የሙነወር ልጅ ማምታቻ እስከ የት?!—————
የሙነወር ልጅና የቡድኑ ዋና ዋና አባላት ከነበሩበት ጠንካራ የሱንና አቋምና በቢድዐህ ባለ ቤቶች የሰልላ ሰይፍ ሆነው ከማስጠንቀቅ ፈፅሞ ባልተጠበቀ መንገድ ቁልቁል ሲወርዱ (የተምይዕ ዋሻ ሲሆኑ) ከታላላቅ የሱንና መሻይኾችና ኡስታዞች ለሚደርስባቸው በማስረጃ የታገዘ ጠንካራ ምላሽ ተደናግረው ከትክክለኛ ማስረጃ የተራቆቱ በመሆናቸው መቋቋም ሲያቅታቸው ቲፎዞዎች እንዳይበተኑባቸው፣ የትቢትና በባጢል ላይ የጭፍን እልህ (ደራ) ባለ ቤት የሆነው የሙነወር ልጅ የሚደርስባቸውን ጠንካራ ምላሽ ይመክትልኛል ብሎ የያዘው መንገድ (ስልት) "በማስረጃ ማሳመን ካልቻልክ አደናግር" የሚለውን አባባል ነው።
ይህ የትም አያደርሳቹም!! ቲፎዞ እንዳይበተን ተጨንቆ ባለ በሌለ ሀይል ስራዬ ብሎ ለማደናገር መሯሯጡና አድፍጦ መጠበቁ የባጢልና የፖለቲካ ባለ ቤቶች መገለጫ ነው!!። ከእልህና ከትቢት ውጥረት ውጡና ትላንት የነበራችሁበት የሐቅ አቋም ላይ ሁኑ!! ለዱኒያቹም ለአኼራቹም የሚጠቅማቹ እሱ ነው።
🔸የሙነወር ልጅ ትላንት ከሶስት/ከአራት አመታት በፊት፣ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ (የነሲሃ) አመራሮች በድብቅ እየተሸማቀቁ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር በኢፍጣር ሰኣት የተነሱትን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቆ "ነጭ ነጯን እንናገራለን" በማለት የጀመረውን ምላሽ የት አደረሰው? ወይስ የመርከዙ ሰዎች ከዛ በኋላ ደንግጠው ተውበት አድርገው ትተውት ወደ ሱናው ተመልሰው ነው?! በጭራሽ!!
የመርከዙ ሰዎችማ ከትላንቱ መደባበቅ ወጥተው ስለ ዲናቸው ጠንከር ያለ እውቀት ለሌላቸው ነጋዴዎች እንኳን ግልፅ በሚሆን መልኩ በአደባባይ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደባለቃቸውን አውጀዋል። በኮንፈረንሶቻቸውና በተለያዩ ዝግጅቶቻቸው ከአል ኢኽኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ከቱባ ቱባ መሪዎች ከነ ጀይላን፣ ኢብራሂም ቱፋና ሙሀመድ ሃሚዲን… መሰሎች ጋር ሆነው አንድ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ሆነው ፎቶና ቪዲዮ በመልቀቅ ለህዝቡ በግልፅ አሳይተዋል። ከዚህም ባሻገር በየ ቦታው (በከተማ በገጠሩ) ከኢኽዋኖች ጋር ሆነው መጅሊስ ውስጥ ተሰግስገው የመንግስት የፀጥታ አካላትን በማሳሳት የሰለፊያ ደዕዋን ለማደናቀፍ እየታገሉ ነው። በነዚህ ሰዎች ላይ ብዕርህ ለምን ደለዶመ?!
🔸 የሙነወር ልጅ ሆይ! እስቲ ልጠይቅህ ለማደናገር መፍጨርጨርህን ትተህ በግልፅ ተናገር፣ ዛሬ ላይም እነዚህ የመርከዙ አመራሮች አንተ ዘንድ ሰለፊይ ናቸው?!
የጀርህና ተዕዲልን ነጥብ ጉዳይ አቆየውና ይህን ጥያቄ መልስ፣ ምክንያቱም አንተ ስለ ጀርህና ተዕዲል ነጥብ የእውቀቱም ሽታ የለህም!! ለዚያም ነው "ውሃ ሲወስድ ውሃ ይጨበጣል" እንደሚባለው፣ ጭልጥ ወዳለው የተምይዕ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በዚህ ርእስ ላይ ይረዳኛል ያልከውን አሰስ'ገሰሱን ኮተቱን ሁሉ ምኑንም ከምኑም ሳትለይ ከተለያዩ ዌብሳይቶች እየለቃቀምክ የነበረው። ይህ አላዋጣ ሲልህ ነው
ሰለፊዮችን አድፍጠህ ጠብቀህ የተቆራረጡ የሰለፊዮችን ቃላቶች እየመረጥክ በቃላት ስንጣ የተጠመድከው።
- ያ ሁሉ በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ የነበረህ ሀይል የት ገባ?! ተውበት አድርገው ሁላቸውም ሰለፊዮች ሆነው ነው ወይስ አንተ ወደ ባጢል ሰዎች ተውበት አድርገህ ነው በሱንና ሰዎች ላይ አንበሳ በቢድዐህ ሰዎች ላይ ሬሳ የሆንከው?!
ለቀድሞዎቹ ኢኽዋኖችና ለቅርብ ጊዜዎቹ የነሲሃ ቲቢ ባለቤት ኢኽዋኖች ሽንጥህን ገትረህ ትከላከላለህ፣
በቀድሞው አቋማቸው የፀኑ መፅሃፍህን መቅደም በማድረግ ሲያበረታቱህ የነበሩ ጠንካራ የሱንና መሻይኾችን ደግሞ የተለያየ ጥላሸት በመቀባትና ውሃ በማይቋጥሩ ነገሮች በመተቸት ሰዎች እንዲርቋቸው ለማድረግና ጭፍን ተከታይ ቲፎዞዎችህ እንዲቆዩልህ ትፍጨረጨራለህ!!። በዚህ ስልትህ ጭፍን ተከታዮችህን ከጥመት ቡድኖች ጋር እንዲግበሰበሱ አድርገሃል።
ይህ ነው አይን ያወጣ ያፈጠጠ ጥመትና የተምይዕ ዋሻ መሆን። ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “
ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571]
አላህ ከጭፍን ተከታይነትና በባጢል እልህ ውስጥ ከመግባት ጠብቆ እሱን እስክንገናኘው ድረስ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ
t.me/IbnShifaየተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifahttps://telegram.me/IbnShifa