እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት?
#8
ትዕግስት እና ባህሩ የሁሉንም ታሪክ እየሰሙ እየጠጡ እያለ ሳባ ዞረችና "ቆይ የሰውን እየሰሙ ግፍ አይሆንባችሁም?! በይ ቲጂ ተናገሪ አንፋታችሁም" ስትል ሁሉም "አዎ... አዎ" ብለው ተስተካክለው ወደ እነሱ ዞረው ተቀመጡ "የሚወራ የተለየ ነገር ስሌለው እኮ ነው" ብላ ዝም አለች ኧረ እንዴ ተንጫጫንባቸው
"እሺ እኔ እነግራችኋለሁ ግን ብዙ drama እንዳትጠብቁ ቲጂ እንዳለችው ነው የሚወራ ነገር የለውም።' ብሎ ባህሩ ቀጠለ መቼም ሰፍ ብለን አፉ ጋር ደርሰናል።
"ተዋወቅን ...ስንተዋወቅ "she is the one" የሚል ስሜት አልተሰማኝም ወይም ብቻ.... እንደማንኛውም ሰው ነው የተዋወቅነው ዩኒቨርሲቲ መጨረሻ አመት ላይ ነው አንድ ክፍል መሆናችንን ራሱ ያወቅኩት በresearch ሰበብ ጊዜ ስናሳልፍ እየተዋወቅን መጣን
እውነት ለመናገር ጓደኝነታችን ያመዝን ነበረ። ለዛ ነው እንደምትጠብቁት አይነት አይደለንም ያልኳችሁ። ከጓደኝነት የዘለለ ግንኙነት ስንጀምርም ተነጋግረን ወሰነን ነው እንጂ "በፍቅር ወድቀን" አይደለም ወይም ደግሞ ከሷ ጋር ስሆን የልብ ምቴ ስለሚዘባረቅ አይደለም ወይ "ቀልቤን ወስዳው" የለተለት ኑሮዬን አመሰቃቅላው አይደለም።
እንደውም የምመኘውን መረጋጋት እሷ ጋር ስለማገኘው ነው አብሬያት ነገዬን ማቀድ ስለምችል ነው አምኜበት ወስኜ የወደድኳት እንጂ ድንገት ከእንቅልፌ ስነቃ "ልቤን ከቦታዋ አጥቻት" አይደለም
ጉሮሮዋን እንደነገሩ ጠራርጋ
እኔም ብሆን ከሰው ተራ አውጥቶኝ ብዬ አላለቃቀስኩም ወይም ምግብ ትቼ ምናምና በየመፅሀፍ እና ፊልም ላይ እንደምናየው አልተቀያየርኩም እንደውም ራሴን የምጠብቅበት ሌላ ምክንያት ነው ያገኘሁት እና እንደምትጠብቁት አይነት ታሪክ ስላልሆነ ልንረዳችሁ አንችልም ብለው እጃቸውን ተያያዙ
ምንም ቃል የለኝም ቺርስ አለች ሳባ ብዙ ቺርሶች ተከተሉ
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss