thoughts


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


books $thoughts

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦

‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..››


ህይወት ያለዉ ተስፋ ውስጥ ብርታት አለ። ህይወት ያለዉ ተስፋ ዉስጥ ጥንካሬ እና ለለውጥ መትጋት አለ። ህይወት ያለዉ ተስፋ ዉስጥ ህይወት ያለዉ ብርሃን አለ። ሌላው የሞተ ተስፋ ስስታዊ ምኞት ነው። ምኞት ከጉጉት የዘለለ ስኬት የለዉም ። ምኞት ረሀብተኛ ጓዳ ታቅፎ ወርቅ ወደሞላው የተቆለፈ የሰዉ ካዝና እያፈጠጡ ማፏሸክ ነው::
✍️ ሃዋዝ የሻነህ


"በራስ መተማመን ማለት ከሌሎች የተሻልክ እንደሆንክ ማሰብ ሳይሆን ከሌሎች ጋር ራስህን የምታወዳድርበት ምንም ምክንያት እንደሌለ መገንዘብ ነዉ"

✍️__ ማርያም ሀሰን


በሕይወት ውስጥ ትልቁ አሳዛኝ ነገር ሞት አይደለም፤ በሕይወት እያለን ቀብረናቸው የምንቀራቸው ሕልሞቻችን እንጂ።
🎤ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ


በጥንት ግሪካውያን ዘንድ አንድ ንጉስ ሲሾም በሄደበት ቦታ ሁሉ አብሮት የሚከተለው ድሃ ይመደብለታል

ይሄ ንጉስ በሄደበት ቦታ ሁሉ ድሃውን ይዞ የመዞር ግዴታ ነበረበት

የዚህ ድሃ ሰው ግዴታ በየ30 ደቂቃ ንጉሱን እየነካ "ንጉስ ሆይ! ሰው መሆንህን አትርሳ" ማለት ነው:: ንጉሱም ልቡ ሸፍቶ: ሰውነቱ ሰብቶ ከነበረ ወደ ቀልቡ ተመልሶ ሰው እንደሆነ ያስባል::

👇🏾

ሰው መሆንህን አትርሳ !!


ጭንቅላት እንደሆድ አይደለም ሲጎድል አያስታውቅም!


Arabic Proverbs


ጠላቶች_ስንሆን፣በደለኛ ስንሆን በልጁ ይቅርታ ያደረገልን ማን እንደ እግዚአብሔር አለ።
ሰው ሲበድል ተበዳዩን ካሳ ሰጥቶ ይቅርታ ይጠይቃል፣ እግዚአብሔር ግን በደለኞች ስንሆን ፣እርሱ እራሱ ካሳውን ከፍሎ ይቅርታ_አደረገልን:: እንዴት ያለ ፍቅር ነው?
"፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር_አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። "
(የዮሐንስ ወንጌል 3: 16)


ደስታህ ግን ጠፍቶ ሊቀር የሚችል ነገር አይደለም- ጊዜያዊ በሆነ ከፈን ሊጋረድ ብቻ ነው የሚችለው።

እናም በህይወት እስካለህ ድረስ ያንን ከፈን ልትገልጠው እድሉ አለህ።ያለምንም መሸማቀቅ እና ፍርሃት የሰማዩን መንበር በሙሉ አይንህ ማየት እስከቻልክ ድረስ- ውስጥህ ሙሉ በሙሉ ንፁህ እስከሆነ ድረስ እመነኝ ፒተር - እዚህ ሁሉ ችግርም ውስጥ ሆነህ ደስታን ማግኘት ትችላለህ።

~አና ፍራንክ


ብልጥ ሰው ጆሮ ሳይነፍጉት ንግግሩን ያቆማል፤ ነገር ግን ንግግሩ ምንም ይሁን ምን አንድን ሰው ማናደድ ከፈለግን ስለ እሱ እውነተኛ ነገር ማውራት በቂ ነው!”

