መቸም ብሆን አትተክዝ።ዱንያ በፍላጎታችን አይደለችም።እሷ’ማ ብሆን በአላህ ትዕዛዝ ናት።የአላህ ትዕዛዝ ሁሉም መልካም ነው።
አይዞህ አትጨነቅ።መጨነቅ ትርፉ ድካም ነው።ጉዳይህን ለአላህ ስጥ።እስከቻልክ ለመቀየር ሞክር።ዱዓም አክልበት።ከአላህ ትዕዛዝ ውጭ የምትሆንበት ቅፅበት የለም።አላህ ረስቶህም አይደለም።ኦሮፋም አሰልፎክ አይደለም።ይልቅ ላንተ ይበጃል ያለው ነገር ግዜው ስላልደረሰ ነው።ገና አላህ ካኖረህ ብዙ አመታትን ትኖራለህ።"ከዚህ ቦኃላ የተፃፈው ብመጣልኝስ ምን ላደርገው ነው "አትበል።
ግዜ የማይፈጀው ሀሳብ እንጂ የትኛውም ነገር ግዜ ይፈጃል።እንዲሁም የትኛውም ዱንያዊም ሆነ ኣኼራዊ ጉዳይ ቁጭ ብለህ አንተ ጋ አይመጣም።ቁጭ ብለህ የሰማይ ምድሩን አትመኝ።በቻልከው ልክ ለመቀየርና ለመቀያየር ጥረት አድርግ።እንደ ታፔላ አንድ ቦታ ላይ ተለጥፈህ ግዜህን አታቃጥል።ያለ ልፋት የሚመጣ ነገር ብኖር ሀሳብና ጭንቀት ብቻ ነው።ለውጥ እንጂ ነውጥ አይበግርህ።በቻልከው ያክል የሚያስተክዙህንና የሚያስከፉ ሰዎችን ለመራቅ ሞክር።የሚያቆሽሽህንና የሚያንቋሽሽህን ችላ በለው።
የሚያስጨንቃቸውና የሚያስከፋቸው ውጤትህና ለውጥህ እንጂ ውድቀትህና ውድመትህ አይደለም።ባንተ ውድቀትና ውጥረት ደስታ የሚያገኝ አካል ካለ ደስታውን አትቀማው።
የሱን ደስታ ለመቀማት ብለህ ሳይሆን ለራስህ ብለህ ራስህን አድን።መሬት ቢንቀጠቀጥ ሰማይ ቢፈርስ በሀያሉ ጌታ የተመካ ሰው ሊጎዳ አይችልም።ሁሌም ክፋት ለሚሰሩብህ ሰዎች ዱዓ አድርግላቸው።በዝምታህም ውስጥ ምክር ለግሳቸው።ባንተ ላይ የተፃፈው እንጂ ስላልተፃፈው ነገር ስልጣን እንደሌላቸው አስረግጠህ ንገራቸው።ጉዳትም ሆነ ጥቅም በሀያሉ ጌታ መሆኑ አንተን ያኮራሃል ።
አልሀምዱ ሊሏህ!!
🏝https://t.me/ibnujemilchannel