ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከዕቅድ በላይ ገቢ ሰበሰበ
*************************************
(ታህሳስ 10/2017ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ካፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በህዳር ወር አፈፃፀሙ እንደተመላከተው በወሩ ሊሰበስብ ካቀደው የገቢ ዕቅድ 107% መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የህዳር ወር እና የአምስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ባደረገበት ወቅት ነው፡፡
የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ቶሉ ፊጤ እንደገለፁት በየጊዜው የሚሰበሰበው የገቢ ዕቅድ ከፍ እያለ መምጣቱን አና ይህ ማለት ደግሞ መንግስት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ላያ ያለው እምነት ከፍተኛ መሆኑን እና ሀገራዊ ወጪ በሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ትልቁ ድርሻ የኛ ነው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በአፈፃፀሙ እንደተመላከተው በህዳር ወር ቀጥተኛ ከሆኑ ታክሶች፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ እቅድ 1,731,682,915.42 ብር፣ ክንዉን 1,858,297,181.38ብር፣ አፈፃፀሙም 107.31% ሲሆን ከእቅድ በላይ 126,614,265.96 ብር መሰብሰብ የቻለ መሆኑን እና አጠቃላይ የአምስት ወራት አፈፃፀሙም 12,113,830,710.12ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 11,650,891,671.40 ብር መሰብሰብ የቻለ እና ይህም በመቶኛ ሲገለጽ 96.18% ይሆናል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀሙ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ቡድን አስተባባሪ ኮማንደር ሞላ ተሾመ ቀርቧል፡፡
በአፈፃፀሙ ዙሪያ የስራ ሂደቶች እና ቡድኖች አስተያየት እና ምላሾችን ሰፋ ባለ መንግድ የሰጡ ሲሆን የዘርፍ ም/ክ ስራአስኪያጆችም የየዘርፎቻቸውን የስራ አፈፃፀም ላይ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ በጋራ ስራዎችን መስራት እና ገቢውን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
አቶ ቶሉ በማጠቃለያቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀምጠው ሲሆን ወሩ የበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት በመሆኑ ስራዎች ከበፊቱ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው እና ግብር ከፋዩን በማክበር፣ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት የታህሳስ ወር የስራ አፈፃፀምን የተሻለ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ግብር÷ ለሀገር ክብር!ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦
https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡-
https://web.facebook.com/info.mto2/ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡-
https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2