                ―ፍሬድሪክ ኒቼ


ባመነ አይደለም ፥ በተጠመቀ
ባወቀ አይደለም ፥ በተጨነቀ

ያመነ አይድንም ፥ የጠረጠረም
ሰው ነገን እንዲያውቅ ፥ አልተፈጠረም ።

ፈዛዛው ፥ ንቁም
መሐይም ፥ ሊቁም
ህይወት ላይ ሲሆን
ምንም አያውቁም ።

ለጽድቅ የሰሩት ፥ ሲዖል ይጥላል
ለሞት የዋጡት ፥ ከሞት ያድናል
ታዲያ ማን ደፍሮ እውነት ነኝ ይላል ?
አይሆንም ያሉት ፥ ሊሆን ይችላል ።

✍️Habtamu Hadera


ደስተኛ ለመሆን ሁለት ነገሮችን ማስወገድ አለብህ፤ የወደፊቱ መጥፎ ይሆናል የሚል ስጋት እና ያለፈውን መጥፎ ትዝታ!


ዓለም በ“አሜን” ባዮች ስለተከበበች በየጊዜው መንታ መንገዶች ላይ ቆማ ወደ ፊት ለመራመድ ታመነታለች። በድንቁርና ውስጥ መጠፋፋትን ማለም ዕጣ ፈንታዋ ይሆናል።አዲስ አሻራና ታሪክን የሚያሳርፍ አይገኝም። አይደለም ሰዎች ከተማዎች በዚያ ዓይነት ድብታ ውስጥ ያንቀላፋሉ። ትውልድ እየመጣ ትውልድ ይሄዳል። ነገር ግን የተለየ አብዮት አይከሰትም። ሁሉም “አሜን” እያለ ያደገድጋል። የቀረበለትን ያነግሣል።

“ጠላትህ ነው” ተብሎ የተነገረውን ይጠላል። “ወዳጅህ ነው” ተብሎ የተነገረውን ይወድዳል። ምክንያትን አይጠይቅም። ሲደሰትም፣ ሲቆጣም፣ ሲለግምም፣ ሲያብርም… በስሜት ላይ እንጂ በተረጋገጠ ገዢ እውነታ ላይ ተመሥርቶ አይደለም። ከዚህ ውስጥ ‘ለምን?’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ይዘን የመጣናቸውን ፍሬዎች በነሲብ ከመብላታችን በፊት በጥንቃቄ እንድንመዝናቸው ያነቃናል። ምክንያቱም ሁሉም የሐሳብ ፍሬ አይበላም። የተበላሹ ፍሬዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። በመዳፋችን የያዝናቸውን መልካም በረከቶችና ክፉ መርገሞችን እናነጻጽራለን። እጃችን ላይ ያለው ምንድን ነው? ምንስ እናድርግበት?

አንድ ማኅበረሰብ የመጣበትን መንገድ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ የሚያደርጉት እንቢተኞች ናቸው።

📖 አልገባኝም
ደራሲ -ዮናስ ዘውዴ


በሌሎች ሰዎች ላይ ስናየው የሚያናድደን ማንኛውም ነገር፣ እራሳችንን በተሻለ ሁኔታ እንድንመረምር እና እንድንረዳ ያደርገናል።

— Carl Jung


ሁሉንም ሰው እንዳንተ መልካም ነው ብለህ የምታስብ ከሆነ የክፉ ሰዎች ተጎጂ መሆንህ የማይቀር ነው።ትልቁ ስህተትህ ሁሉም ሰው በህግና በሞራል ይመራል ብለህ ማመንህ ነው።ይሄን አምነህ ክፉ በሆኑ ሰዎች መሀል ሁልጊዜ ጥሩ ለመሆን እየሞከርክ ከሆነ ራስህን ለማጥፋት እየፈረምክ ነው ማለት ነው።ስለዚህ ራስህን ለማዳንና ዓለምን ለማሸነፍ እንደየሰው ባህሪ መለዋወጥ(?) እና ለጥሩዎች ጥሩ ለክፉዎች ክፉ መሆን አለብህ።

📕ርዕስ፦ልዑሉ
✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኪያቬሊ


ከአሳማ ጋር አትላፋ ሁለታችሁም ትግማ..ላቹ እሱ ደስ ይለዋል!

George Bernard Show
ከማይሆኑ ሰዎች ጋር አንጋጭ ለማለት ነው😂


ሰዎች የሚኖሩበት ትልቁ ወህኒ ቤት "ሌሎች ምን ይሉኛል" የሚለው ፍርሃት ነው፡፡


አዕምሯችንም ይደክማል!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን -የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት)

ብዙዎቻችን የአካላችንን ድካም በቀላሉ እንረዳዋለን ለምሳሌ እግራችን ሲደክም እንቀመጣለን፣ ትከሻችን ሲዝል ደግሞ ጋደም ብለን ለማረፍ እንሞክራለን። ነገር ግን አዕምሯችን የሰውነታችን ሁሉ መሪ ሆኖ 24 ሰዓት ያለእረፍት እንዲሠራ እናስገድደዋለን። አዕምሮ ልክ እንደ አካላችን ካልተንከባከብነውና ተገቢውን እረፍት ካልሰጠነው መድከሙ የማይቀር ነው።

በየቀኑ በኑሮና በሥራ ሩጫ ውስጥ ስንሆን አዕምሯችን " ደክሞኛል፣ እረፍት እፈልጋለሁ! " እያለ በተለያየ መንገድ ድካሙን ይገልፃል።

አንዳንዴ በእንቅልፍ ማጣት፣ አንዳንዴ የማተኮር አቅም በማጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለምክንያት ቶሎ በመበሳጨትና በስሜት መለዋወጥ ሊገለፅ ይችላል።

ታዲያ እነዚህን ምልክቶች እንደ ቀላል አይቶ ችላ ማለት ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል። የአዕምሮ ጤናን መጠበቅ የሚጀምረው ራስን ከማድመጥና ለራስ ጊዜ በመስጠት ነው።

ለአዕምሯችን ጊዜ መስጠትና ማሳረፍ ስንል ምን ማለታችን ነው?

- በቂ እንቅልፍ ወስደን አዕምሯችን ራሱን እንዲያድስ እድል በመስጠትና ከመተኛታችን በፊት ከስልክና ሶሻል ሚዲያ በመራቅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲያርፍ ማድረግ።

- ብቻችንን ከመብሰልሰል ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ የውስጥን ጫና እና ጭንቀት ማውራት፤ ስሜትን ለምናምነው የቅርብ ሰው ወይም ለባለሙያ በማጋራት የአዕምሮን ሸክም በማውረድ።

- ከዕለት ተዕለት ጩኸት ራቅ ብሎ በንጹህ አየር እና በተፈጥሮ መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን በማሳለፍ እንዲሁም ከአደንዛዥ እፆች ፣ ከጫት እንዲሁም ከአልኮል ጊዜያዊ መጠለያነት በመራቅ የአዕምሮን ጤና መጠበቅ እና መንከባከብ እንችላለን።


"ራሔል ስለ ልጆችዋ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ በራማ ተሰማ ፤ መጽናናትንም እንቢ አለች፤ ልጆችዋ የሉምና።"
ማቴ2፥18


አሁን እጆቻችን ላይ የተደላደሉ የመሰሉን ፀጋዎች የእኛ አለመሆናቸው የሚገባን ጊዜ ይመጣል። ገንዘባችን..ስልጣናችን..ዝናችን በእኛ ላይ የሚሸጋገሩ የዓለም ንብረቶች ናቸው።ለቀጣይ ተረኛ እናስረክባቸዋለን።

📕ርዕስ፦ጥሪ ወደ ሞት
✍️ደራሲ፦አህመድ ሁስ(ሻድ)


ወጣትነት ካላወቅሽበት ሬት ካወቅሽበት ደግሞ ማር ነው።

📚፦ኤጭ
📝፦አዘርግ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.