ታሪክ በዛሬው እለት:-
ረፋድ አካባቢ... ክብድ ያለ ቀን ነበር፡፡ አደባባይ ላይ የተሰበሰበው የፊንፊኔ ህዝብ የሚሆነውን ነገር ለማየት በጭንቀት ባህር ውስጥ ሆኖ ይጠባበቃል ...
...
ወዲያው አንድ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ መልካቸው ጠየም ያለና አዋቂነታቸው ከገፃቸው ላይ የሚነበብ ሰው... በጭቃ የተለወሰ ጥቁር የጵጵስና ካባቸውን እንደለበሱ በከበቧቸው ፈርጣማ ወታደሮች እየተገፉ ከህዝቡ ፊትለፊት
ቆሙ...
...
ደቂቃዎች ነጎዱ... አንዳች አስፈሪ ድባብ ሁኔታውን ለማየት በተሰበሰበው ህዝብ መሀል ነግሷል... በወታደሮች ተከበው የመጡት የጳጳስ ልብስ የለበሱት ቆራጥ ሰውዬ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸውም ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው አጠገባቸው ቆሞ የነበረውን ወታደር
በትህትና ጠየቁት። እንዲቀመጡ ፈቀደላቸው...
...
ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ የሞት ፍርዳቸው ለህዝቡ ተነበበ... ሰውዬው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለእርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየፀለዩ ሕዝቡን ባረኩ። ወዲያውም የሞታቸው ሰዓት መድረሱን አውቀው ሰዓታቸውን
ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። ምንም አይነት ፍርሃት በፊት ገፃቸው ላይ አይነበብም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣልያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥና ታላቅ ፍርሃትም በፊቱ ይታይ
ነበር...
...
ብዙም ሳይቆይ በአቅራቢያቸው ከነበረው ግንብ አጠገብ ጀርባቸውን ወደ ህዝቡ አዙረው እንዲቀመጡ ተደረገ... ከዚያ በኋላ 8 የታጠቁ ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም የታጠቁትን ጥይት በኢትዮጵያዊዩ ጳጳስ ላይ አዘነቡ ፡፡ ንፁህ ደም ከጳጳሱ ገላ ላይ እየተንዠቀዠቀ ወደ መሬት ፈሰሰ...
...
በዚያች ሌሊት በፊንፊኔ ውስጥ በየቤቱ ልቅሶና ዋይታ ሆነ... ይህ የግፍ ግድያ ልክ በዛሬዋ እለት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ከ84 አመታት በፊት በጨካኞቹ የኢጣሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያዊው አርበኛ መገርሥ በዳሳ( በአቡነ ጴጥሮስ) ላይ ተፈፀመ...
ሀጫሉ በዘፈኑ ከትንሽ እስከ ትልቅ ገበርን ያሀገር ለኛ አልሆን አለ ብሏል አዎ አሁንም ኢትዮጵያ ኦሮሞ ደሙን እየሰጠ ዞራ ቀርጥፋ ምትበላው ሀገር ሆና ቀጥላለች