Bahiru Teka dan repost
🚫 እውነትም እንቁ – ጣጣሽ
እንቁ የሚለው ቃል እኔ የማውቀው የከበረ ማእድን መሆኑን ነው ። እኛ ሀገር ግን ዘመን መለወጫ ላይ የሚወጣን አበባ ለመግለፅ ይጠቀሙበታል ። በእነርሱ እይታ አበባዋና ጣጣዋ ምን እንደሆነ ባላውቅም በኔ እይታ ግን የዘመን መለወጫን ተክትላ የምትመጣው እንቁ ብዙ ጣጣ አላት ። በሌላ አባባል ዘመን መለወጫው ብዙ ጣጣ አለው ።
ከሁሉም በፊት ይህ ባአል ከክርስትና እምነት ጋራ የተገናኘ ስለሆነ ሙስሊሞችን አይመለከትም ። ሙስሊሞች በአመት ሁለት ዒድ ( ባአል አላቸው) እነርሱም ዒደል አድሓና ዒደል ፊጥር ናቸው ። የዘመን አቆጣጠራቸውም የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ሂጅራ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በሂጅሪያ ነው የሚቆጥሩት ። በዚህ አቆጣጠር መሰረት አመቱ አልቆ አዲሱ የሚጀምርበት ወር ሙሐረም ይባላል ። ይሁን እንጂ ይህን የዘመን መለወጫ ቀን እንደ ባአል አያከብሩትም ።
እንቁጣጣሽ የሚባለው ግን ከክርስትና እምነት ጋር የተገናኘ ባአል ነው ። ዘመኑንም ዘመነ ዮሐንስ, ማቲዮሰ, ሉቃስና ዻውሎስ ብለው ይሰይሙታል ።‼ ታዲያ ይህንን እንዴት ሙስሊሞች ያከብሩታል ? በጣም የሚገርመው የኢኽዋን መሪዎች አብሮነት በሚል ይህን ባአል የጋራ ለማድረግ ሲታትሩ መታየቱ ነው ። አልፎም በዚህና በጥምቀት ባአል ላይ በክብር እንግድነት ሲሳተፉና መግለጫ ሲሰጡም ሊታይ ይችላል ። ይህ የዲናቸውን ክብር ማስነካትና ራሳቸውንም ከማዋረድ ውጪ ጥቅም የለውም ።
የሀገረችን ሙስሊም በሱፍይ መሪዎች አማካይነት ታቦት ሲሸኝና ጥምቀት አብሮ እየጨፈረ ሲያከብር ይኖር ነበር ። ተራው የኢኽዋን ሆነና በተራቸው ጭራሽ እየሱስ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው ‼ ብለው አረፉት ። ይህም ለሙስሊሙ ወላእና በራእ የሚለው የዐቂዳ ውድቀት ሰበብ ሆነ ። የአላህ መልእክተኛ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ መሪዎችን ነው ያሉት ይህ ነው ።
ወደ ርእሴ ስመለስ እንቁ – ጣጣሽ እውነትም ብዙ ነው ጣጣሽ እላለሁ ። በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ዐቂዳ ሁሌም ኮተት አያጣውም ። ዘመን መለወጫ ሲመጣ ሰዎች ካለፈው አመት ድክመታቸውና ስህተታቸው ታርመው የበለጠ ለመስራት ከመዘጋጀት ይልቅ የህይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ መተትና ኮተት ያማትራሉ ። በመሆኑም ከምን ጊዜውም በላይ በዚህ የእንቁ–ጣጣሽ ባአል ላይ መተትና ድግምት ይሰራል ጠንቋዮች በጣም ቢዚ ይሆናሉ ። ይህ መተትና ድግምት የእነርሱ ህይወት ሊለውጥ የሌላው ህይወት ማጥፋት አለበት ብለው ነው የሚያስቡት ። በመሆኑም በአብዛኛው የሚሰሩ ድግምትና መተቶች በሰዎች ላይ ይሆናል ።
አላህ ከፈቀደው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ። መጠንቀቁና ሰበብ ማስገኘቱ መልካም ነው ። በዘመን መለወጫው ማለዳ ( ጠዋት) ላይ የተለያዩ ዶሮዎች በተለያየ መንገድ ተገለው በሰዎች መውጫና መግቢያ ላይ ወይም መንገድ ላይ ሊጣሉ ይችላሉ ። በሌላ መልኩ መሬት ተቆፍሮ ሊቀበሩም ይችላሉ ። ሙስሊሞች በተለይ በዚህ ቀን ጠዋትም ሆነ ቀኑ ላይ ከቤታቸው ሲወጡ " ቢስሚላህ ተወከልቱ ዓለላሂ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ብለው መውጣት ይኖርባቸዋል ። ለልጆቻቸው ይህን ዚክር ማስተማርና መንገድ ላይ የሚያገኙትን ነገር እንዳይረግጡ ፣ እንዳያነሱና እንዳይጫወቱበት መንገር ይኖርባቸዋል ።
ይህን ዚክር አድርገው ሰበብ ካስገኙ በአላህ ይጠበቃሉ ። በእንቁጣጣሽ ጣጣ እንዳይገቡ ይረዳቸዋል ።
በመጨረሻም ይህን ኮተት ተሸክሞ የሚመጣውን ዘመን መለወጫ የሁሉም ነው ከማለት መቆጠብና ይዞት ከሚመጣው ጣጣና ኮተት በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል ።
አላህ ሙስሊሞችን ከሸረኛች ተንኮል ይጠብቅልን ።
https://t.me/bahruteka