የለህማ
ደሞ ደሞ
ነገር ጠሞ
ከግጥምጥም...ክፉ ተርታ
የቋጠርኩት...እስኪፈታ
ወንድነቴ...እስኪረታ
ትንሽ ያልኩት...እስኪንቀኝ
ያቀረብኩት...እስኪርቀኝ
አማረ ያልኩት...ቢያሳቅቀኝ
የሞላሁት...ቢጎዳድል
የታገልኩት...ቢያረገኝ ድል
ቀን ቢያጎርሰኝ...ክፉን ዕድል
ቀና ብዬ ወደሰማይ
ሽቅብ ሽቅብ አየሁና፤
በታከተው
ሆድ በባሰው፥በቸኮለ፥ ባዶ ህሊና፤
እግዜርን አልኩ
የ.ለ.ህ.ማ...!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ
እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
ደሞ ደሞ
ነገር ጠሞ
ከግጥምጥም...ክፉ ተርታ
የቋጠርኩት...እስኪፈታ
ወንድነቴ...እስኪረታ
ትንሽ ያልኩት...እስኪንቀኝ
ያቀረብኩት...እስኪርቀኝ
አማረ ያልኩት...ቢያሳቅቀኝ
የሞላሁት...ቢጎዳድል
የታገልኩት...ቢያረገኝ ድል
ቀን ቢያጎርሰኝ...ክፉን ዕድል
ቀና ብዬ ወደሰማይ
ሽቅብ ሽቅብ አየሁና፤
በታከተው
ሆድ በባሰው፥በቸኮለ፥ ባዶ ህሊና፤
እግዜርን አልኩ
የ.ለ.ህ.ማ...!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ
እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....