Ålem poêⓂs🎀🌎(ስነ-ግጥም)


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Poems//ግጥም🎀❤

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




የጀንበር ነገር!✨☺️

አያረጋም ወይ
አይመስጥም ወይ የፀሐይ ሰንበር፥
...
በዋይታ ጩኸት በሰከረ አገር፥
በልብ አርምሞ እንደመናገር!
...
በሌሊት ጭለም በመሸ መንደር፥
በገና አንስቶ እንደመደርደር!!

//የአመሻሽ ወጎች//🙌🏿

[ ዓለም ]


መንምኖ ቀልጦ የእጅ መክሊት፣
የማይከረፍፍ ሁሌ ቀን ተ ሊት፣
ይህ ልቡናችን ምን አደንድኖት፥
እምባ ትዝብቱን ከምኔ ረስቶት፥
ብቻውን ቆመ ቀንበሩን ሰብሮት?!

ሰው ባንደበቱ ፥ ሽሙጥ ሲወግረን፣
በምሽት አደን፥ በቀን ሰቀቀን፣
በጊዜ ትንግርት ፥ በመኖር አልቀን፤
ወላፈን ችንካር ፥ ሳይነቀንቀን፣
የሕይወት ጀንበር ፥ እስክታመልጠን፣
ከሃኬት ሞት ጋር ፥ እኩል ተሯሩጠን፤

ላዘን ርክብክብ ፥ ባይኖርም ወገን፣
ልክ እንደ ደና ፥ ጸንቶ መጀገን፤

ለሲቃ ለቅሶው ፥ ስናመሰግን፧
            እንዴት ቻልነው ግን?!😊


ለጽኑአኑ🙌🏿

[ዓለም]


ላለመጠየቅ!

በሳቅ መሸዋወድ
የጊዜው አንድምታ፥
ለመሸሽ ለማምለጥ
ከጥያቄ እሩምታ፤
ከእሮሮው ጥላ ስር
የሚገለፍጠው፣
ላለመጠየቅ ነው
ሁሉም የሚስቀው!

[ዓለም]


፨፨፨   ፨፨፨   ፨፨፨   ፨፨፨   ፨፨፨   ፨፨፨

ገበና ተባብለን ቤት ያወጋነውን
እውጭ እንዳይወጣ፣
ተማምለን ተማምነን ...
ከኛ ካልሆኑት ግን እንደምን ቃል መጣ።

በልብ ተሳስረን በንባ ላንቃጣ፣
እንዴት ሳንካካድ የጓዳ ጉዳችን ጎዳና ተሰጣ!
ታማኝ የተባለው ከሆነ እንደ ስሙ፣
ታዲያ እነ'ገሌ በየት በኩል ሰሙ?!

በየት በኩል ሰሙ?!

[ዓለም]


... ... ... ...!


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨  ፨፨፨፨፨፨፨
እንዳበባ~ቅጠል
እንደ ክረምት~ጠል
እንዳለቀ~ከሰል
እንደ ጢሰ~ሰንደል

     ክፍተት እያበጁ
     በተስፋ እያጃጁ

            የካብናቸው ሁሉ
            ቀስ ቀስ እያሉ

       በዝምታ በደል
       ተነጠሉን አይደል?!:፧:

[ዓለም]


እኔ ምላችሁ ልባችሁ ጥልጥል ብሎ ያውቃል? መቼም ህይወትን በፅሁፍ ማየት እንደመትፈልጉ ጥርጥር የለኝም!

ይህ Channel:- ልዩ ድርሰት(ልብ ሰቃይ)
                     አዝናኝ ወግ
                   የህይወት ምክር
                     ግጥም....



Join


https://t.me/haniyen1621


አልክድም መሆኔን ድኩም
ስሉል ነኝ አልጠነከርኩም
ከንብርክክ ተማፅኖዬ ጋር
ከደጅህ አልተነጠልኩም።
°
ተመልከት ከድቶ ሲተፋኝ
ያያዝኩት ምርኩዝ ሲጠፋኝ
ዘመመ ቅፅሬ ተናደ
በወረት ክንዴ ታጨደ።

°
እንግዲህስ ቀኜ ካራቀኝ
የዋጥኩት መድህን ካነቀኝ
ለብሼ ልብሴ ካረዘኝ
በቁሜ ሰው ከገነዘኝ
ይቅርብኝ መሸነጋገል
አንተው ነህ የምታጸድቀኝ።
°
አላዝን አልንገዳገድ
ከንግዲህ ማንስ ቢረታኝ፣
ምን ቀረኝ ብዬ ዝላለሁ
ሃይልህ ነው የሚያበረታኝ።
°
[ዓለም]


ይብቃን እኔም በቃኝ
በአርምሞ ዘመን እንቃኝ!

ሳይረፍድ እናንቀላፋ
ከቆየን ደግሞ እንዳንከፋ
ከሁከት ፈጥነን እንጥፋ!

የሕይወት ጽዋ ሳታልፈን
መከራ ቁር ሳይሰይፈን
ከጊዜ ዘመን ውጭ ሁነን
እንውጣ አንዳች ሳይገደን


ምጽአት እስከሚያነቃን
ዓለሙ ደርቶ ሳይደቃን

ቁስልና ደም ሳያደቀን
ከ አንብዕ ከሳቅ ተላቅቀን

ሳይሰማ ማንም ሳያውቀን
ምንም ምን እንዳይጠይቀን
እንፍለስ ዓለምን ለቀን

ይብቃን እኔም በቃኝ
በአርምሞ ዘመን እንቃኝ!🙂🙃

ምጽዓት እስከሚያነቃን!


[ዓለም]


አወኩብሽ፥በጥርሶችሽ ስትዋሺ
ያላየሁኝ መስሎሽ፥ሁሌ ስታለቅሺ
የሞላሽልኝ ሳቅ፥በእምባሽ ጠብታ
አየሽ ወይ እማማ፥ጭንቀቴን ሲፈታ?!

አላምንሽ በጉዝጓዝ፥ቤቱን ብታሞቂ
እንስፍስፍ ነው ልብሽ፥አርፎ መቼ ታውቂ?

ምን ይገኛል ዘዬ፥ላንቺስ የሚሞላ
እጅሽ እኔን ዋጀ፥ለራሱ እየላላ
ያስፈራኛል ቀልብሽ፥ያሳሳኛል ልብሽ፣
ሁሉንም ተይና
እስቲ ፈገግ በይ፥ዛሬኮ ነው ቀንሽ ፧፧!🥀

መልካም ያንች ቀን🙌

[ዓለም]


ነፍሴ ግን ይህን ወደደች!

ፎካሪም ሲፎክር ዋለ
ተቀኚም ሞቅ ሞቅ አለ
ተራቢም ሲተርብ ቆየ
በመንደር ሲዋልል ታየ
ጥርሶቹን እያገጠጠ
ጨፋሪም ጮቤ ረገጠ
ልቡናው እየቀለጠ
ሀብታምም ልብሱን ለወጠ።

በነኑ በሩጫ መንገድ
            ተያይዘው በውሸት ኪዳን፣
ለማይቆም መራመድ ማለት
            ፈውስ ነው ልክ እንደመዳን።

"ስህተት ነው የለም ሁነኛ"
አልልም ልክ እንደ ዳኛ

ሰው እንዶን በህይወት ሳለ
           የልቡን ለማን ይተዋል፣
መሻቱን መጻኢ ነፍጎት
           እንደምን ይከለክላል!

ፎካሪም ሲፎክር ዋለ
አዝማሪም ጠጅ አማለለ
ቀማሚም ግኝቱን ኳለ
ተራማጅ ተንቀለቀ።
አማኙ በንባ ማለለ
ይሁዳም በ'ግዜር ስም ማለ!

