ገና ከጅምሩ ኡስስ አለ ተቅዋ
በሩን ክፍት አድርጎ ጀምሮዋል ደዕዋ
አልሐምዱሊላሂ ለፊቱም ለኃላ
ከመደሰት በቀር ምን ይባላል ሌላ
ነገም ይሰብስበን በፍርደውሰል አዕላ
#ኢብን ሙዘሚል
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy
ከሐይማኖት መሮጦ ሰጠን እስልምና
ደግሞ በችሮታው ወፈቀን ለሱና
በአይን የምናየው በጆሮ ምንሰማው
መች ተቆጥሮ ያልቃል ይዘለቃል ኒዕማው
የሰው ዘር በሙሉ ሲሆን በኪሳራ
በአላህ ያመነ መልካምን የሰራ
በሐቅና በሶብር ያሉትን አደራ
ካከሳሪው መኃል አወጣ እስትስና።
አልሐምዱሊለህ ይገባው ድጋሚ
መካሪ ለሰጠን ለሆነ ሰው ሰሚ
ወጡ ሲባል ሰምተን ወንድሞች ዚያራ
ተመኝተን ነበር እኛም ብንጋራ
ከድስ'ሳባ ቂልጦ እረጅም በመጓዝ
ልጆቹንም መክሮ ያሉትን ከመርከዝ
አዲስ ለሐገሩ መች ሆኖ እንግዳ
አሸበረቃቸው 'ሰነን'እስከ 'ጎዳ'
ተከሰተላቸው መድረሳ ሳንኩራ
በአለም ገበያ ተውሂድን ሊዘራ
ሱናን የሚጣራ አይደክመውም ሄዶ
ደግሞ ተሻገረ ወደ ወላይታ ሶዶ
ከዒሻ ቦኃላ ትላንት ከመሼ'
መክሮ ተሰናብቶ መጣልን ከሻሼ
መክሮ አስተምሮ ከደረሰው ስፍራ
ዛሬ ወግ ደርሷታል ወራቤም በተራ
መካሪዎች መጡ ብለናልም አህለን
ውዴታ ከኢማን መቼም አይለየን
በሰለፉ ሳሊህ በቀናው ጎዳና
በአዲሱ መስጅድ በመስጅደ ሱና
ና በል ወንድሜ ቁርኣን ሀዲስ ስማ!
ገና ከጅምሩ ኡስስ አለ ተቅዋ
በሩን ክፍት አድርጎ ጀምሮዋል ደዕዋ
አልሐምዱሊላሂ ለፊቱም ለኃላ
ከመደሰት በቀር ምን ይባላል ሌላ
ነገም ይሰብስበን በፍርደውሰል አዕላ
#ኢብን ሙዘሚል
t.me/abufawzanibnufarisaselefiy