مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ ቻነል ከፉሪ ወደ ዑመር ኢብኑ ዓብዱልዐዚዝ መስጂድ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ኑሪ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአል ኢስላሕ መድረሳ የቴግራም ቻናል ነው!!!! በአላህ ፍቃድ በመድረሳው የሚሰጡና በተለያዩ የሰለፊያህ ዱዓቶች፣ ኡስታዞችና መሻኢኾች የሚተላለፉ መልዕክቶች (በድምፅም ይሁን በፅሑፍ) ይተላለፉበታል!!!!
https://t.me/medresetulislah

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


قَـال شَـيخُ الإسلاَم ابن تَيمِيَّـة -رحمَـه الله تَعـَالَـى-:

‏”مـن أعرض عن اتباع الحق الذي يعلمه تبعا لهواه فإن ذلك يورثه الجهل والضلال حتى يعمى قلبه عن الحق الواضح“

‏🔦انظر: [📚مجموع الفتاوى 10/ 10 ]
نقله شيخ حسين بن محمد السِّلطي


☑️እርምት ለኸድር አልከሚሲይ: 2

الجرح المفسر مقدم …

🟥 የርዕሱ አሳሳቢነት ለሁላችንም

🟥የሀዲስ ዑለማዎች መንሃጅ

🟩 አደገኛ የሆኑ አዳዲስ መርሆችን መጠንቀቅ


ሸይኽ ሁሰይን ሙሀመድ ለከኸድር አህመድ ከፃፈው እርምት (ረድ) የተወሰደ ጠቃሚ የመንሃጅ ትምህርት።


ከፍል 3 ይቀጥላል🔘🔘🔘

🎤ሸምሱ (አቡ ሀመዊያህ)
http://t.me/Abuhemewiya


ጀግና ሴቶች dan repost
የእብድ ውሻ በሽታ እና መውሊድ

በዲን ላይ አዲስ አምልኮ (ቢድዓህ) ምንኛ መርዛማ በሽታ መሆኑን ከሚጠቁሙ ሀዲሶች አንዱ:
عن مُعَاوِيَةَ بْنِ أَبِي سُفْيَانَ ، أنه قَامَ حِينَ صَلَّى صَلَاةَ الظُّهْرِ، فَقَالَ : إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " إِنَّ أَهْلَ الْكِتَابَيْنِ افْتَرَقُوا فِي دِينِهِمْ عَلَى ثِنْتَيْنِ وَسَبْعِينَ مِلَّةً، وَإِنَّ هَذِهِ الْأُمَّةَ سَتَفْتَرِقُ عَلَى ثَلَاثٍ وَسَبْعِينَ مِلَّةً - يَعْنِي الْأَهْوَاءَ - كُلُّهَا فِي النَّارِ إِلَّا وَاحِدَةً، وَهِيَ الْجَمَاعَةُ، وَإِنَّهُ سَيَخْرُجُ فِي أُمَّتِي أَقْوَامٌ تَجَارَى بِهِمْ تِلْكَ الْأَهْوَاءُ كَمَا يَتَجَارَى الْكَلَبُ بِصَاحِبِهِ، لَا يَبْقَى مِنْهُ عِرْقٌ وَلَا مَفْصِلٌ إِلَّا دَخَلَهُ ". الحديث :مسند أحمد
حسنه الألباني: (صحيح أبي داود 4597 )

…የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ《 ሁለቱ የመፅሀፍ ባልተቤቶች እኮ በሀይማኖታቸው ወደ ሰባ ሁለት መንገዶች ተለያይተዋል። ይህችም ህዝብ እኮ ወደ ሰባ ሶስት መንገዶች ትለያያለች። አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው። አንዷም (የምትድነዋ) አልጀማዐህ ነች። እነሆ በኡማዬ (በህዝቦቼ) ውስጥ ልክ የእብድ ውሻ በሽታ በበሽተኛው ላይ እንደሚሰራጨው በሰውነታቸው ውስጥ እነዚህ ስሜቶች (ቢድዓዎች) የሚሰራጩባቸው ሰዎች ይወጣሉ። እርሱ ያልገባበት ደምስርም ይሁን መገጣጠሚያ አይተርፍም።

የመውሊዱ ሰዎች

በቢድዓህ መርዙ ስለተመረዙ
በስሜት ተውጠው ሰክረው አየጦዙ
ከደማቸው ገብቶ ታስሮ ካጥንታቸው
በመውሊድ መፈንደቅ ውዴታ መስሏቸው
ውዴታና እብደት ተገላብጦባቸው
እንዳበደ ውሻ ሲያክለፈልፋቸው
መረጃ በሌላው ባዶው ጩሀታቸው
ጤነኛውን ሁሉ መንከስ አማራቸው
ሀዲሱን በተግባር በነርሱ አየነው




✍ሸምሱ ( አቡ ሀመዊያህ)
http://t.me/Abuhemewiya


☑️እርምት ለኸድር አልከሚሲይ 1⃣

الجرح المفسر مقدم …

🟩በማስረጃ የተብራራን ትችት መቀበል

🟩 አደገኛ የሆኑ አዳዲስ መርሆችን መጠንቀቅ


ሸይኽ ሁሰይን አስልጢይ ለከኸድር አልኸሚሲይ ከፃፈው እርምት (ረድ) የተወሰደ ጠቃሚ ትምህርት።


ከፍል 2 ይቀጥላል🔘🔘🔘

🎤ሸምሱ (አቡ ሀመዊያህ)
http://t.me/Abuhemewiya


ሳሊህ አህመድ ስለ ሰምምነቱ ከዱዓቶች ጋር የተነጋገሩበት መሆኑን
በፊት ያደረጋችሁትን ረድ አድርጉ የሚሉ እንዳሉና እንደማይቀበሉት በስምምነቱ እንደሚካፈሉ
ጥፋት ካዩ ዝም እንደማይሉ ይነግረናል ።
ታዲያ ጥፋት ስታዩ መልስ ሰጣችሁ ?ይህ ባጢል ነው አላችሁን ?
ወይስ የሰማችሁትና ያያችሁት ባጢል አልነበረም ? እንላቸዋለን ።




ኢልያስ አሕመድ ስለ አሁኑ ስምምነት የተናገረው
አብዛኞቹ በፅሑፉ ላይ ስለ ተነሱ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ብቻ ላንሳ በስምምነቱ ላይ የተሳተፉት ታላቁ ዓሊም ያሉዋቸው አይነት ሰዎች ናቸውን ?
እዛ ላይ የተሰሱትን ባጢሎች መልሰዋልን ?


