✍️የዓለማችን አጭሩ ዶክተር ✍️
👉ዓለም ላይ ምንም የማይቻል ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ይሉታል፡፡ በቁመቱ ማጠር ያጋጠሙት መድሎዎች ዶክተር ከመሆን ህልሙ አሰናክለው አላስቀሩትም፡፡ ፈተናዎችን በጽናት ማለፉ የብርቱ ሰብእና ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ የህይወት መርሁ በተስፋ መትጋት ነው፡፡
👉በማይድን ህመም የመጠቃቱ የሀኪሞች መርዶ ለወላጆቹ የደረሰው ገና የ4 ዓመት ህጻን እያለ ነበር፡፡በትምህርት ቤት ቆይታው በቁመቱ ማጠር እና በጭንቅላቱ መግዘፍ በርካቶች ቢሳለቁበትም የሚያበረቱ ጥቂት አብሮ አደጎቸን ነበሩት፡፡
👉አንድ ቀን ወላጅ አባቱ በቀን 200 ሩፒ የሚያስገኝ የስራ እድል ቀረበላቸው፡፡ ስራው ልጃቸውን ለአስቂኝ ትዕይንት የቡድናቸው አባል ለማድረግ ከወጠኑ የሰርከስ ቡድን ባልደረቦች የመጣ ነበር፡፡ ወላጅ አባቱ ቆፍጠን ያለ መልስ ሰጡ፤ "ልጄ ተምሮ ሀኪም ይሆናል…"
👉በህንድ ጉጃራት ግዛት ተወልዶ ያደገው የ23 ዓመቱ የዓለማችን አጭሩ ዶክተር ጋነሽ ባርያ የወላጅ አባቱን ውለታ ተናግሮ አይጠግብም፡፡ ልጃቸውን ሰርቀው ለስራ እንዳይወስዱባቸው ሰግተው ስራቸውን ጥለው ከእርሱ ጋር ትምህርት ቤት እስከዋል ደርሰው ነበር፡፡
👉ጋነሽ ባለበት አካላዊ የአቅም ውስንነት ሳይበገር በጥሩ ውጤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ደርሶ ህክምና ለማጥናት "ብሃቭናጋር" ወደ ተባለ የመንግስት ኮሌጅ ማመልከቻ አስገባ፡፡ ኮሌጁ ግን ተቀብሎ ሊያስተምረው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡
👉ጉዳዩን ወደ ሕንድ የሕክምና ምክር ቤት ወሰደው፡፡ የምክር ቤቱ መልስም "በ91 ሳ.ሜ ቁመት በአስቸኳይ ሁኔታዎች ውስጥ የህክምና ተግባር መፈጸም አይቻልም" የሚል ነበር፡፡ የሀገሪቱን የትምህርት ሚኒስቴር እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠንቶ መፍትሄ ሲያጣ የፍትሕ ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዳዩን ወደ ሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አደረሰው፡፡
👉በመጨረሻም እ.አ.አ በ2018 ፍርድ ቤቱ ለጋነሽ በቀዶ ጥገና ትምህርት ክፍል ውስጥ የመመዝገብ መብት ሰጠው፡፡ በብሃቫናጋር በሰር-ቲ ሆስፒታል ውስጥ በተለማማጅ ዶክተርነት እየሰራ የሚገኘው እጩ ዶ/ር ጋነሽ ባሪያ በቅርቡ ትምህርቱን ያጠናቅቃል፡፡
👉"ከሦስት ዓመታት በፊት በጣም ተከፍቼ ነበር፣ አትችልምን ለመቀበል ባለመፍቀዴ ግን እዘህ ደርሻለሁ"ይለል እንደማንኛውም ሰው ጥሩ ኑሮ መኖር እና ወላጆቹ ማኮራት እንደሚፈልግም መናገሩን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያመላክታል፡፡
Via 👉EBC
@seleeewnet