ባመነ አይደለም ፥ በተጠመቀ
ባወቀ አይደለም ፥ በተጨነቀ
ያመነ አይድንም ፥ የጠረጠረም
ሰው ነገን እንዲያውቅ ፥ አልተፈጠረም ።
ፈዛዛው ፥ ንቁም
መሐይም ፥ ሊቁም
ህይወት ላይ ሲሆን
ምንም አያውቁም ።
ለጽድቅ የሰሩት ፥ ሲዖል ይጥላል
ለሞት የዋጡት ፥ ከሞት ያድናል
ታዲያ ማን ደፍሮ እውነት ነኝ ይላል ?
አይሆንም ያሉት ፥ ሊሆን ይችላል ።
✍️Habtamu Hadera
ባወቀ አይደለም ፥ በተጨነቀ
ያመነ አይድንም ፥ የጠረጠረም
ሰው ነገን እንዲያውቅ ፥ አልተፈጠረም ።
ፈዛዛው ፥ ንቁም
መሐይም ፥ ሊቁም
ህይወት ላይ ሲሆን
ምንም አያውቁም ።
ለጽድቅ የሰሩት ፥ ሲዖል ይጥላል
ለሞት የዋጡት ፥ ከሞት ያድናል
ታዲያ ማን ደፍሮ እውነት ነኝ ይላል ?
አይሆንም ያሉት ፥ ሊሆን ይችላል ።
✍️Habtamu Hadera