ኢልያስ አሕመድ የማዘጋጃ ቤቱን ስምምነት ውቀድቅ መሆኑና የሁደይቢያ ስምምነት እንደማይመለከተው
በባጢል እጅ ለእጅ ተጨባብጦ አንድ ነን ማለትን የወገዘበት


Bahiru Teka dan repost
🔷 የመርከዙ ሰዎች የተምዪዕ ማረጋገጫ
ክፍል አምስት
🔹ከአህባሽ ከሱፍይና ከኢኽዋን ጋር አንድ መሆን ( መደመር )
ኢብኑ መስዑዶች ቀስ በቀስ ወደ ለዘብተኛ አካሄድ በጥንቃቄ እየተጋዙ የሱናው ማህበረሰብ ለዝቧል ከኛ አይወጣም የሚሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ወደ መደመር አቀኑ ። እንደ ጠበቁት ባይሆንም እነርሱ ወይም ሞት የሚል ሙሪድ አላጡም ። እነርሱ የሰሩት ነገር ሁሉ ያለ ምክንያት አይደለም እኛ ስለማይገባን ነው በማለት ራሳቸውን ያሳመኑና ምንም ቢሰሩ ትክክል ናቸው ብሎ ዑዝር ለመስጠት የተዘጋጁ ሙሪዶችን በተዋጣለት ሁኔታ በማፍራት ከሱፍይ ሼኾች የበለጡበትን እውነታ አረጋገጡ ።
እዚህ ጋር ሊጤን የሚገባው የአንድነት ስምምነቱ ላይ የተሳተፉት ተራ ሰዎች ሳይሆኑ የተቋሙ መሪዎች ናቸው ። የማንኛውም ተቋም ወይም ጎሳ ወይም ሀገር አቋም ያ አካል በሚልካቸው ተወካዮቹ አማካይነት ነው የሚገለፀው ። በመሆኑም እዛ ላይ የተንፀባረቀው የተቋሙ አቋም እንጂ የግለሰቦች ነው ማለት ራስን ከሟሞኘት ያለፈ ውጤት የለውም ።
ኢብኑ መስዑዶች በዚህ አንድነት ላይ እንደ ተቋም ሲሳተፉ ሁለት ሰዎች በራሳቸው ጊዜ ሄደው የግል ሀሳባቸውን ያቀረቡበት ሳይሆን በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ተደርገው ተነጋግረውበት ለመሆኑ ከራሳቸው አንደበት እንሰማዋለን ። ይህን ለማስተባበልና እንዳልሆነ ለማድረግ የሚጥር ቢኖርም ።
መንግስት አንድ የሙስሊሞች ተቋም ሊኖር ይገባል አንድ ሆናችሁ ኑ ብሏል ብለው !!!! ከአሕባሽ ፣ ከዓሻኢራ ፣ ከኢኽዋን ፣ ከሱፍያና የመሳሰሉ አንጃዎች ጋር ሁሉም የራሳቸውን ተወካይ በመላክ አሕባሽና ኢኽዋን በመራው መድረክ አንድነታቸውን ከተቀመጡበት በመነሳት ከእነዚህ የጥመት አንጃዎች ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ አረጋገጡ ።
🔹 የአንድነቱ ( የስምምነቱ ) መሪ ቃል
ከእንግዲህ ተብሊጊ ፣ ኢኽዋኒ ፣ ሰለፍይ የሚባል ነገር የለም ሁላችንም የኢትዮጥያ ሙስሊሞች ነን ።
🔹የጉባኤው ረእስ
የኢትዮዽያ ዓሊሞች የአንድነትና የትብብር ጉባኤ !!!!!
በጉባኤው ላይ ከተከሰቱ ከእስልምና ሊያስወጡ የሚችሉ የኩፍር ንግግሮች ውስጥ
የፕሮፌሰር ተብዬው ቅርሽት
" ስለዚህ እኛ እድሉ መጥቶልናል , ከዚህ የበለጠ እድል ወላሂ ወቢላሂ ከአሁን በኋላ ሙሳም ቢመጡ ፣ ዒሳም ቢመጡ ፣ ነብዩና ሙሐመድም ቢመጡ ከዚህ የበለጠ እድል " እያለ በጎደለ ሙሉ ብሎ በስሜት የሰከረና ያሰከረ ንግግር ይገኝበታል ።
የዚህ ንግግር አደጋ
– ሶስት ዑሉል ዐዝሞችን ከሙርተድ ጋር ማነፃፀርና የሱ ስርአት መብለጡን መስበክ
– የሰው ሰራሽ ህግ ከመለኮታዊው ህያው የአላህ ቃል ማስበለጥ
– ይህንን በመሀላ ማረጋገጥ
🔹 የኢብኑ መስዑዶች አቋም
ስምምነታቸውን ከተቀመጡበት በመነሳት እጅ ለእጅ ተያይዞ ከፍ በማድረግ መግለፅ !!!!!!!
ይህ አቋም የግለሰቦች ሳይሆን የተቋሙ ለመሆኑና ተነጋግረውበት መሳተፋቸውን በሳሊህ አሕመድ ንግግር ታዩታላችሁ ።
በመሆኑም የተስማሙትና የተጨባበጡት ሁለት ሰዎች ናቸው እነርሱ ይጠየቁ ማለት መልስ አይደለም ። መልስ ሊሆን የሚችለው እነዚህን ሰዎች ከመሪነት አንስቶ ኢብኑ መስዑድን አይወክሉም ስምምነቱም መርከዙን አይወክልም ሲባል ካልሆነ እየአንዳንዱ ዳዒ ራሱን ከዚህ ተቋም አርቆ እኔን አይወክልም ሲል ብቻ ነው ።
🔹 ከስምምነቱ በኋላ ምን ሆነ?
ኢብኑ መስዑዶች ከወጡ በኋላ ይህ ስምምነት እኛን አይወክልም እዛ የተነሱ ሀሳቦች የሰለፍያን አቋም የሚፃረሩ ናቸው ከአቅማችን በላይ ስለነበረ ነው አሉ ?
በጭራሽ ከማንም በላይ ተቀብለውት በስሮቻቸው ያሉትን ዱዓቶች ባጠቃላይ ሀገሪቱ ስምምነቱን የሚፃረር ዳዕዋ እንዳይደረግ ስለኢኽዋን ፣ ስለዓሻኢራ ፣ ስለተብሊግ እንዳይነሳ ይህን ርእስ የሚያነሱ ኪታቦች እንዳይቀሩ በማድረግ በሁሉም ላይ ተግባራዊ እንዲሆን አደረጉ ።
በዚህ አላቆመም ይህን የተቃወመን የተለያየ ሰም በመስጠት ወሰን አላፊ ሀዳዲ በል አቡለሀብ እሰከ ማለት ደረሱ ።
ስለዚህ ጉዳይ በተለያየ መድረክ ሲጠየቁ መንግስት አንድ ተቋም ይኑራችሁ ስላለ 86 ገፅ ፅፈን መጅሊሱ በምን መልኩ መቋቋም አንዳለበት ሰጥተናል በዚህም ልንወደስ እንጂ ልንወገዝ አይገባም የሚል መልስ ይሰጣሉ !!!!!
ይህ ከጥያቄው ለመሸሽ የሚደረግ ማምታቻ ነው ። 86 ገፁ የት አለ ብትላቸው መልስ የላቸውም ወይም መጅሊስ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ነው የሚል ነው ሊሆን የሚችለው ። ቢሆንም ማንም በዚህ አልወቀሳቸውም 86 ገፅ መፃፋቸው የልዩነቱ ምክንያት አይደለም ። በወቅቱ እነርሱ ይጠቅማል ብለው ፃፉ እኛ መተዉ ሱና ነው ብለን በሱና ተርኪያ ሰራን ። ስለአሕባሽና ኢኽዋን ስለምናውቅ ።
ለምን እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣሉ ቢባል ምስኪን ሙሪዶቻቸውን ዝም ለማሰኘት እንጂ እራሳቸውም ያውቁታል ።ሌላው እኛ ምን አገባን ሄደው የተሳተፉና እጅ ለእጅ ተጨባብጠው የተስማሙት ይጠየቁ የሚል ነው ። ይህም ጉዳዩን የግለሰቦች ለማስመሰል ነው ። አይደለም እንደ ተቋም ተነጋግረውበት ተቋሙን ወክለው እንዲሳተፉ የተላኩ የተቋሙ መሪዎች ናቸው እንላቸዋለን ። በመሆኑም እኛ ሳንሆን እራሳቸው ተስማምተው ሰለፍዮች አይደለንም የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ነን ብለው በመውጣታቸው አው ሰለፍዮች አይደላችሁም ሙመዪዓዎች የኢተዮዽያ ሙስሊሞች ናችሁ የምንለው ። ከዚህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የድምፅ ፋይሎች አላህ ካለ ቀጥሎ ይቀርባሉ ።
https://t.me/bahruteka


