የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 2️⃣1️⃣
⏳ሻዕባን 21፣ 1208 እንደ ሒጅራ ወይም እ
.አ.አ. ጁላይ 25፣ 1793 ታላቁ የአዝሐር ሼኽ ኢማም አሕመድ አልዓሩሲ አረፉ። ሰውየው በአዝሀር ሸይኾች ዝርዝር ውስጥ አስራአንደኛው ሼኽ ናቸው። ሼኹ ጀግንነታቸውን ባንጸባረቁ አጋጣሚዎቻቸው ይታወቃሉ። በአንዳንድ ንጉሶች በደል ያረረውን ህዝብ በመርዳት ይታወቃሉ። የዒልም መድረክ ላይም ጎልተው የሚታዩባቸው መጽሐፍትም አሏቸው። ከነዚህም መሀል “ሙኽተሰሩል-ዓሩሲ ፊል ፊቅህ” የታወቀ ነው።
⏳ሻዕባን 21፣ 489 እንደ ሒጅራ ወይም ኦገስት 15፣ 1096 የአውሮፓው ጳጳስ የመስቀል ጦረኞች ቆስጠንጢኒያ ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጠሩ። ጥሪው ምስራቁን የሙስሊሙን ሀገር (ሶሪያ፣ ዒራቅ፣ ፊሊስጢን፣ ሊባኖስ) ለመውረርና አልቁድስን ከሙስሊሞች እጅ ለመመንጠቅ የሚደረግ ዝግጅት ለማድረግ ያቀደ ነበር።
⏳ሻዕባን 21፣ 559 ወይም ጁላይ 19፣ 1164 ሰላሁድ-ዲን አል-አዩቢይ ሑምስን ከመስቀለኞች እጅ የመነጠቀበት ቀን ነበር። ይች ቦታ እስትራቴጂካዊ ሚና ስለነበራትም ሌሎች የአካባቢው ቦታዎች ከእጁ ወድቀዋል።