"'በጣም ጨካኝ ነው አይወደኝም' ብላ ከእንባዋጋ መታገል ጀመረች 'ከኔ በላይ ሌላ ጉዳይ አለው እኔ አላስደስተውም' እንባዎቿ ኮለል አሉ 'ንገረኝ እስኪ ምን ላርግለት' አለች
'ምንም ያደረግሽው በቂ ነው' የኔ ምላሽ ነበረ ይሄን ባወራች በሳምንቱ እየተፍለቀለቀች መጥታ የሰርግ ካርድ ሰጠቺኝ"
"ልጄ ባሰበበት የዋለ የተመኘውን ሁሉ ያገኘ የለም አትከፋ"
"እማ እኔ ከሷ ውጪ ማፍቀር አልችልም"
"አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"
"ጠይቂኝ"
"እጅህን ቆረጥከው ይባል መልሶ አይድንም"
"ይድናል"
"እሺ ፀጉርህ ተቆረጠ ይባል መልሶ አያድግም"
"ያድጋል"
"አየሀ ሁሉም ነገር በጊዜው ይሆናል የቆሰለው እጅህ ባንድ ቀን እንደማይድነው ባንድ ቀን አትረሳትም ግን ጊዜ ሲሄድ የራስህን ህይወት ትጀምራለህ"
"አልችልም እወዳታለሁ ያለሷ አልኖርም"
"እስኪ መተንፈስ አቁም"
"ልገይኝ ነው እንዴ"
"የማትኖረው ያለ አየር ነው እንጂ ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል" ይሄ ቃል ነበረ ትላንቴን ያስረሳኝ ሰው እስካልሞተ ይኖራል እኔም ከህመሜ ያዳነቺኝ እናቴንም ሆነ ህመሜ የሆነችውን ፍቅሬን አጥቼ እየኖርኩ ነው መተንፈስ እስከማቆም