የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
(ሜሪ ፈለቀ)
ክፍል 6
«ልጄ ዘመንሽን ሁሉ ክፉ ያደረጉብሽን ሰዎች ለመበቀል ስትዪ ነው የኖርሽው። እንደገባኝ ከሆነ ከበቀል እና ለወንድምሽ ከመኖር ውጪ ሌላ ልምድም ህልምም ስላልነበረሽ የጎዳሽን ሰው ካጠፋሽ በኋላ አንቺ የምትኖሪለት ነገር አጥተሽ ነበር። ልጄ የበደሉሽን ይቅር በይ፣ ራስሽን ይቅር በይ! ለፍቅር በፍቅር ለመኖር ራስሽን አስለምጂ! እግዚአብሄር አዲስን እድል ሰጥቶሻል።» አሉኝ ከጉልበታቸው ላይ ሳልነሳ ብዙ ደቂቃዎች ወይም ሰዓት ካለፈኝ በኋላ
«አባ ለምንድነው ብዙ የሚያውቁት ነገር ያለ ግን ያልነገሩኝ የሚመስለኝ?»
«የማይበጅሽን ብነግርሽ ምን ሊጠቅምሽ ልጄ? ስላሴ ከጭንቅላትሽ ብን አድርጎ ያጠፋው ባይጠቅምሽ አይደል? ወይም ለጊዜው ባያስፈልግሽ? »
«አባ ያለትናንት ዛሬን መኖር ይቻላል? ትናንት የሌለበትስ ዛሬ አለ? እያንዳንዱ ከሰዎች ጋር የሚያያይዘኝ ገመድ ከትናንት ጋር የተጋመደ አይደለም? ቤተሰቦቼም እኮ ትናንቴ ውስጥ የነበሩ ናቸው። እሺ ካልነገሩኝ እናቴን ወይ ወንድሜን እንዴት አገኛቸዋለሁ?»
«የሚጠቅምሽን መረጃ አልደብቅሽም ልጄ። ስለእናትሽ ብዙም አላወራሽኝ ስለወንድምሽ ግን አውርተሽ አትጠግቢም። ስሙን በየእለቱ የምትደጋግሚው ስለሆነ አልዘነጋሁትም። ኪዳን! አዎ ኪዳን ነው።» ጀርባዬ ላይ በትልቁ የተነቀስኩት የወንድሜን ስም ነው ማለት ነው። «ጥይምናው እና ፈገግታው ያንቺው ነው።» ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉልበታቸው ቀና አልኩ
«እንዴ አባ ያውቁታል? አብሮኝ መጥቶ ያውቅ ነበር?» አልኩኝ በጉጉት
«እንደዛ አይደለም ልጄ! በስልክሽ ነው ምስሉን ያሳየሽኝ። » ጠይም ሳቂታ .......... የአልጋዬ ኮመዲኖ ላይ ያለው ፎቶ ነው የሚሆነው
ስልኬ! ......... እንዴት እንደምከፍተው ማወቅ አቅቶኝ መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጥኩት መስታወቱ የተሰነጣጠቀ ስልኬ! ቀና ብዬ ጎንጤን አየሁት። ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ
«አባ ልሂድ በቃ! ብመጣ አገኝዎታለሁ? »
«አለሁኝ ከቤቱ የት እሄዳለሁ? (ወደ ሰማይ መልከት አደረጉ) በአይንሽ ካጣሽኝ መልከፃድቅን ጥሩልኝ በይ!» የለበስኩትን እያጤኑ «ለምስጋና እንደመጣሽ አምኜ አምላኬን አመሰግናለሁ» አሉኝ። መጨረሻ ላይ የተናገሩት እንዳልገባኝ ገብቷቸው ፈገግ እያሉ። «ሁሌም ስትመጪ ሌጣሽን ያለክንብንብ ደግሞም የክፉ ነገሮች ምስል ያለበት ልብስ ለብሰሽ ነበር። አንድ እለት ከጀርባው ትልቅ የእባብ ምስል ያለበት ጃኬት አድርገሽ 'ምነው ልጄ ከጀርባሽ ፈልገሽው ነው?' ብልሽ። ' ከእግዚአብሄር የታረቅኩ ቀን ለምስጋና ስመጣ ቀሚስ ለብሼ ነጠላ ደርቤ እመጣለሁ።' ብለሽኝ ነበር።» አሉኝ።
እቤት የምደርስበት ሰዓት እርቆብኝ ከደረስኩ በኋላ ከስልኬ ጋር ተፋጥጫለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምስላቸው የሌሉ ነገሮችን እንኳን ስይዛቸው በደመነፍስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። ለምንድነው ስልኬን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ የገባኝ?
«ባትሪ ያለው አልመሰለኝም! እንዱለው ይሆን?» አለኝ ጎንጤ አለማወቄ ቢገባውም እንዳያሳፍረኝ በመጠንቀቅ ዓይነት። አቀበልኩት። ተቀብሎኝ ግድግዳው ላይ ተሰክቶ ገመዱ የተዝረከረከ ገመድ ብድግ ሲያደርግ የሚቀጥለው ሂደት ጫፉን ስልኩ ላይ መሰካት እንደሆነ አውቃለሁ። የሆነ አለ አይደል ሰው መንገድ ጠፍቶበት ልክ ቤቱን ሲያየው ይኸው እንደሚለው ዓይነት ነገር?
