አለሕግ🟠AleHig dan repost
አስገዳጅ የውል ህግ ድንጋጌዎች
=====================
• አስገዳጅ የውል ህግ ድንጋጌዎች (Mandatory provisions of the low of contract) በባህሪያቸው ተዋዋይ ወገኖች ውል የመዋዋል ነፃነታቸውን ተጠቅመው የውል ስምምነት ሲያደርጉ በግዴታ ሊከተሉት የሚገባውንና ሊያሟሉ የሚገባቸውን መሥፈርቶች የሚደነግጉ ናቸው፡፡
እነዚህ ድንጌጋዎች ህግ አውጭው ተዋዋይ ወገኖች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ትእዛዝ የሚሰጥባቸው ብቻ ሣይሆኑ ህግ አውጭው በድንጋጌዎቹ የሰጠውን ጥብቅ ትእዛዝ አለመፈፀም ወይም አለማሟላት ውሉን ህጋዊ ህልውና እንዳይኖረው የሚያደርግ ውጤት አልባ (Void) ወይም ውሉ እንከን ያለበትና ፈራሽ (voidable) እንዲሆን የማድረግ ሀይልና ጉልበት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው በህግ ፊት የፀና እንዲሆን ከፈለጉ አስገዳጅ የሆኑ የውል ህግ ድንጋጌዎችን መከተልና ማሟላት አለባቸው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 34803 ቅጽ 8
via Legal consulting limited
#ሼር #አለ #Share #ALE
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties