15 የሕግ ባለሞያዎች የግልግል ዳኝነትን ለመጀመር ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረቡ
#Ethiopia | በኢትዮ ሌግዠር ሆምስ ስር የተደራጁንና በአብዛኛው በዳኝነት፣ በጥብቅና ከ25 ዓመታት ባለይ መስራታቸውን የተናገሩ 15 የህግ ባለሞያዎች የግልግል ዳኝነትን ለመጀመር ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናገሩ፡፡
በዚህም በ2013 ዓ.ም ከወጣው የግልግል ዳኝነትና የዕርቅ አሰራር ስረዓትን ለመደንገግ ከወጣው አዋጅ በኋላ በዘርፉ ለመሰማራት ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ በማቅረብ የመጀመሪያዎቹ መሆነቸውን ነግረውናል፡፡
የኢትዮ ሌግዠሪ ሆምስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በዳዳ ገመቹ ይህንኑ ጥያቄ ህዳር 20፣2017 ለፍትህ ሚኒስቴር ማቅረባቸውን አስድተዋል፡፡
በተለይ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ ነክ አለመግባባቶችን ለመፍታት የግልግል ዳኝነትና የእርቅ አሰራርን መዘርጋት ጥቅሙ የበዛ መሆኑ ይታመንበታል፡፡
የግልግል ዳኝነትና የእርቅ አሰራር የቢዝነስ አቀላጣፊዎች አለመግባባት ሲያጋጥማቸው ከመደበኛው የፍርድ ቤት ይልቅ ወጪ በመቀነስ ፣ ምስጢርን በመጠበቅ ፣ ልዩ ሞያ ያላቸው ባለሞያዎችና በዳኝነት እንዲሳተፉ በማድረጉ ተመራጭ መሆኑ ይነገርለታል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንኑ አምናበት እዚህ የተነሱት ነጥቦች በአዋጇ ጠቅሶ አራት ዓመታት በፊት የግልግል አዋጅ አውጥታለች፡፡
በግልግል ዳኝነት፣ የፍቺ፣ የጉዲፈቻ፣ የወንጀል ጉዳዮች፣ የግብር ጉዳዮች፣ መክሰር ላይ የሚሰጥ ውሳኔ ፣ አጠቃላይ የመሬት ጉዳዮች እና ሌሎች በህግ የተከለከሉ ጉዳዮች አይታዩበትም፡፡
በተለይ ንግድ ነክ የሆኑ ማለትም እቃዎችን ወይንም አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወይንም ለመለዋወጥ የሚደረግ የንግድ ግንኙነት፣ ለማከፋፈል የሚደረግ ስምምነት ፣ የንግድ ወኪልነት ፣ ማማከር፣ የምህድስና ፣ የባንክ የኢንሹራንስ የመሳሰሉት በግልግል ዳኝነት መታየት የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡
ይህንና ሌሎች ጉዳዮችን የሚያስረዳው የግልግል ዳኝነትና የእርቅ አሰራር ሥርዓት አዋጅ ከወጣ አራት ዓመት አልፈው ከዚህ ወዲህ ምን ሆነ? አዋጁስ ተንተርሰው በዘርፉ ለመሰማራት የፈለጉ አሉ ወይ?
ጥያቄውን ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርበን ቀጠሮ ሰጥተውን የነበረ ቢሆንም መልሱን ግን አልነገሩንም፡፡
በኢትዮ ሌግዠር ሆምስ ስራ የተደራጀው የህግ ባለሞያዎች ይህንን አዋጅ ተንተርሰው ስራውን ለመስራት ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ነግረውናል፡፡
"እኛ አስከምናውቀው ድረስ ይህንን አዋጅ ተከትሎ ፈቃድ የጠየቀ ግለሰብም ሆነ ድርጅት አንደሌለ ለማጣራት ጥረት አድረገናልል፡፡ ምንም የለም'' ብለዋል
ስለዚህ የግል ዳኝነትና የእርቅ ስረዓቱን ለመደንገግ መንግስት ባወጣው አዋጅ መሰረት ተደራጅተን መጥተና፣ ፍቃድ ስጡን ያልን የመጀመሪያዎቹ ነን ምን አልባት የንግድ ምክር ቤትየሚሰራበት እንዳለ አናውቃለን፣ ዝርዝሩንባናውቅም ከዚህ አዋጅ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ድሮ ጀምሮ የሚሰሩበት ነው፡፡
አዋጁ ከወጣ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ሌግዠሪ ሆምስ የግልግል ዳኝነት ጥያቄ የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለን አናምናለን ብለዋልየኢትዮ ሌግዠሪ ሆምስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገመቹ።
በአዋጅ ተለይቶ ከተሰጠባቸው ስልጣን በስተቀር በግልግል ዳኝነት በሚታዩ ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቶች ጣልቃ አይገቡም፡፡
ABEL👇👇👇👇👇👇
http://t.me/lawabelethiohttp://t.me/lawabelethiohttp://t.me/lawabelethiohttp://t.me/lawabelethiohttp://t.me/lawabelethio