ዓለም በ“አሜን” ባዮች ስለተከበበች በየጊዜው መንታ መንገዶች ላይ ቆማ ወደ ፊት ለመራመድ ታመነታለች። በድንቁርና ውስጥ መጠፋፋትን ማለም ዕጣ ፈንታዋ ይሆናል።አዲስ አሻራና ታሪክን የሚያሳርፍ አይገኝም። አይደለም ሰዎች ከተማዎች በዚያ ዓይነት ድብታ ውስጥ ያንቀላፋሉ። ትውልድ እየመጣ ትውልድ ይሄዳል። ነገር ግን የተለየ አብዮት አይከሰትም። ሁሉም “አሜን” እያለ ያደገድጋል። የቀረበለትን ያነግሣል።
“ጠላትህ ነው” ተብሎ የተነገረውን ይጠላል። “ወዳጅህ ነው” ተብሎ የተነገረውን ይወድዳል። ምክንያትን አይጠይቅም። ሲደሰትም፣ ሲቆጣም፣ ሲለግምም፣ ሲያብርም… በስሜት ላይ እንጂ በተረጋገጠ ገዢ እውነታ ላይ ተመሥርቶ አይደለም። ከዚህ ውስጥ ‘ለምን?’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ይዘን የመጣናቸውን ፍሬዎች በነሲብ ከመብላታችን በፊት በጥንቃቄ እንድንመዝናቸው ያነቃናል። ምክንያቱም ሁሉም የሐሳብ ፍሬ አይበላም። የተበላሹ ፍሬዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። በመዳፋችን የያዝናቸውን መልካም በረከቶችና ክፉ መርገሞችን እናነጻጽራለን። እጃችን ላይ ያለው ምንድን ነው? ምንስ እናድርግበት?
አንድ ማኅበረሰብ የመጣበትን መንገድ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ የሚያደርጉት እንቢተኞች ናቸው።
📖 አልገባኝም
ደራሲ -ዮናስ ዘውዴ