...ከእለታት አንድ ቀን አሚር አውዘል ቀርነይኒ ቀንድ አበቀለ።በጥምጣሙ ደበቀው።አንድ ቀን ግን ፀጉር ቆራጩ ቀንዱን አየበት።
"ስለዚህ ነገር ከእኔና ከአንተ በቀር የሚያውቅ የለም ትናገርና ወዮልህ!"
"ኧረ እኔ አልናገርም" ይላል ሰውየው ግን መናገር አስፈለገው።ለሰው እንዳይናገር መጥፊያው ይሆናል፤ግን ወሬው ሆዱን ነፋው።አልቻለም።በመጨረሻም ከከተማ ወጥቶ ርቆ ሄዶ መሬት ቆፍሮ ለመሬት ነገራት "አውዘል ቀርነይኒ ቀንድ አብቅሏል!" ይህን ተንፍሶ ወደ ጉዳዩ ሄደ።እዚያች ስፍራ ዋንዛ ዛፍ በቀለ።ጊዜው ሲደርስ ተቆረጠና ከበሮ ሆነ።ሰዎች ከበሮውን ሲመቱት"አውዘል ቀርነይኒ ቀንድ አብቅሏል!" ይላል።
ወይ አውዘል ቀርነይኒ!
(ከሰብሀት ገብረእግዚአብሔር እግረመንገድ ገፅ 98
አርትኦት ደምሴ ፅጌ )
@mekereze