Muhammed Mekonn dan repost
ሂድ ወደ ገጠሩ ተውሂድ መግባቸው ‼️
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️

ወጣቱ ተነሳ ሁልህም በአንድነት
ተውሂድን አስተምር ሽርኩ ይንኮታኮት
ቢድዓ ይወገድ የሱናችን ጠላት

በገጠር ላይ ያሉ ተውሂድ የጠማቼው
ብዙ ሰወች አሉ አኔ የማውቃቸው
እውቀት አልባ ሁነው አስተማሪ አጥተው
ጀግናየ ሂድና ተውሂድ መግባቸው
የረሱሉን ሱና በደንብ አሳያቸው
በሱና ይዋቡ ከሽርካሽርክ ወጥተው
ሽርክ እና ቢድዓን ከስሩ እጨደው
ደግሞ እንዳይነሳ ድቅቅ አድርገህ ጣለው
በሱ ቦታ ወስደህ ተውሂድን ትከለው

የሀገሬ ህዝብ በጣም የምወደው
የሰው ልጅን ክብር በደንብ የተረዳው
እንግዳ ተቀባይ ሰውን አክባሪ ነው

ነገር ግን አቂዳው በጣም ደካማ ነው
ተውሂድን አያውቅም አስተማሪም የለው
በሽርክ በቢድዓ የተዘፈቀ ነው
ለቀብር ለጅኑ ቁርባ የሚያቀርብ ነው
ብቻ በአጠቃላይ በሽርክ በሽታ የተበከለ ነው

ትንሽም ቢኖሩ የሱፍይ ሸኽ ናቸው
አኼራን የረሱ ዱንያቸውን ወደው
ከሽርክ ከቢድዓ ማስጠንቀቅን ትተው
አስረው ይዘውታል ምርኮኛቸው አድርገው

አላዋቂው ህዝብ እሱን እንዲያከብረው
ብሎ ይሰብካል እኔ
ላስጣችሁ ሀጃችሁ ምንድነው
ጫቴን እየቃምኩኝ ያረቢ እርዳኝ ብለው

እኔን ይሰማኛል ጌታየ ቅርብ ነው
ብሎ ይፎክራል ልክ አቅም እንዳለው
እነሱም ጃሂሎች እውቀት የሌላቸው
ሸኹ መጀን አሉ ይሰጣል መስሏቸው

አንተ ውድ ወንድሜ አድምጠኝ ልንገርህ
ሀቅን ከመናገር ወደ ሗላ ብለህ
አለባብሶ መሄድ መቼም ላያዋጣህ

ሀቅን ከማስተማር በጣም ተዘናግተህ
አኼራን ዘንግተህ ዱንያን አስቀድመህ
መቼም የማይቀር ነው
አንድ ቀን መሞትህ

ገጠር የሚገኙ ምስኪን ዘመዶችህ
ተውሂድ መግባቼው ከሽርክ አስወጥተህ


ወንድሞች እንንቃ ተውሂድን እንዝራው
ከተማ ገጠሩ አጭዶ እንዲበላው
ሽርክ እና ቢድዓን አራግፎ ይጣለው
ሸኹ ድረሱልኝ ማለቱን ይተወው
በጠዋትም በማታም
ተውሂድ እንመግበው
በሰለፎች መንገድ ጉዞውን ያድርገው


📝 ቢንት አህመድ አላህ ይጠብቃት

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


Bahiru Teka dan repost
🔷 ወንድማዊ ምክር
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው ብላችሁ ርእስ ቀይራችሁ ስሙን አጥፍታችሁ የራሳችሁን ስም ፅፋችሁ በቻናላችሁ ላይ የምትለቁ ይህ ተግባር በየትኛውም መመዘኛ ስህተት ነው ። ወንድሜ ሆይ እራስህን ለመሆን ሞክር , ምክንያቱም በሌላ የተሸፈነ ማንነት ሽፋኑ ተነስቶ መታየቱ አይቀርምና ። አንድ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ አይነት ተግባር አይጠበቅም እንኳን ወደ ሱና ከፍ ብያለሁ ከሚል ይቅርና ። አላህ ሰዎች እንኳን ባልሰሩት ስራ መመስገን ሊፈልጉ ይቅርና በራሳቸውም ስራ ሊመፃደቁ እንደማይገባ ካልሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَا أَتَوا وَّيُحِبُّونَ أَن يُحْمَدُوا بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا فَلَا تَحْسَبَنَّهُم بِمَفَازَةٍ مِّنَ الْعَذَابِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ"
آل عمران ( 188 )
" እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አታስብ ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታሰባቸው ፡፡ ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው ፡፡"
ይህ አንቀፅ የዚህ አይነቱ ተግባር የሙስሊሞች አለመሆኑን ነው የሚያሳየን ። በዲን ጉዳይ አንድን ንግግር ስንወስድ ንግግሩን ወደ ባለቤቱ ማስጠጋት አማና ዒልሚያ በመባል ይታወቃል ። የእውቀት አደራ ነው ። ይህ ከሌለ አደራ እንደመብላት ይቆጠራል ።
ትላንት ( ወደ አላህ ሽሹ ) በሚል ርእስ የፃፍኩትን ፁሁፍ አንዱ ተነስቶ ( ወደ አለህ እንሽሽ ) በሚል ርእስ ቀይሮ ስሙን አጥፍቶ በራሱ ስም በቻናል ላይ የለቀቀው መሆኑን ሲያሳዩኝ በጣም ነው ያዘንኩት ። ምን አይነት ትወልድ እያፈራን እንደሆነ ያውም በዲን ጉዳይ !!!!!
መልእክቱ ራሱ ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንራቅ የሚል ነው ። ከወንጀል ርቀን ተውበት አድርገን ወደ አላህ መጠጋት እንዳለብን ነው የሚመክረው ።
ታዲያ ያልሆኑትን ነኝ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
የሰውን ሐሳብ የኔ ነው እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለ?
ያልሰጡትን ሰጥቻለሁ እያሉ ወደ አላህ መሸሽ አለን ?
ሰው የፃፈውን ሽፋኑን ቀዶ ጥሎ በራስ ስም ሌላ ሽፋን አበጅቶ ለአንባቢ እያቀረቡ ወደ አላህ መሸሽ አለ እንዴ ?
ይህ ተግባር እኔንም ሆነ ሌሎች ሀሳባቸው የሚሰረቅባቸውን ወንድሞች አይጎዳም የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ሌሎችም ለካ እንዲህ ማድረግም ይቻላል እንዴ ብለው የዚህ አይነት የሐሳብ ሌብነት ውስጥ እንዳይገቡ ነው ለማስታወስ የተፈለገው ። እንጂ ተግባሩ የግለሰቡን ማንነት ከማሳየቱ ሌላ ፋይዳ የለውም እና ከእንደዚህ አይነት ተግባር እንጠንቀቅ ።
https://t.me/bahruteka


الرد_على_خضر_في_الجرح_المفسر_تم_الحفظ_تلقائيًا_تم_الحفظ_تلقائيًا.pdf
658.0Kb
👉 አዲስ pdf

الرد على خضر كمسي في الجرح المفسر.pdf

ኸድር አሕመድ ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ) “ጀርሀ አል-ሙፈሰርን" በተመለከተ ባንፀባረቀው የተሳሳተ አመለካከት ላይ የተሰጠ መልስ።

بقلم الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና በቅርብ ወደ አኼራ የሄዱት የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ በሆነው በሸይኽ ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Bahiru Teka dan repost
🔷 ወደ አላህ ሽሹ !!!!
በተለያየ የሀገራችን ክፍል በተለይ በሰሜንና ምእራቡ ያላችሁ ወንድምና እህቶች አባቶችና እናቶች ስቃዩና መከራው በየቀኑ እየጨመረ ይነጋል ሲባል እየጨለመ በሚመስል ሁኔታ ትክክለኛው ያላችሁበት ስሜት እናንተና አላህ ብቻ የምታውቁት ሲሆን ምድር ከመስፋትዋ ጋር የጠበበች ብትመስላችሁም የአላህ ፈረጀት ይመጣል ። አብሽሩ !!!!
በጭንቀት መሪነት እግራችሁ ወዳቀናበት ብትሸሹም በዋነኝነት በልባችሁ ወደ አላህ ሽሹ !! የፀፀት እንባ አንቡ !! ከሱ በስተቀር መጠጊያም መመኪያም ያለ መኖሩ እወቁ !! ከመከራ በኋላ ፈረጀት ፣ ከጥበት በኋላ የእዝነት ስፋት ከፅልመት በኋላ ንጋት መኖሩን አስታውሱ ።
በምድር ላይ የሚከሰት ማንኛውም በላእ በየብስም ይሁን በባህር ምክንይቱ የሰው ልጆች ሀጢያት ቢሆንም ከአላህ ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –
" وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا فَأَخَذْنَاهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ
الأعراف" ( 96 )
" የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር ፡፡ ግን አስተባበሉ ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው ፡፡"
አሁንም በሌላ የቁርኣን አንቀፅ እንዲህ ይለናል : –

" ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
الروم " ( 41 )
" የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና ፡፡"
አላህ ይህን መከራና ጭንቀት ያመጣበትን ምክንያት ሲነግረን የሰዎች እጆች በሰሩት ሀጢያት ነው ይለናል ። በዚህ መከራ የተፈለገው ደግሞ የእነርሱ ከወንጀል መመለስ ነው ። ተመልከቱ የአላህ እዝነቱ ባሮቹ ባሉበት ወንጀል ትቷቸው የእሳት ቅጣት እንዳያገኛቸው በዱንያ ላይ መከራ አቅምሷቸው ተመልሰው የሱ ትክክለኛ ባሮች እንዲሆኑና ዘላለማዊው የተድላ ሀገር እንዲወርሱ ነው ። ሱብሃናላህ !!!!!!
ለዚህ ነው አላህ የኑህ ሕዝቦችን በመልእክተኛቸው አማካኝነት በሱ ላይ ከማጋራት ወጥተው ወደርሱ እንዲሸሹ ያዘዛቸው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል : –
" فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ "
الذاريات ( 50 )
« ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ" ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው) ፡፡
" وَلَا تَجْعَلُوا مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ ۖ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِين ٌ"
الذاريات ( 51 )
" ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና ፡፡"
ከዓባስና ዐልይ – ረዲየላሁ ዐንሁማ – በተያዘ አሰር እንዲህ የሚል መጥቷል : –
" ما نزل بلاء إلا بذنب ولا رفع إلا بتوبة "
በላእ አልተከሰትም በሀጢያት ቢሆን እንጂ አልተነሳምም በተውበት ( በፀፀት )
እንጂ
ስለዚህ የዚህ በላእ መፍትሄ ወደ አላህ መሸሽ ፀፀት አድረጎ መመለስ ወደርሱ ማልቀስ ነው ።
የበላእ ምክንያቱ ሀጢያት ነው ሲባል የግድ ሁሉም ሀጢያተኛ ነው ማለት አይደለም ። በህዝቦች መካከል ወንጀል ሲንሰራፋ ፣ ግፍ ሲበዛ ፣ በደል ሲስፋፋ ተዉ የሚል ከሌለ የሚመጣው በላእ ሁሉንም ይነካል ። ይህንንም አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَاب ِ"
الأنفال ( 25 )
" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ ፡፡"
በመሆኑም አሁንም ወደ አላህ የመመለሻው ጊዜ አለ በስደት ላይ ሆነን ወንጀል መስራት ሳይሆን ተውበት አድርገን መመለስና አላህን መገዛት አለብን ። የመጣውን በላእ አንሱልን ብሎ ለቆሌ ፣ ለአድባር ፣ ለሙታን ፣ መለመንም ሆነ መማፀን በላኡ አንዲብስ የሚያደርግ ተግባር ስለሆነ መራቅ ይኖርብናል ። ሌሎቻችን ደግሞ ወገኖቻችንን በቁሳዊ ነገር መርዳት የማንችል በዱዓእ ስስታም አንሁን ። አላህ ሀገራችንን ሰላም እንዲያደርግልን ህዝቦቿንም ከመከራ እንዲያወጣልን ልንለምነውና ሁሌም ልንማፀነው ይገባል ።
https://t.me/bahruteka


Bahiru Teka dan repost
👉 የመርከዙ ሰዎች የተምዪዕ ማረጋገጫ
ክፍል አራት
የማግራራት አካሄድ ( منهج التساهل )
የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ከነበሩበት ዐቂዳ ለመንሸራተታቸውና የሰለፍያ ዳዕዋ ባለበት ማስኬድ ሙተሸዲድነት ነው ብለው ወደ ማግራራት አካሄድ ለመሄዳቸው የተወሰኑ ነጥቦችን እናያለን ። እንደ ሚታወቀው የተውሒድ ዳዕዋ ሲጀመር ከዳር እስከ ዳር ወጣቱ ወደ ተውሒድ አስተምሮ እየተመመ ሰላሰቱል ኡሱል ፣ ኪታቡ ተውሒድ ፣ አል ኢረሻድና የመሳሰሉ ኪታቦች በየገጠሩ ጭምር እየተቀሩ ሽርክ ወደ መቃብር ሊወርድ ሲቃረብ ኢኽዋኖች እንባ ጠባቂ ሆነው ነው ያተረፉት ። ኪታቡ ተውሒድ ውስጥ ከተካተቱ ባቦች አንዱ :–
ባቡ ማ ጃአ ፊል ሙሰዊሪን ( ምስል ቀራጮችን አስመልክቶ የመጡ ዛቻዎች ) የሚለው ይገኝበታል ።
ይህ ባብ ሁሉም ዳዒ ወይም ኡስታዝ አይኑ ቀልቶ ጡንቻው ተገታትሮ ፎቶ ሐራም ነው ። የኑሕ ህዝቦች ሽርክ ውስጥ የገቡት በምስል አማካይነት ነው እያለ ወጣቱ ዓእምሮ ውስጥ የፎቶ ሐራምነት በማስረፅ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ ያውም እየቀፈፈው ፎቶ እንዲነሳ አድርገው ነበር ። ከእነዚህ ኡስታዞች አብዛኞቹ የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ኡስታዞች ነበሩ ።
ቴሌቪዥን ሐራም ነው አላህን ፍሩ ቤታችሁ እንዳታስገቡ ።
ቪዲዮ ሐራም ነው ። እየተባለ ነበር ዳዕዋ ሲደረግ የነበረው ። እንኳን ዳዒዎች ሊቀረፁ ኢኽዋኖች በቴሌቪዥን ቻናል ሲመጡ ረድ ይደረግ ነበር ። ያኔ !!!!
🔹 ከተወሰኑ አመታት ጀምሮ የመርከዙ ሰዎች ፋሽኑ ያለፈበትና ኢኽዋኖች የሰለቹትን የማግራራት አካሄድ በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቤያ በመክፈት በሱና ላይ ሆነው ቤታቸው ከቴሌቪዥን እርቆ አላህን በመፍራት ላይ የነበሩትን እነእገሌ በቴሌቪዥን ሊቀርቡ ነው ። በማለት የሱና ቤቶች በዲሽና በቴሌቪዥን እንዲጨናነቁ አደረጉ !!!!! ።
🔹 በዚህ አላበቃም የማግራራት አካሄዱ ወደ አሶሳ የነበረውን የዳዕዋ ጉዞ ከኤርፖርት ጀምሮ በክላክስና በፉጨት ታጅቦ እየተቀረፁ ከተማ አቋርጠው ሲሄዱ ቀርፀው ለህዝብ አስተዋወቁ ። በዚህም ኢኽዋንን አስናቁ ።
🔹 ቀጠለ በዚህ አላበቃም በየክፍለ ሀገሩ ወንድና ሴት መሀል ሆነው ዳዕዋ ሲያደርጉ እየተቀረፁ በሚዲያ ላይ ለቀቁ !!!! በዚህም ወደ ኢኽዋን የቀረቡ መሆናቸውን አስመሰከሩ ።
🔹 ጉዱ በዚህ አላበቃም ኢኽዋንን ኮቴ በኮቴ እየተከተሉ የማስናቁን ስራ ቀጥለውበት ረመዳን ላይ የጎዳና ኢፍጣር ብለው አምስት ገዳናዎችን በመዝጋት ሰዎችን መተላለፊያ በማሳጣት ሸሪዓውን በጣሰ ኢኽዋንን ባስናቀ መልኩ ወንድና ሴት በተቀላቀለበት ድሀው ከሀብታሙ በማይታወቅበት የፖለቲካ ፉክክር አሸናፊ መሆናቸውን ቀርፀው ለህዝቡ ዒባዳ ነው ብለው አስተዋወቁ ።
በዚህ መልኩ ከነበሩበት ጠንካራ የሰለፍያ አቋም ወጥተው በስሙ በመነገድ በየጊዜው ከሰለፍያ አካሄድ እየራቁ ወደ ኢኽዋን እየተጠጉ አልፈው ሊሄዱ ጫፍ ላይ ደርሰው ነው ያሉት ። አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል ወሳኙና ከሰለፍያ በፍቃደኝነት የወጡበትን ዋናውን መሰረታዊ ነጥብ ይዤ እመለሳለሁ ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚቀበሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka


👉 የመርከዙ ሰዎች የተምዪዕ ማረጋገጫ
ክፍል አራት
የማግራራት አካሄድ ( منهج التساهل )
የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ከነበሩበት ዐቂዳ ለመንሸራተታቸውና የሰለፍያ ዳዕዋ ባለበት ማስኬድ ሙተሸዲድነት ነው ብለው ወደ ማግራራት አካሄድ ለመሄዳቸው የተወሰኑ ነጥቦችን እናያለን ። እንደ ሚታወቀው የተውሒድ ዳዕዋ ሲጀመር ከዳር እስከ ዳር ወጣቱ ወደ ተውሒድ አስተምሮ እየተመመ ሰላሰቱል ኡሱል ፣ ኪታቡ ተውሒድ ፣ አል ኢረሻድና የመሳሰሉ ኪታቦች በየገጠሩ ጭምር እየተቀሩ ሽርክ ወደ መቃብር ሊወርድ ሲቃረብ ኢኽዋኖች እንባ ጠባቂ ሆነው ነው ያተረፉት ። ኪታቡ ተውሒድ ውስጥ ከተካተቱ ባቦች አንዱ :–
ባቡ ማ ጃአ ፊል ሙሰዊሪን ( ምስል ቀራጮችን አስመልክቶ የመጡ ዛቻዎች ) የሚለው ይገኝበታል ።
ይህ ባብ ሁሉም ዳዒ ወይም ኡስታዝ አይኑ ቀልቶ ጡንቻው ተገታትሮ ፎቶ ሐራም ነው ። የኑሕ ህዝቦች ሽርክ ውስጥ የገቡት በምስል አማካይነት ነው እያለ ወጣቱ ዓእምሮ ውስጥ የፎቶ ሐራምነት በማስረፅ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ ያውም እየቀፈፈው ፎቶ እንዲነሳ አድርገው ነበር ። ከእነዚህ ኡስታዞች አብዛኞቹ የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ኡስታዞች ነበሩ ።
ቴሌቪዥን ሐራም ነው አላህን ፍሩ ቤታችሁ እንዳታስገቡ ።
ቪዲዮ ሐራም ነው ። እየተባለ ነበር ዳዕዋ ሲደረግ የነበረው ። እንኳን ዳዒዎች ሊቀረፁ ኢኽዋኖች በቴሌቪዥን ቻናል ሲመጡ ረድ ይደረግ ነበር ። ያኔ !!!!
🔹 ከተወሰኑ አመታት ጀምሮ የመርከዙ ሰዎች ፋሽኑ ያለፈበትና ኢኽዋኖች የሰለቹትን የማግራራት አካሄድ በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቤያ በመክፈት በሱና ላይ ሆነው ቤታቸው ከቴሌቪዥን እርቆ አላህን በመፍራት ላይ የነበሩትን እነእገሌ በቴሌቪዥን ሊቀርቡ ነው ። በማለት የሱና ቤቶች በዲሽና በቴሌቪዥን እንዲጨናነቁ አደረጉ !!!!! ።
🔹 በዚህ አላበቃም የማግራራት አካሄዱ ወደ አሶሳ የነበረውን የዳዕዋ ጉዞ ከኤርፖርት ጀምሮ በክላክስና በፉጨት ታጅቦ እየተቀረፁ ከተማ አቋርጠው ሲሄዱ ቀርፀው ለህዝብ አስተዋወቁ ። በዚህም ኢኽዋንን አስናቁ ።
🔹 ቀጠለ በዚህ አላበቃም በየክፍለ ሀገሩ ወንድና ሴት መሀል ሆነው ዳዕዋ ሲያደርጉ እየተቀረፁ በሚዲያ ላይ ለቀቁ !!!! በዚህም ወደ ኢኽዋን የቀረቡ መሆናቸውን አስመሰከሩ ።
🔹 ጉዱ በዚህ አላበቃም ኢኽዋንን ኮቴ በኮቴ እየተከተሉ የማስናቁን ስራ ቀጥለውበት ረመዳን ላይ የጎዳና ኢፍጣር ብለው አምስት ገዳናዎችን በመዝጋት ሰዎችን መተላለፊያ በማሳጣት ሸሪዓውን በጣሰ ኢኽዋንን ባስናቀ መልኩ ወንድና ሴት በተቀላቀለበት ድሀው ከሀብታሙ በማይታወቅበት የፖለቲካ ፉክክር አሸናፊ መሆናቸውን ቀርፀው ለህዝቡ ዒባዳ ነው ብለው አስተዋወቁ ።
በዚህ መልኩ ከነበሩበት ጠንካራ የሰለፍያ አቋም ወጥተው በስሙ በመነገድ በየጊዜው ከሰለፍያ አካሄድ እየራቁ ወደ ኢኽዋን እየተጠጉ አልፈው ሊሄዱ ጫፍ ላይ ደርሰው ነው ያሉት ። አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል ወሳኙና ከሰለፍያ በፍቃደኝነት የወጡበትን ዋናውን መሰረታዊ ነጥብ ይዤ እመለሳለሁ ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚቀበሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka


محاضرة جديدة

بعنوان: "تعرف البدعة وأنواعه وأحكامه"

لفضيلة الشيخ يوسف أحمد حفظه الله

بالمسجد البخاري بمدينة بحر دار

تاريخ ربيع الأول ١١\١٤٤٣ه‍
አዲስ ሙሓዶራ

ርዕስ – "የቢድዓ ምንነት፣ አይነቶቹና ሸሪዓዊ ብይኑ"

በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ

ጥቅምት 07 ‐ 2014

በመስጅደል ቡኻሪ (ባህር ዳር)

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


🔷 የሰዎችን መከራ መነገጃ ማድረግ
እንደሚታወቀው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ስቃይ ቃላት ሊገልፁት የማይችሉት በተለይ ለሱና ቤተሰቦች ከህይወት ሞትን እስከመምረጥ የሚያደርስ ፈተናና ሰቆቃ ሆኖባቸዋል ። ባለቤትህን ይዘህ እስከማስደፈር ሴት ልጅህን ተገናኝ እስከ ማለት የደረሰ ፈተና !!!!, ታዲያ እንዲህ አይነቱን ግፍና መከራ ሸሽተው ሁሉን ጥለው ህፃናትን ተሸክመው ሴቶችን አስከትለው እግራቸው ወደ መራቸው የሚሰደዱ ብዙዎች ናቸው ። እነዚህ ሰላም ወደ ሆነ አካባቢ ከደረሱ በደረሱበት ያሉ ወገኖች በአቅማቸው እንባቸውን ጠርገው ከእለት ጉርሳቸው አካፍለው ወገን መሆናቸውን ያሳዩዋቸዋል ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሰው ፊት ቆመው የውስጣቸውን የሚናገሩበት አቅም አይኖራቸውም ። በጣም የሚያሳዝነው አንዳንድ አፈ ጮሌዎች በአቋራጭ ለመክበር እዚህ መሀል ከተማ ላይ የቤተሰቦቻቸውንና የራሳቸውን ህይወት ለማዳን ሸሽተው የመጡ በማስመሰል የህብረተሰቡ ልብ የተነካና ምንም ወደ ኋላ እንደማይል ስላዩ በወገኖች ስቃይ የሚነግዱ እየታዩ ነው ። ይህ እኛን ከገጠመን ክስተት በመነሳት ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ ነውና አንድ ሰው ተነስቶ በጣም በሚያሳዝንና በሚያስለቅስ መልኩ እንዲህ አይነት ታሪክ ሊያቀርብልን ይችላል ። ይዘን አረጋግጠን እውነት ከሆነ መለመን የለበትም ከጎኑ ልንሆን ጀማዓ ሆነን ቤት ተከራይተን ቀለብ አስገብተን ስራ እንዲሰራ ማድረግ ካልሆነ ለሚመለከተው አካል ይዘን ማሳወቅ ይኖርብናል ። በእንደዚህ አይነት የሰዎች ስቃይ መነገድ ምንኛ ያማል !!!! ።
በመከራ በስቃይ በእረሀብ ላይ ላሉ ወገኖቻችን ትክክለኛ በሆኑ ተቋማት ወይም ማህበራት አማካይነት የምንችለውን ከማድረግ ወደ ኋላ ማለት የለብንም ። አላህ በወንጀላችን ምክንያት የመጣብንን በላእ አንስቶ ወገኖቻችንን ወደ ቄያቸው መልሶ የሰላም አየር የሚተነፍሱ ያድርግልን ።
https://t.me/bahruteka




አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂወበረካቱ
ዛሬ ኡስታዝ ሀጃ ስለገጠመው ደርስ አይኖርም
ሚድያ ለማይጠቀሙ ቀጥታ በመደወል እንዳይለፉ እንንገራቸው


የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ኢብራሒም አሊ ሸይኽ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
ጥያቄ፡- የነብዩ ሙሐመድ ﷺ መውሊድን በተመለከተ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው? ሶሃቦች ፣ ታብዕዮች እና ሌሎችም ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ሰርተውታልን?
መልስ፡- የነብዩን ﷺ መውሊድ ማክበር በዲን ላይ የተፈጸመ አዲስ ፈሊጥ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በኢስላማዊው ዓለም ማህይምነት ከተሰራጨ በኋላ ለጥመት ፣ ለብዥታ እና ለውዥንብር ጥርጊያ መንገዶች ተከፍተዋል፡፡ አይኖች ታወሩ ፣ ጭፍን ተከታይነት ጉልበት አግኝቶ ተንሰራፋ፡፡ አብዛኛው ሰው እከሌ ወደተናገረው ወይም እከሌ ወደወደደው .. እንጅ ሸሪዓዊ ወደሆኑ ማስረጃዎች ለመመለስ ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ ጸያፍ ስለሆነው የመውሊድ በዓል ከረሡል ﷺ ባልደረቦች ፣ ከታብዕዮች እንዲሁም ከታብዕዩ ታብዕይ ዘንድ አንድም የተገኘ ማስረጃ የለም፡፡
ረሡል ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي تمسكوا بها وعضوا عليها بالنوجذ ، وإياكم ومحدثات الأمور فإن كل محدثة بدعة ، وكل بدعة ضلالة"
“የእኔን ሱና ከእኔ በኋላ የቅን መሪዎችና ምክትሎቸን ሱና አደራ አጥብቃችሁ ያዙ! በመንጋጋ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! ከነገሮች አዳዲስ ፈሊጦችን አስጠነቅቃችኋለሁ! ማንኛውም አዲስ ፈሊጥ ቢድዓ ነው ፤ ማንኛውም ቢድዓ ደግሞ ጥመት ነው፡፡” (አህመድ: 17144, አቡዳውድ: 4607, ኢብኑ ማጀህ: 42)
አሁንም በተጨማሪ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد"
“በዚህ (በዲናችን) ከእርሱ የሌለን አዲስ ፈሊጥ ያመጣ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” (ቡኻሪ: 2697, ሙስሊም: 1718)
መውሊድን የሚያከብር አካል ረሡልን ﷺ ለማላቅ እና ህያው ለማድረግ አላማ አድርጎ ከሆነ ፣ ጸያፍና መጥፎ ነገሮች ከተዋሃዱበት የመውሊድ በአል ውጭ ረሡልን የሚያከብርበት ፣ የሚያልቅበት መንገድ መኖሩ የሚያጠራጥ አይደለም፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴿وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ﴾
“መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል፡፡” (አሽ`ሸርህ፡ 4)
የረሡል ﷺ መወሳት በአዛን ፣ በኢቃማ ፣ በኹጥባ ፣ በሶላቶች ፣ በተሸሁዶች ፣ በሶለዋቶች ወይም በዱዓዎች ላይ ሁሌም የሚገኝ ጉዳይ በመሆኑ አዳዲስ ፈሊጦችን መጨመሩ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ረሱል ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"البخيل من ذكرت عنده فلم يصل علي"
“ንፉግ ማለት እኔ ከእርሱ ዘንድ ተወስቸ በእኔ ላይ ሶለዋት የማያወርድ ነው፡፡” (አህመድ: 1736)
እርሳቸውን በመታዘዝ ፣ የተናገሩትን እውነት በማለት ፣ የከለከሉትን በመከልከል እርሳቸው በደነገጉት ህግ እንጅ አላህን ባለመገዛት እርሳቸውን ማላቅ ይገኛል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ረሱልን በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ከማውሳትም የላቀ ተግባር ነው፡፡
ይህ ክብረ በዓል መልካም ቢሆን ኖሮ ደጋግ የሆኑ ቀደምቶች ወይም ሰለፎች በዚህ ነገር ከእኛ የበለጠ ተሳታፊዎች ይሆኑ ነበሩ፡፡ ሰለፎቹ ለረሱል ያላቸው ውዴታ እና ክብር በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ ለመልካም ነገሮች ያላቸው ጉጉትም የላቀ ነው፡፡
የመውሊድ ባለቤቶች ጉዳይ አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች ከሚያወሱት የዘለለ አይደለም፡፡ እርሱም ሰዎች የድክመት ፣ የውርደት ባህሪዎች ሲገጥማቸው መሪዎቻቸው ሲፈጽሙት ከነበረው ትክክለኛ ተግባር በማፈንገጥ ደካማ የሆነች ነፍስ በቀላሉ ልትፈጽመው የምትችለውን እና ልፋት የማይጠይቅ በሆነው አመታዊ የማስታወሻ በአል አከባበር ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
እውነተኛው አክብሮት ማለት የሚያከብረውን አካል መታዘዝ ፣ ለእርሱ ታማኝ መሆን ፣ መልእክተኛም ከሆነ ዲኑ ልቅና የሚያገኝበትን ፣ እርሱ ያዘዘውን መተግበር ፤ ንጉስም ከሆነ ንግስናው የሚስተካከልበትን ተግባር ብቻ መፈጸም ይገባዋል፡፡ ወደኋላ ከመጡ አካላት ይልቅ ቀደምት ሰለፎች ለረሡልም ﷺ ይሁን ለሶሃቦች ያላቸው ክብር ከፍተኛ ነበር፡፡ በእንዲህ አይነት መሰል የቢድዓ ተግባር ገንዘብህን ፣ ነፍስህን መስዋእት ከማድረግም ይከለክሉ ነበር፡፡ ሰለፎች ለረሡል ﷺ የሚሰጡት ክብር በመመራትም ይሁን በመከተል የሰለፎች ጎዳና የጠፋበት ዘመን ላይ ለመሪዎቻቸው ባዶ የሆነ ልቅና ከሚሰጡ የጥመት ጎዳና ተከታዮች የተለየ ነበር፡፡
ረሡል ﷺ በማንኛውም ልቅናና ክብር ከሰዎች ሁሉ ተገቢ መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለማላቅ ብለን በዲን ላይ መጨመር ፣ መቀነስ እና መቀያየር ደግሞ ተገቢ አይደለም፡፡ የአላህን ሀቅ አሳልፈን ለረሡል ﷺ መስጠት ይህ እርሳቸውን ማላቅ ሳይሆን የእርሳቸውን ክብር መቀነስ ነው፡፡ መልካም አስተሳሰብ መኖር በዲን ላይ የሚደረግን ቢድዓ የተፈቀደ አያደርግም፡፡ አብዛኛው ከዚህ ቀደም የነበሩ ሀይማኖት ተከታዮች በዲን ላይ የሚያደርጉት ፈጠራ ከመልካም አስተሳሰብ የተነሳ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን መልካም አስተሳሰብን መሰረት በማድረግ በዲናቸው ላይ አዳዲስ ነገሮችን ከመፍጠር አልተወገዱም፡፡ በዚህ ምክንያት እምነታቸው መልእክተኞች ከመጡበት ውጭ ሆኗል፡፡ ቀደምት ወይም ሰለፎቻችን ልክ ኸለፎች (ወደኋላ የመጡት) በዲን ጉዳይ እንደተዘናጉት ቢዘናጉ ኖሮ የዲን መሰረቱ ሙሉ በሙሉ ይጠፋ ነበር፡፡
ነገር ግን ቀደምቶቹ ለእኛ ዲኑን ጠብቀው አስረክበዋል፡፡ ስለዚህ ወደዲናችን መመለስ ፣ ዲናችንን በመንጋጋ ጥርሳችን ነክሰን መያዝ በእኛ ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

285

obunachilar
Kanal statistikasi