የወርሀ ሻዕባን ታላላቅ ክስተቶች 2️⃣0️⃣
⏳ሻዕባን 20፣ 852 (ሒጅራ) ወይም ኦክቶበር 19፣ 1448 (እ.አ.አ.) የዑስማኒያው ሱልጣን ሙራድ ሁለተኛው ክርስቲያናዊውን የአውሮፓ ሠራዊት አሸንፏል። አውሮፓዎቹ መቶ ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን በዚህ ጦርነት ላይ አሰልፈዋል። ውጊያው የተካሄደውም ኮሶቮ ውስጥ ነበር። ሦስት ቀን ከፈጀ ውጊያ በኋላ 17 ሺህ የሚሆኑ አውሮፓዊያን ተገድለውበት ጦርነቱ ተጠናቋል። ይህ ውጊያ አውሮፓዎች ዑስማኒዮችን ከአውሮፓ ለማስወጣት ካደረጓቸው ዘመቻዎች መካከል ስድስተኛው ነበር። ነገር ግን አልተሳካም።