አባ 'እግዚአብሄር ጭንቅላትሽን እንደህፃን ልጅ ነጭ ወረቀት አድርጎ ሰጥቶሻል፣ የሚቀጥለውን ዘመንሽን አስተካክለሽ ፃፊበት' ይበሉኝ እንጂ እንደህፃን ነጭ ወረቀት የሆነ ጭንቅላት እንዳልቀረኝ አውቃለሁ። እንደህፃን እንዴት እንደምበላ ከ 'ሀ' አልጀመርኩም ወይም አፌ አልጠፋብኝም፣ መራመድ ለመቻል ከመዳህ አልጀመርኩም ፣ 'ኡፉ ነው' ባልባልም እሳት እንደሚፋጅ ሳየው አውቄያለሁ፣ ሽንቴን ልብሴ ላይ ይሁን ሽንት ቤት የምሸናው ሳላውቅ እላዬ ላይ አልለቀቅኩም፣ ሱሪ ለመልበስ በአንገቴ አላስገባሁም ወይም ጫማ ለማጥለቅ ግራ አልተጋባሁም፣ አልጋ ሳይ ይሄ መተኛሽ ነው ሳልባል ገልጬ ውስጥ ገብቼ ተኝቻለሁ ፣ የጥርስ ብሩሽ ሳይ ምንም ሳልጠይቅ እጄ አንስቶ ጥርሴን ቦርሿል .........
2. ስልኬ
ስልኬ ለመጀመር የሚያስችለውን ባትሪ ሲያገኝ ራሱ ከፈተ። እስክሪኑ ሲበራ ዘልዬ አጠገቡ ደረስኩ እና አነሳሁት። ያ አልጋዬ አጠገብ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ዓይኖች ያሉት ፎቶ ይታያል። ራሱ ነው! ኪዳን ነው። ትልቅ ሰው ሆኖ! ይሄን ምስል ሳየው እስከአሁን ምስሎቹን በወረቀት ሳየው ከተሰማኝ የተለየ ስሜት ተሰማኝ። የሆነ የሚያፍን ፈንጠዝያ! ልቤ ሰውነቴ ውስጥ ይነጥር ጀመር። ስልኬን በችኮላ ብነካካውም በኮድ ተዘግቷል። ተስፋ ቆርጬ መሬቱ ላይ እንደተቀመጥኩ
«እትዬ ስልኮትን በፊትዎት ነው ሲከፍቱ ያየሁት!» አለችኝ። እንዳልገባኝ አውቃ ስልኩ እጄ ላይ እንዳለ ወደ ፊቴ ስታቀርበው እውነትም የኮድ ምልክቱ ተነሳ። የሚቀጥለውን ፍለጋዬን ለማድረግ በረጅሙ ተነፈስኩ። ወዲያው ስልኩ በመደዳ የማያቆም ተደጋጋሚ ድምፅ ያሰማ ጀመር። ለምን እንደሆነ ድምፁ ረበሸኝ። የሆነ ቀጥሎ መጥፎ ክስተት ይከሰት ይመስል ጭንቅላቴን ወጠረኝ። መሬቱ ላይ አስቀመጥኩት። የሆነ ግጭት ጭንቅላቴ ውስጥ የተከሰተ መሰለኝ። የሆነ የተኩስ ድምፅ ነገር።
«ምነው እትይ? አመሞት እንዴ? » ወድያው አስከትላ «ጎንጥ! አንተ ጎንጥ» ጆሮዬ ላይ አምባርቃ ተጣራች። በረንዳው ላይ የነበረ መሰለኝ
«ምንድነው?» ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«እኔእንጃ የስልኩ ድምፅ ረበሸኝ።» አልኩት ስልኩን ካስቀመጥኩበት አንስቼ እያቀበልኩት።
«ደውሎ ያጣዎትን ስልክ መልእክት እየላከልዎት ነውኮ! ሌላም መልዕክቶች አሉት።»
«የሚጠቅም ነገር ካለው አንብብልኝ» አልኩት ልቤ ለምን እንደፈራ ሳላውቀው እየተርበተበተብኝ። ዝም ብሎ ስልኩን ሲነካካ ቆይቶ
«ሾካካ የሚባል ሰው 'ዛሬ ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ ስለሚመጡ ቤቱ ይፅዳ' የሚል መልዕክት ልኮልዎት ነበር። ኦው ብዙ መልዕክት ነው የላከው። 'ምነው ዘጋሽኝ? በሰላም ነው ስልክሽ የማይሰራው?'......... 'ኸረ ምንድነው ጉዱ አንቺ ሳትኖሪኮ ቤቱ ስርዓት አጣ! '...... »
«ተስተምረሃል እና?» አለች ተናኜ በጣም በተገረመ አባባል አገጭዋን በእጅዋ ደግፋ ጎንጤን እያየችው። እሷ ማንበብ እንደማይችል እንዴት አሰበች እኔ እንዴት እንደሚያነብ እርግጠኛ ሆንኩ? አላውቅም! እሱ ተናኜን ቁጣና ግልምጫ ደባልቆ ለግሷት ወደንባቡ ሲመለስ የሚያነብበት ስልት እና ፍጥነት ስለእርሱ ብዙ የማላውቀው ነገር እንዳለ እንድጠረጥር አደረገኝ።
« ........ 'ሜሉ መላ ሳይገባልኝኮ ሁለት ሳምንት ተቆጠረ.' ........... እእ 'መታመምሽን በወሬ ሰማሁ መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ቤትሽን የሚነግረኝ አጣሁ። ብደውል ስልክሽ አሁንም ዝግ ነው።'»
«ራሱ ሾካካው ነው?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ሁለቱም እኩል ሲስቁ አባባሌ ራሴንም አሳቀኝ! ጎንጤ ሳቁን ሲገታ «አዎ ራሱ ነው!........ ' አንቺ በቅርቡ የማትመለሺ ከሆነ ለዳዊት መላዬን እንዲቆርስልኝ ንገሪልኝ ዛሬ ሄጄ ስጠይቀው የማውቅልህ ነገር የለም ብሎ አባርሮኛል።' ......... እ ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር........