👆
"የታላቁ አንዋር መስጅድ አካል የሆኑ ሱቆች እንዳይነሱ የከተማ አስተዳደሩ የፕላን ማሻሻያ አድርጓል፡፡"
ኢ/ር ታከለ ኡማ
**********************************ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኡለማዎች እና የቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከዚህ ቀደም በህዝበ ሙስሊሙ ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በሚል ከእምነቱ ተከታዮች እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ በደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያም ተነጋግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት የይዞታ ጥያቄዎችን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሌሎች የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በመንገድ ግንባታ ምክንያት ሊነሱ የነበሩ የታላቁ አንዋር መስጅድ አካል የሆኑ ሱቆች እንዳይነሱ የከተማ አስተዳደሩ የፕላን ማሻሻያ እንዳደረገም
ኢ/ር ታከለ ኡማ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የጋራ በሆኑ አጀንዳዎች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
@kushmedia