የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 1️⃣5️⃣
⏳ሻዕባን 15፣ 1294 (ሒጅራ) ወይም ኦገስት 25፣ 1877 (እ.አ.አ.) የዑስማኒያው የጦር መሪ አሕመድ ሙኽታር ባሻ የሩሲያውን ጦር “ኩድክለር” በተሠኘው የጦር አውድማ አሸንፎታል። በዚህ ድል የተነሳ “ጋዚ” ወይም “ዘማቹ” የሚል ማእረግ ከዑስማኒያው ሱልጣን “ዐብዱልሐሚድ ሁለተኛው” ተበርክቶለታል። አሕመድ ሙኽታር ባሻ ሩሲያዎችን ከዚህ ውጭም በተለያዩ የጦር አውድማዎች ላይ ተደጋጋሚ ድሎችን ተጎናጽፏል።
⏳ሻዕባን 15፣ 476 ሒጅሪያ ወይም እ.አ.አ. ዲሴምበር 28፣ 1083 ላይ ታላቁ ዓሊም አቢል ፈድል ዒያድ ኢብኑ ሙሳ አል-የሕሶቢይ አል-ሲብቲይ ተወለዱ። ቃዲ ዒያድ የሚታወቁበት ሥማቸው ነው። የምዕራቡ (ሞሮኮ) ሐፊዝ ናቸው። ከአምስተኛውና ስድስተኛው ምእተአመት (እንደ ሒጅራ) ታላላቅ የዒልም ሠዎች ይመደባሉ። ፊቅህ፣ ሐዲስ፣ ታሪክ እና ሌሎችም የእውቀት ዘርፎች ላይ የፃፏቸው መጽሐፍት ታላቅነታቸውን ይመሰክራሉ። ከእነዚህ መሐል “መሻሪቁል አንዋር” እና “ኢልማዕ” ምርጦቹና የታወቁት ናቸው።
⏳ሻዕባን 15፣ 1217 እንደ ሒጅራ ወይም እ.አ.አ. ዲሴምበር 11፣ 1803 ታላቁ ኢማም አቢስ-ሰናእ ሺሀቡድ-ዲን መሕሙድ አል-አሉሲይ ተወለዱ። አስራ ሶስተኛው ምእተአመት ሒጅሪያ ላይ ከነበሩት ታላላቅ ኢማሞች ይቆጠራሉ። “ሩሑልመዓኒ” የተሰኘው የቁርአን ማብራሪያ (ተፍሲር) ከመጽሐፍቶቻቸው መሀል የአሉሲይን ታላቅነት ይጠቁማል።