ልቤ ግን አውቆ ዝም አለ።

የሆነን ይሁን በማለት
                ሁሉንም ስለሰደደች፣
መተውን ለምዳለችና
                ነፍሴ ግን ይህን ወደደች!

state of calm🧘🏾‍♀

[ዓለም]


በፍጡር ሕሊና አክለህ ተችለህ፣
እንዴት ቀለልክ ወደህ ፈቅደህ?!


ሰውን ፈጥረህ ሳትወያይ ሳትማከር፣
አንተው ካንተ ስትናገር።

ያለማነስ ያለመቅለል፣
አምላክ ሁነህ ሰው ስታክል፣
ነፃ ፈቃድ ሳትከለክል፣
ረቂቅ ሁነህ ሰፊ ክልል፤!

ከሰማይ ምድር ገዝፈ ሳለኽ፣
የፍጡር ልብ እንዴት ቻለኽ ?!


የ'ሮብ ለቱ ማስታወሻ!(የተማከሩብህ)🙌🏿

[ዓለም]


ስደክም ሃይለኛ ነኝ!😈


በድካሜ ወራት ሰበብ አስባብ አርገህ፣
አንተ ክፉ ጠላት ...
ልትፈታተነኝ ከሆነ ከጅለህ፣

ተመለስ አፈግፍግ ደምኽን አቀዝቅዘህ፣
ወደ ኋላ መትር ጦር  መድፍህን ጥለህ፤

ስደክም ሃይለኛ ነኝ መቼም ታውቀኛለህ!!


ድካምም ሃይል የሚሆንበት ጊዜ አለ!

[ዓለም]


ማነው የከዳሽ?

የአገር ኩራት ተስፈኛዋ እንስት
እጅሽ ታቃቢ አይንሽ የማይስት
ልብሽ ደርባባው ስለማይሰስት
ባንቺ ስም መማል አይደለም ግዝት፤

ምነዋ ዛሬ ጠቁሯል መብራትሽ
ሰውም ዝር አይል አይመጣም ደጅሽ።

ብርቱ አልነበረ? ጣሪያ ግድግዳሽ?
ማን አፈረሰው ማነው የከዳሽ?!

ላልተጠየቁ🙌🏿

[ዓለም]


ችዬ እንዳይመስልህ!

ደክርቼ ሳለሁ ዐለት የመሰልኩ፣
በሃያላን ፊት ደክሜ ያልሰለልኩ፣
ወና ብሆንም ከሌለኝ ያጣው፣

እንደ ምንዱባን ደጅ የማልጠናው ፣
ችዬ እንዳይመስልህ አስችሎኝ ነው።😁

...አስችሎን አይደል?!🙂‍↕️
[ዓለም]


መቼቱን ባናውቅ ፡ ምን ባይታየን፣
አናምን እንጂ ፡ ካበድንስ ቆየን!

[ዓለም]✍🏿


..🥀..


ክንድ ያዝላል
ልብ ያሳሳል
ሆድ ያስብሳል
ዓለት ሲናድ እንዴት ያማል?!


ሃይለ ብርቱ ለንብ አውራ
ልበ ግዙፍ አይናገር አያወራ
የበራው ቀን እኪጨልም
ታክቶት ሲዝል ታይቶ አያውቅም።

ሺህ ሰበባት ሲከጅሉት
ዕድሜው ጊዜው ሲደልሉት፤
ችሎ አቻችሎ፣
ለራሱ ቃል ምሎ፣
ሲጥር ሲግር ውሎ፤

ጨካኞች ግን እየገፉት
ገደል አፋፍ አደረሱት፨

የሰራውን አፈረሱት
ሳያነባ አስለቀሱት፨

አስመረሩት፣
አስጨነቁት፣
ተስፋ ሳይቆርጥ አጨለሙት፨

ሰባበሩት፣
ከሰው መሃል አነጠሩት፨

አስጨከኑት፣
ከሕልሙ ፊት አተነኑት!፨

ከዚህ ወዲያም አላየሁት!🥀

ለከሸፉ ሕልሞች🙌🏿

[ዓለም]✍🏿


ማደር ቀላል አይደለም🙌🏿

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

556

obunachilar
Kanal statistikasi